AM/Prabhupada 0090 - የተቀነባበረ አስተዳደር መኖር አለበት፡፡ አለበለዛ ግን ይህ የዓለም ዓቀፍ የክርሽና ንቃት ድርጅት እንዴት ሊሳካ ይችላል

Revision as of 06:06, 29 November 2017 by Sahadeva (talk | contribs) (Text replacement - "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->" to "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Morning Walk -- December 5, 1973, Los Angeles

ፕራብሁፓድ፡ “ሁሉም ሰው የክርሽና ቤተሰብ አካል ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሰው ለክርሽና ምን እያደረገ እንዳለ መገምገም ያስፈልጋል፡፡” ለምሳሌ ሁሉም የመንግስት ዜጋ ነው፡፡ ሆኖም እያለ፡ አንዳንድ ሰው ትልቅ ኃላፊነት ወይንም ደረጃ ተሰጥቶት እናያለን፡፡ ፕራብሁፓድ፡ ይህ ለምን ሆነ? ምክንያቱም በባህሪው የታወቀ ሰለሆነ ነው፡፡ ሱዳማ፡ አይደለምን? ፕራብሁፓድ፡ “ስለዚህም አንድ ሰው ለክርሽና አገልግሎቱን መስጠት ይገባዋል፡፡ እኔ የክርሽና ቤተሰብ ነኝ ማለቱ ብቻ በቂ አይደለም፡፡” ሱዳማ፡ አዎን ያ ጥሩ አይደለም፡፡ ፕራብሁፓዳ፡ ያ ጥሩ አይደለም። ይህም እንደ ሲኦል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ማገልገል ካልጀመረ፡ክርሽናን እንደገና መርሳትን ይመጣል፡፡ ሱዳማ፡ “እነዚህ ክርሽናን የረሱ ሃይል ሊኖራቸው ይችላል” ”ምንም እንኳን የክርሽና ቤተሰቦች ቢሆኑም“ "ክርሽናን በጣም በመርሳታቸው፡ እኛንም ክርሽና እንድንረሳ ሊገፋፉን ይችላሉ፡፡" ፕራብሁፓዳ፡ መርሳት ማለት “ማያ” ማለት ነው፡፡ ሱዳማ፡ አዎን፡ ፕራብሁፓዳ፡ ማያ ማለት ክርሽናን መርሳት ማለት ነው፡፡ ይኅው ነው፡፡ መርሳት በተፈጥሮ የተከሰተ እና የቆመ ነገር አይደለም፡፡ ነገር ግን የሰው ልጅ በዚህ ሲጠቃ፡ አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ይወድቃል፡፡ ሱዳማ፡ “ከዚህ በፊት ድቮቲ አገልጋዮች ደስተኛ አለመሆናቸውን ገልጸውልኛል” ታድያ ደስተኞች ካልሆኑ፡ በዚህ በክርሽና ንቃት መቀጠል ይገባቸዋልን? እኔም እንዲህ እላቸዋለሁ፡ “አንድ ሰው ደስተኛ ካልሆነ” (ፕራብሁፓድ) አንተ እራስህ በምሳሌ ማስተማር አለብህ፡፡ አንተ የተለየ ምሳሌ የምታሳይ ከሆነ እንዴት አድረገው ሊከተሉህ ይችላሉ? "ምሳሌ ከህግጋት የተሻለ ነው፡፡" ለምንድን ነው አንተ ውጪ ይምትኖረው? (ሱዳማ) እኔ: (ሱዳማ)፡ ባለፈው ግዜ ህምም በጣም በርትቶብኝ ነበር፡፡ ሰለዚህም ይህንን ቦታ ትቼ ለመሄድ በቃሁ፡፡ ይህ ማለት ህብረተሰቡን መልቀቅ ይገባናል ማለት አይደለም፡፡ ህንድ አገር ሂጄ ህምሜን ለማስታመም በቅቼ ይሆናል፡፡ ወይንም ወደ ለንደን ሂጄ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን እንቀበለዋለን፡፡ ስለዚህ የጤና ጉዳይ ምክንያት ሊያመጣ ይችላል፡፡ ነገር ግን ህርረተሰቡን ገድፈን መሄድ ይኖርብናል ማለት አይደለም፡፡ እዚህ ለጤናዬ ተስማሚ ካልሆነ፡ ወደ ሌላ መሄድ እችላለሁ፡፡ በመቶ የሚቆጠሩ ቅርንጫፎች አሉንና፡፡ ህምመህንም ለማስታመም ከዚህ ትዕይነተ ዓለም ውጪ አትወጣምና፡፡ በዚሁ ትዕይንተ ዓለም ውስጥ ቀርተህ ማስታመም አለብህ፡፡ ታድያ ለምንድነው ከህብረተሰቡ ወጥተህ የምትገኘው? ሽሪ ናሮታማ ዳስ ታኩር፡ ከትጉህ አገለጋይ ድቮቲዎች ጋር መኖር ይገባናል፡፡ ለምንድነው እኔ ቤተሰቤን ትቼ የሄድሁት? ይህም እነርሱ ትሁት አገልጋዮች ባለመሆናቸው ነው፡፡ ሰለዚህም ወደ እዚህ መጣሁ፡፡ አለበለዛ ግን፡ በዚህ በእርጅና ግዜዬ፡ የተመቸ ኑሮ መያዝ እችል ነበረ፡፡ ትጉህ አገለጋይ ድቮቲ ካልሆኑ ሰዎች ጋር መኖር አይገባንም፡፡ ቤተሰብም ሆነ ማንም ሰውም ቢሆን፡፡ ልክ እንደ ማሀራጃ ቪብሃሴና፡፡ ወንድሙ ትጉህ አገልጋይ ድቮቲ ባለመሆኑ፡ ትቶት ሄደ፡፡ ወደ ራማቻንድራም ሄደ፡፡ ቪብሀሴና፡፡ ይህን ታውቃላችሁን? (ሱዳማ) አዎን፡፡ ( ህርዳያናንዳ)፡ ፕራብሁፓድ፡ እንደተገለፀው፡ ሳንያሲ (መሎክሴ) ብቻውን መኖር ይገባዋል ሲባል፡ ከድቮቲዎች ወይንም አገልጋዮች ጋር ነው ማለት ነው፡፡ አይደለምን? (ፕራብሁፓድ)፡ ማን? የት ነው ሳንያሲ ብቻውን ሊኖር ይገባዋል ተብሎ የተገለፀው? (ህርዳያናንዳ)፡ ማለቴም፡ አንዳንድ ግዜ መፅሀፍቶችህ ውስጥ ተጠቅሷል፡፡ (ፕራብሁፓድ) ምን አልክ? ( ህርዳያናንዳ)፡ አንዳንድ ግዜ መፅሀፍቶችህ ውስጥ ተጠቅሷል፡፡ ታድያ ይህ ማለት ከድቮቲዎች ጋር ማለት ነውን? (ፕራብሁፓድ)፡ በአጠቃላይ ደረጃ፡ ሳንያሲ ብቻውን ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን የሳንያሲ ሀላፊነት መስበክ ነው፡፡ (ሱዳማ)፡ ይህንንስ ፈጽሞ ማቆም አልፈልግም፡፡ (ፕራብሁፓድ)፡ ምን አልክ? (ሱዳማ)፡ መስበክን በፍጹም ለማቆም አልፈልግም፡፡ (ፕራብሁፓድ)፡ መስበክን እራስህ ለመፍጠር አትችልም፡፡ መስበክ የምትችለው፡ በመንፈሳዊው አባትህ በተሰጠህ መመሪያ እየተከተልክ ሲሆን ብቻ ነው፡፡ የራስህን የሆነ የመስበክ ስልት ልትፈጥር አትችልም፡፡ መመሪያውን መከተል ያስፈልግሀል፡፡ መሪ መኖር ይገባዋል፡፡ በመሪውም ስር መተዳደር ይገባል፡፡ "ያስያ ፕራሳዳ ብሃገቫት" ለምን ይህ ተጠቀሰ? በማንኛቸውም ቢሮዎች ብንመለከት፡ የቢሮው ሀላፊ ይገኛል፡፡ እርሱንም ማስደሰት ይገባሀል፡፡ ይህ ነው አገልግሎቱ፡፡ በቢሮ ውስጥም በሚገኙት ንኡስ ክፍል፡ የክፍሉ ሀላፊዎች ይገኛሉ፡፡ ሆነም ግን፡ አንተ እንደአሻህ የምተሰራ ከሆነ፡ "እኔ እንዲህ ነው ለመስራት የሚመቸኝ" በማለት፡ ሆነም የቢሮው ሀላፊ ካልተደሰተብህ፡ ይህ አይነት አገልግሎት አሰደሳች ይመስለሀል? እንደዚሁም ሁሉ የትም በሄድንበት ቦታ ሁሉ፡ ሀላፊ የሆነ ሰው ይገኛል፡፡ ሰለዚህም እንደ ሀላፊው ትእዛዝ መስራት ይገባናል፡፡ ይህም ስርአት ያለው ይሆናል፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው የፈለገውን መፍጠር ከጀመረና፡ የራሱ የሆነ አኗኗር መፈልሰፍ ከጀመረ፡ የተበጠበጠ ኑሮ ሊሆን ይችላል፡፡ (ሱዳማ)፡ አዎን ይህም ትክክል ነው፡፡ (ፕራብሁፓዳ)፡ አዎን፡ በአሁኑ ግዜ ድርጅታችን ዓለም አቀፍ ነው፡፡ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ የሆኑ ነገሮችም ያስፈልጉናል፡፡ ይህንንም መንፈሳዊ እና ቁሳዊ የሆኑ አስፈላጊ ነገሮችን፡ በጥሩ ስርዓት ማስደዳደር አለብን፡፡ አለበለዛ እንዴት አድረገን ልንቋቋመው እንችላነን? ለምሳሌ፡ ጎውራ ሱንደር፡ ቤት ሽጦ ነበረ፡፡ ነገር ግን ገንዘቡ ወዴት እንደገባ አይታወቅም፡፡ ይህስ ምንድን ነው? የጠየቀውም ሰው ማንም የለም፡፡ ቤቱ ተሸጠ፡ ነገር ግን ገንዘቡ የት እንደገባ ሊታወቅ አልተቻለም፡፡