AM/Prabhupada 0088 - የእኛ ማህበር ውስጥ የገቡ ሁሉ የማዳመጥ አዝማማያቸውን ያበረከቱ ናቸው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on BG 7.1 -- San Diego, July 1, 1972

ጌታ ብራህማ እንዲህ አለ፡፡ ጌታ ብራህማ በመላው የትእይንተ ዓለም ውስጥ በከፍተኛው ደረጃ የሚገኝ ነዋሪ ነው፡፡ እርሱም እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ "አንድ ሰው ይህንን ግምታዊ ምርምር እርግፍ አድርጎ መተው ይገባዋል፡፡ " "ግያኔ ፕራያሳም ኡዳፓስያ" በዚያን ግዜም ትሁት መሆን ይጠበቅበታል፡፡ አንድ ሰው ሁሉንም ነገር እንደሚያውቅ ሰው ሆኖ መቅረብ አይገባውም፡፡ በምርምር እና በግምታዊ መንገድ አንድ ነገር መፍጠር እችላለሁ ብሎ ማሰብ አይገባውም፡፡ ይህም ልክ እንደ ሳይንቲስቶች ይመሰላል፡፡ እነርሱም ግምታዊ በሆነ የምርምር መንገድ ከፍተኛ ግዜን ሲያባክኑ ይታያሉ፡፡ ምንም አዲስ ነገር በእኛ ሊፈጠር አይቻልም፡፡ ሁሉም ነገር በዓብዩ ጌታ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው፡፡ ምንም ዓይነት የተፈጥሮን ባህሪ ለመቀየር አንችልም፡፡ ይህም የተፈጥሮ ሕግጋት ግን እንዴት እንደተቀነባበረ ለማየት እንችላለን፡፡ ይህንን ያህል ማድረግ እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን የተፈጥሮን ሕግ ለመቀየርም ሆነ የተሻለም ስፍራ ከተፈጥሮ ውጪ ለመፍጠር አንችልም፡፡ ይህም አይቻልም፡፡ ይህንን ለማድረግ አንችልም፡፡ ዳይቪሂ ኤሻ ጉና ማዪ ማማ ማያ ዱራትያያ (BG 7.14) ዱራትያያ ማለት በጣም አስቸጋሪ ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ጌታ ቼታንያ ማሀ ፕራብሁ ይህንን የጌታ ብራህማን ቃላቶች ሰማ፡፡ ይህም አንድ ሰው ግምታዊ የሆነውን የምርምር ጥረት ማቆም እንደሚገባው እና አንድ ሰው ምንም ዓይነት ነገር መፍጠር እንደማይችል ሰማ፡፡ እነዚህ ስሜት የማይሰጡ ልማዶች ሁሉ መቆም ይኖርባቸዋል፡፡ አንድ ሰው በጣም ትሁት መሆን ይገባዋል፡፡ ይህም ከሳር በታች ትሁት መሆን ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ምንም እንኳን ሳርን በእግራችን ብንረጋግጠውም ምንም ዓይነት ብሶት አያሰማንም፡፡ "እሺ ጌታዬ ተራመድብኝ" ይህንን የመሰለ ትህትና ማለት ነው፡፡ "ትርናድ አፒ ሱኒቼና ታሮር አፒ ሳሂሽኑና" ታሩ ማለት ዛፍ ማለት ነው፡፡ ዛፍ በጣም ከፍተኛ ትእግስት ያለው ነው፡፡ ስለዚህ ቼታንያ መሀብራብሁ እንዲህ ብሎናል፡፡ "ግያኔ ፕራያሳም ኡዳፓስያ ናማንታ ኤቫ" "ከዚያስ? እንደ ምክርህ ይህንን የግምታዊ ምርምር ስርዓት በመተው ትሁት ከሆንኩስ በኋላ ምን ማድረግ ይገባኛል?" የሚቀጥለውም ሀላፊነት “ናማንታ ኤቫ” ከትሁትነት በኋላ “ሳን ሙክሀሪታም ብሀቫዲያ ቫርታም” ከትሁትነት በኋላ አንድ ሰው ትሁት የሆነ የዓብዩን ጌታ አገልጋይን መቅረብ ይገባዋል፡፡ ከእርሱም በማዳመጥ መማር ይገባዋል፡፡ “ስትሃኔ ስትሂታህ” ባላችሁበትም መቆየት ትችላላችሁ፡፡ እንዳላችሁበትም በአሜሪካ ውስጥ መቅረት ትችላላችሁ፡፡ ወይንም ህንድ መሆን ትችላላችሁ፡፡ ወይንም ክርስትያን መሆን ትችላላችሁ፡፡ ወይንም ሂንዱ መሆን ትችላላችሁ፡፡ ጥቁር ወይንም ነጭ ሰው ሆናችሁ መቅረትም ትችላላችሁ፡፡ ሴት ወይንም ወንድ ሆናችሁም መቅረት ትችላላችሁ፡፡ ይህም እንደ ፈቃዳችሁ ይሆናል። ማድረግ የሚገባችሁ ግን የመስማት ሀይላችሁን በመንፈሳዊ ንቃት ለዳበረ ሰው ስጡት፡፡ ይህ ነው የተመከረው፡፡ በሰማችሁም ግዜ ማሰላሰል ትችላላችሁ፡፡ ለምሳሌ አሁን እኔን እያዳመጣችሁኝ ነው፡፡ ይህንንም ስዋሚጂ የተናገረነውን ነገር በማስታወስ የምታሰላስሉ ከሆነ “ስትሃኔ ስቲሂታሀ ሽሩቲ ጋታም ታኑ ቫን ማኖብሂህ” ”ሽሩቲ ጋታም“ ሽሩቲ ማለት በጆሮዋችን ማዳመጥ ማለት ነው፡፡ በማሰላሰል እና ገላችሁን እና ሀሳባችሁን የምትጠቀሙ ከሆነ ቀስ በቀስ ለመረዳት ትችላላችሁ፡፡ ምክንያቱም ዓላማችሁ ራስን ስለማወቅ በመሆኑ ነው፡፡ ራሳችን ማለትም ከፍተኛው ሀይል ማለት ነው፡፡ ዓብዩ ጌታ ታላቅ ሲሆን እኛ ደግሞ የእርሱ ቅንጣፊ እና ወገን ሆነን እንገኛለን፡፡ በዚህም ስርዓት ጌታ ቼታንያ መሀ ፕራብሁ እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ ዓብዩ ጌታ ወይንም “አጂታ” ፈፅሞ ሊሸነፍ የማይችል ነው፡፡ በግምታዊ ምርምር እና በእልህ ዓብዩ ጌታን ለመረዳት ብንሞክር ፈፅሞ ልናውቀው አንችልም፡፡ ዓብዩ ጌታ ፉክክር ውስጥ አይገባም፡፡ ይህም አብይ በመሆኑ ነው፡፡ ዓብዩ ጌታ የኛን ፉክክር ለመቋቋም ምን ፍላጎት ይኖረዋል? እንዲህም እንል ይሆኖል፡፡ “ውድ ዓብዩ ጌታዬ ሆይ በውኔ እንዳይህ ወደ እዚህ ቀረብ በልልኝ፡፡” ዓብዩ ጌታ እንዳሻን ልንጠራው ወይንም ልናዘው የምንችለው አይደለም፡፡ በተቃራኒ መንገድ ግን እኛ የእርሱን ትእዛዝ መቀበል ይገባናል፡፡ ይህ የዓብዩ ጌታን ንቃት መያዝ ማለት ነው፡፡ ዓብዩ ጌታም እንዲህ ብሏል፡፡ “ሙሉ አንደበትህን ለእኔ ስጥ፡፡” ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሸረናም ቭራጃ“ (BG 18.66) ዓብዩ ጌታን ለመረዳትም ስርዓቱ ይህ ነው፡፡ ”ዓብዩ ጌታን አውቃለሁ“ በሚል ትእቢት ልንረዳው አንችልም፡፡ ወይንም ጥሩ አእምሮ ስላለኝ በግምታዊ ምርምር እደርስበታላሁ በማለት አምላክን ልንረዳ አንችልም፡፡ ስለዚህ ይህ ማዳማጥ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ የመስማት ስርዓት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም የክርሽና ንቃተ ማህበራችን የተስፋፋው ወደ ማህበራችን የገቡ ተማሪዎች ሁሉ በጥሞና መንፈሳዊ መልእክቱን በማዳማጥ ላይ ስለነበሩ ነው፡፡ ይህም ማዳመጥ መንፈሳቸውን ሁሉ ለመቀየር በቃ፡፡ በዚህም ምክንያት ወደ ማህበራችንን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ የቀድሞ ሕይወታቸውን በመተው ለማገልገል ሲመጡ እናያቸዋለን፡፡ ይህም በመቀጠል ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ማዳመጥ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለሕብረተሰቡም ሁሉ የመንፈሳዊ መልእክትን የማዳመጥ እድል ለመስጠት በየቦታው ቅርንጫፎችንም በመክፈት ላይ እንገኛለን፡፡ ስለዚህ ይህንን የማዳመጥ እድል እንድትጠቀሙበት እንጠይቃችኋለን፡፡