AM/Prabhupada 0094 - ስራችን የክርሽናን ቃላቶች መደጋገም ብቻ ነው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on BG 1.20 -- London, July 17, 1973

ሕይወቱ በመንፈሳዊ ህልውና ያልተመሰጠ ሰው፡ ስለ አብዩ አምላክ ምርምር አያደርግም፡ ወይንም ሊረዳውም አይችልም፡፡ ይህንንም ጥቅስ ከዚህ ቀደም ደጋግመን አንስተነዋል፡፡ "ዬሻም ትቭ አንታ ጋታም ፓፓም ጃናናም ፑንያ ካርማናም ቴ ድቫንድቫ ሞሀ ኒርሙክታ ብሀጃንቴ ማም ድርድሃ ቭራታሀ" (ብጊ 7.28) ፓፒስ ወይንም ሀጥያተኛ የሆኑ ሰዎች፡ ይህንን ሊረዱ አይችሉም፡፡ የሚረዱትም ወይንም የሚያስቡትም፡ "ክርሽና ብሀገቫን ከሆነ፡ እኔም ራሴ ብሀገቫን ነኝ" በማለት ነው፡፡ "ክርሽና እንደ እኔ ተራ ሰው ነው፡፡ ምናልበት ሀይሉ ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል፡፡ በታሪክም በጣም የታወቀ ሰው ሊሆን ይችላል፡፡" "ይሁን እንጂ ዞሮ ዞሮ ሰው ነው፡፡ እኔም እራሴ ሰው ነኝ፡፡ ታድያ እኔስ ለምን አምላክ አልሆንም?" ይህ የአብሀክታዎች ወይም የአምላክ አገልጋይ ያልሆኑ እና የሀጥያተኞች አስተሳሰብ ነው፡፡ እንደዚህም ሁሉ፡ ማንም ሰው እራሱን እንደ አምላክ አድርጐ የሚቆጥር ሰው፡ በጣም ትልቅ ሀጥያተኛ እንደሆነ መረዳት ይገባናል፡፡ የዚህንም አይነት ሰው ሕይወት ብታጠኑ፡ የአንደኛ ደረጃ ሀጥያተኛ ሰው እንደመሆኑ መረዳት ትችላላችሁ፡፡ በዚህ ነው መረዳት የምንችለው፡፡ ሀጥያተኛ ያለሆነ ሰው ግን እኔ አምላክ ነኝ ብሎ ሊያስብ አይችልም፡፡ ይህ አይነቱ ውክላና በሀሰት የተሞረኮዘ ስለሆነ ነው፡፡ ማነም ሰው እንዲህ ሊያስብ አይችልም፡፡ መንፈሳዊ ሰው እንደዚህ ፈጽሞ አያስብም፡፡ ደረጃውን በትክክል ያውቃልና፡፡ "እኔ ማን ነኝ? እኔ ተራ ሰው ነኝ፡፡ እንዴትስ አድርጌ፡ የአብዩ አምላክን ደረጃ ለመውሰድ እችላለሁ?" እነዚህም ሀጥያተኞች፡ በተንኮለኞች መሀከል በጣም ታወቂ ሁነው ይገኛሉ፡፡ በሽሪማድ ብሀገቨታም እንደተገለፀውም ሁሉ፡ "ሽቫ ቪድ ቫራሆስትራ ክሀሬይህ" (ሽብ 2.3.19) ይህስ ጥቅስ ሰለምን ያስተምረናል? "ኡስትራ ክሀሬይህ ሳምስቱታሀ ፑሩሻ ፓሹ" በዚህ ዓለም ላይ ብዙሀን ታላላቅ ተብለው የሚጠሩ ሰዎች እናያለን፡፡ እነዚህም ታላላቅ የሚባሉ ሰዎች በህዝብ ሲመሰገኑ እናያለን፡፡ ብሀገቫታም እንደዚህ ይለናል "ማነም ሰው ቢሆን የአምላክ አገልጋይ ካልሆነ" "የሀሬ ክርሽናንም ቅዱስ ስም የማይዘምር ከሆነ" በነዚህ በተንኮለኛ ሰዎች፡ ታላቅ ተብሎ ሊታወቅ ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን ከእንስሳ ተነጥሎ ሊታይ አይችልም፡፡ ሰለዚህም እንዲህ ተብሎ ተጠቅሷል፡ "ሽቫ ቪድ ቫራሃ ኡስትራ ክሀሪይህ" "ሰለዚህም እንዴት ታላላቅ ሰዎች ብለን ለመጥራት እንችላለን? ምክንያቱም ታላቅ ሰው የምንለው ከእንስሳ በላይ ሊቆጠር የማይችል ነው፡፡" በዚህ አለም ላይ፡ የእኛ ስራ ምንም ምስጋና የሌለው ስራ ነው፡፡ ምክንያቱ አንድ ሰው መንፈሳዊ ወይንም የአምላክ አገልጋይ ካልሆነ፡ ተንኮለኛ ወይንም ሀጥያተኛ ብለን እንጠራዋለን፡፡ ይህን በጣም ከበድ ያለ እና የማይዋጥ አነጋገር ነው፡፡ ነገር ግን ግልጹን መናገር ግዳጃችን ነው፡፡ አንድ ሰው የክርሽና አገልጋይ አለመሆኑን ስናይ፡ ወዲያው ተንኮለኛ ሰለመሆኑ እንረዳለን፡፡ እንዴትስ ይህን ለማለት እንችላለን፡፡ ይህ ሰው ጠላቴ አይደለም፡፡ ቢሆንም ግን ግልጹን መናገር ይገባናል፡ ምክንያቱን ይህ በክርሽና የተገለፀ ሰለሆነ ነው፡፡ የክርሽና ንቃታችንም የዳበረ ከሆነ፡ ማድረግ ያለብን ሁሌ የክርሽናን ቅዱስ ስም ደጋግሞ መዘመር ነው፡፡ በክርሽና ተዋካዮች እና ክርሽናን ከማይወክሉ ሰዎች መሀከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? ልዩነቱም የክርሽና ተወካዮች ሁሌ ክርሽና የተናገረውን ደጋግመው ይፈጽማሉ፡፡ በዚህ ምድር ላይም የክርሽና ተወካዮች ሁነው ይገኛሉ፡፡ ይህንንም ለማድረግ ብዙ ሙያ አይጠይቅም፡፡ የሚጠበቅብንም በሙሉ ልቦና እና እምነት ክርሽና የተናገረውን ደጋግመን መፈፀም ነው፡፡ ክርሽናም እንዲህ ብሏል፡ "ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ (ብጊ 18.66) ይህንንም በጥሩ ልቦና የተቀበለ ሰው እንዲህ ብሎ ያስባል "ለክርሽና ሙሉ ልቦናዬን ከሰጠሁት፡ ሁሉ ሰራዬ የተሳካ ይሆናል" እንዲህም የሚያስብ የክርሽና ተወካይ ነው፡፡ በጣም የተማረ ወይንም የበለፀገ ሰውም ለመሆን መጣጣር አያስፈልግም፡፡ ይህም ክርሽና የሚያስተምረንን በቀላሉ የምንቀበል ከሆነ፡ ማለት ነው፡፡ አርጁናም እንዲህ ብሎ ገልጾልናል፡ "ኤታም ርታም ማንዬ ያድ ቫዳሲ ኬሻቫ (ብጊ 10.14) "ክርሽና ሆይ፡ ኬሻቫ ሆይ፡ የምትነግረኝን ሁሉ፡ምንም ቀይሬ ሳልረዳ፡ በሙሉ ልቦና ተቀብዬዋለሁ፡፡ ይህም የብሀክታ አስተሳሰብ ነው፡፡ ሰለዚህም አርጁና "ብሀክቶ ሲ" ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ይህ የብሀክታ ወይንም የአገልጋይ አንደበት ነው፡፡ ለምን ብዬ ክርሽና እንደ እኔ ተራ ሰው አድርጌ አስበዋለሁ? የብሀክታ እና ብሀክታ ያልሆነ ሰው ልዩነቱ ይህ ነው፡፡ ብሀክታ ወይንም አገልጋይ፡ "እኔ ከምንም የማልቆጠር የክርሽና ቅንጣፊ ሀይል ነኝ" ብሎ ያስባል፡፡ ክርሽና ሰው ነው፡፡ እኔም ሰው ነኝ፡፡ ነገር ግን የክርሽናን ሀይል እና የእኔን ሀይል ስናወዳድር፡ የእኔ ሀይል በዝቅተኝነቱ ከምንም የሚቆጠር እንዳልሆነ እናገኘዋለን፡፡ ይህ ነው የክርሽና ንቃት ማለት፡፡ ይህንንም ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ሀጥያተኛ ሳይሆን፡ ትሁት መሆን ብቻ ነው የሚገባው፡፡ ሀጥያተኛ ሰው አምላክን ለመረዳት ያዳግተዋል፡፡ ሀጥያተኛ ሰው እንዲህ ይላል "ክርሽና ሰው ነው፡ እኔም ሰው ነኝ፡ ታድያ ለምን እኔ እራሴ አምላክ ልሆን አልችልም?" አምላክ የሚሆነው እርሱ ብቻ ነውን? እኔም፡ እርሱም፡ አንተም፡ ሁላችንም፡ አምላክ ለመሆን እንችላለን፡፡ ቪቬካናንዳም እንዲህ አለ፡ "ለምንድነው አምላክን የምትፈልጉት?" "ብዙ አምላኮች በመንገድ ሲዘዋወሩ አታዮአቸውምን?" "አያችሁ፡ ይህ ማለት አምላክን ማወቅ ማለት ነው" በዚህም በተሳሳተ አስተሳሰብ፡ አንድ ሰው ሁሉንም እንደ አምላክ በማየቱም፡ እንደ ትልቅ ሰው ሁኖ ይቆጠራል፡፡ ይህንንም አይነት ሞኝነት እና ተንኮለኝነት፡ በመላው ዓለም ላይ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ እንዲህ አይነቱም ሰው፡ አብዩ አምላክ ምን እንደሆነ፡ የሀይሉስ መጠን ምን ያህል እንደሆነ፡ አምላክ ማለት ምን እደሆነም አይረዳም፡፡ በአሁኑ ግዜም እነዚህን ተንኮለኞች እንደ አብዩ አምላክ አድረገው ይቀበሏቸዋል፡፡ ከዚያም ሌላ ተንኮለኛም የመጣ እና፡ እኔ ፈጣሪ አምላክ ነኝ ብሎ እራሱን አግንኖ ያወራል፡፡ ይህ አምላክ መሆንም ልክ የቀለለ ነገር ሁኖ ተቆጥሮ ይገኛል፡፡ ነገር ግን እንዲህ በማሰባቸው አእምሮ እንደሌላቸው ያስረዳናል፡፡ አምላክ ነኝ ብለን እራሳችንን የምንሰየመው፡ ምን ሀይል አለን እና ነው? ይህም የተሰወረ እና ሚስጢር ሁኖ የገኛል፡፡ የአብዩ አምላክ አገልጋይ ካልሆንም፡ ይህንን አምላክን የመረዳት ሚስጢር ለመረዳት አንችልም፡፡ ክርሽናም በብሀገቨድ ጊታ አንድ ሰው እንዴት እርሱን ሊረዳ እንደሚችል ገልጾልናል፡፡ "ብሀክትያ ማም አብሂጃናቲ ያቫን ያሽ ቻስሚ ታትቫታሀ" (ብጊ 18.55) ይህን በትሁት አገልግሎት ብቻ ነው፡፡ እንዲህም ለማለት ይችል ነበር፡፡ "በጣም ከፍ ባለ እውቀት ወይንም በዮጋ ስርአት" ወይንም እንዲህ ለማለት ይችል ነበር፡፡ "ትልቅ ካርሚ ወይም የዚህ አለም ትጉህ ሰራተኛ በመሆን፡ ሊረዳኝ ይችላል" ነገር ግን ይህንን አላለንም፡፡ እነዚህ "ካርሚ፡ ግያኒ፡ ዮጊ" የሚልዋቸው ሁሉ ተንኮለኞች ናቸው፡፡ ክርሽናንም ሊረዱት አይችሉም፡፡ ሁሉም ተንኮለኞች ናቸው፡፡ ካርሚስ ሶስተኛ ደረጃ ተንኮለኞች ናቸው፡፡ ግያኒስ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ተንኮለኞች ናቸው፡፡ ዮጊዎች ደግሞ አንደኛ ደረጃ ተንኮለኞች ናቸው፡፡ ይህ ነው ድምደማው፡፡