AM/Prabhupada 0091 - እዚህ ራቁትህን ቆመህ፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Morning Walk -- July 16, 1975, San Francisco

ድሃርማድህያክሻ:በአሁኑ ግዜ ስህተታቸውን በመረዳት:ስለሞት ጥናታቸውን በመቀጠል ላይ ይገኛሉ: የሰው ልጅን ለሞት ለማዘጋጀት ጥረት እያደረጉ ነው: ግን ሊነግሯቸው የሚችሉት “ሞትን ተቀበሉት” ማለት ብቻ ነው: ማለት የሚችሉት ነገርም “መሞትህ አይቀርም” ብቻ ነው: “ስለዚህም በደስተኝነት ተቀበለው” ፕራብሁፓዳ:ግን መሞት አልፈልግም:ለምን ደስተኛ መሆን አለብኝ? አንተ ተንኮለኛ “ለሞት ደስተኛ ሁን ትለኛለህ?” (ሳቅ) “በደስታ መሰቀል” (ሳቅ) ዳኛው እንዲህ ይላል “ግድ የለም:ፍርዱ ተፈርዶብሃል” “አሁን መሰቀልን በደስታ ተቀበል” (ሳቅ) ድሃርማድህያክሻ:የዘመኑ የሳይኮሎጂ መድረሻው የሰውን ልጆች በዚህ አለም ላይ እንዲኖሩ: ህይወታቸውን እንዲያስተካክሉ መርዳት ነው: ይህን አለም ደግሞ ለቅቀን ወደ ሌላ አለም ለመሄድ ስንመኝ ደግሞ:አሁን እብድ ሆናችኋል ይሉናል: እንደዚያ ሳይሆን አሁን ወደ እዚህ አለማዊ ኑሮ ራስን ማስተካከል ያስፈልጋል ይሉናል: ባሁላሽቫ:የህይወትን ስቃይ እንዴት መቀበል እንዳለብንም ያስተምሩናል:ሁሉን ስቃይ ችለን መኖር እንዳለብን ያስተምሩናል: ፕራብሁፓዳ:ለምን ይህ ሁሉ ስቃይ?እናንተ ትላልቅ ሳይንቲስቶች ናችሁ:ይህንን ችግር መፍታት አትችሉም? ድሃርማድህያክሻ:ችግሩን ሊፈቱት አይችሉም:ምክንያቱም እራሳቸውም ይኅው ችግር አላቸው: ፕራብሁፓዳ:ይህም የተመሳሰለ ሎጂክ ነው “በደስተኝነት መሰቀል” ይኅው ነው: አንድ አስቸጋሪ ርእስ ሲያገኙ:እርግፍ ያደርጉታል: የማይረባ ግምትም ይገምታሉ:ይኅው ነው: ይህ ነው ትምህርታቸው: ትምህርት ማለት:“አትያንቲካ ዱህካ ኒቭርቲ” የጭንቀት ሁሉ የበላይ መፍትሄ ማለት ነው: ይህ ነው ትምህርት ማለት:“ሞትን በደስታ ተቀበለው” ማለት ግን ትምህርት አይደለም ”ዱክሃ“ ጭንቀት ምንድን ነው?ይህም በክርሽና ተገልጿል: ”ጃንማ ምርትዩ ጃራ ቭያድሂ ዱክሃ ዶሳኑ“ (ብጊ13 9) እነዚህ ናቸው የእናንተ ጭንቀት:መፍትሄም ፈልጉለት: ይህን ግን በጥንቃቄ ወደ ጎን አድርገውታል: ሞትን:መወለድን:ማረጅን: መታመምን:ሊያቆሙ አይችሉም: በዚህም በአጭር ህይወታችን:በትውልድ እና በሞታችን መሃል:ትላልቅ ህንፃ ይገነባሉ: የሚቀጥለው ግዜ ደግሞ በሰራው ህንጻ ውስጥ:አይጥ ሁኖ ሊወለድ ይችላል: ይህ ተፈጥሮ ነው:ማንም ሊያቆመው አይችልም: ሞትንም መሸሽ አይቻልም:እንደዚሁም ተፈጥሮ ሌላ ገላ ይሰጣችኋል: በዚህም ዩኒቨርስቲ ዛፍ መሆን ትችላላችሁ:ለ5000 አመት መቆምም ትችላላችሁ: ራቁት መሆን ከፈለጋችሁም:ማንም ሰው አይቃወምም:እንደዛፍ ራቁት መቆም ትችላላችሁ: