AM/Prabhupada 0113 - ምላሳችንን ለመቆጣጠር በጣም አስቸጋሪ ነው፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on SB 5.6.2 -- Vrndavana, November 24, 1976

ራጉናት ዳስ ጎስቫሚ የተባለው ባህታዊ መንፈሳዊ መመሪያውን በጥብቅ ይከተል ነበር፡፡ ጌታ ሽሪ ቼታንያ መሀፕራብሁም እንደዚሁ መመሪያውን በጥብቅ ይከተል ነበር፡፡ እንደዚሁም ሩፓ ጎስቫሚ የተባለው ባህታዊ መመሪያውን በጥብቅ ይከተል ነበር፡፡ ምንም እንኳን አንድ ሰው የባህታዊ ቁራጭ ልብስ ለብሶ በቭርንዳቫን ከተማ የሚኖር ቢሆንም ልክ እንደ ታላቁ ባህታዊ ሩፓ ጎስዋሚ ሆነ ማለት አይደለም፡፡ ሩፓ ጎስዋሚ ሙሉ በሙሉ በመንፈሳዊ አገልግሎት ላይ የተሰማራ ነበር፡፡ "ናና ሻስትራ ቪቻራናይካ ኒፑኖ ሳድ ድሀርማ ሳምስትሀፓኮ ሎካናም ሂታ ካሪኖ" ይኖሩ የነበረው በቭርንዳቫን መንፈሳዊ ከተማ ሲሆን ሀሳባቸው በሙሉ ግን እንዴት ለሰው ልጆች በዚህ ዓለም ላይ ጥሩ ነገር ማድረግ እንደሚችሉ ነበር፡፡ ይህም ልክ እንደ ፕራህላድ ማሀራጅ ይመሰላል፡፡ "ሶቼ ታቶ ቪሙክሀ ቼታሳ" የሳድሁ ወይንም የባህታዊ ሰው ሀሳብ ሁሉ ግዜ እንዴት በዓለማዊ መንገድ የተሳሳቱ ሰዎችን እንደሚረዳ ነው፡፡ በዚህ ዓለም ስቃይ ላይ ሰለሚገኙም ሀሳባቸው ሁሉ እንዴት ሊረዷቸው እንደሚችሉ ፕላን ማድረግ ነው፡፡ ሳድሁ ወይንም ባህታዊ ማለት እንዲህ ነው ፡፡ "ሎካናም ሂታ ካሪኖ" ሳድሁ ማለት "ልብሴን ቀየርኩኝ እና ባህታዊ ሆንኩኝ" ማለት አይደለም፡፡ "ባህታዊ ከመሰልኩም ሰዎች በስሜታቸው ተመስጠው ዳቦ ይሰጡኛል እርሱን በልቼ አረፍ እላለሁ" ማለት አይደለም፡፡ ይህ ሳድሁ ማለት አይደለም፡፡ ዓብዩ ጌታ ብሀገቫን ክርሽና ሳድሁ ማን እንደሆነ ገልጾልናል፡፡ "አፒ ቼት ሱ ዱራቻሮ ብሃጃቴ ማም አናንያ ብሀክ ሳድሁር ኤቫ ሳ ማንታቭያህ" (ብጊ፡ 9 30) ሳድሁ ማለት እንዲህ ነው፡፡ ሳድሁ ማለት ሕይወቱን በሙሉ ለዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና የሰዋ ማለት ነው፡፡ ምንም እንኳን አንዳንድ ጥሩ ያልሆኑ ልማድ ቢኖረውም ነው፡፡ ጥሩ ያልሆነ ልማድ ማለት ግን ሳድሁ ጥሩ ልማድ የለውም ለማለት ዓይደለም፡፡ምክንያቱም አንድ ሰው ሳድሁ ከሆነ... ምንም እንኳን በመጀመሪያ ግዜ መጥፎ ልማድ ቢኖረውም ይህ መጥፎ ልማድ ከግዜ በኋላ ሊጠፋ ይችላል፡፡ "ሻሽቫድ ብሃቨቲ ዳሃርማትማ ሺፕራም ብሀቫቲ ዳሀርማትማ ሽሽቫች ቻንቲም ኒጋቻቲ" አንድ ሰው ሳድሁ ወይንም ባህታዊ ለመሆን ከበቃ በአጭር ግዜ ውስጥ ከመጥፎ ልማዱ ሊወገድ ይችላል፡፡ ይህም ማለት በአጭር ግዜ ውስጥ ማለት ነው፡፡ የባህታዊ ሕይወትን ይዞ መጥፎ ልማድን ሳያስወግዱ መኖር አይቻልም፡፡ ይህ ሊሆን አይገባውም፡፡ ይህ የሳዱ ወይንም የባህታዊ ኑሮ አይደለም፡፡ ምናልባት ከቀድሞ ልማዱ አኳያ አንዳንድ ግዜ ስህተት ሊያደርግ ይችል ይሆናል፡፡ ለዚህም ምህረት ሊደረግለት ይገባል፡፡ ነገር ግን የሳዱ ወይንም የባህታዊ ኑሮ ላይ እያለ መጥፎ ልማዱን የሚቀጥል ከሆነ ይህ ንፁህ መንፈሳዊ ሰው ሳይሆን አታላይ ሰው ነው፡፡ ሳዱ ወይንም ባህታዊ አይደለም፡፡ "አፒ ቼት ሱ ዱራቻሮ" "ቼት ያዲ" በመጥፎ እድል ወይንም በስህተት ግን ሊሆን ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን የክርሽና መንፈሳዊ ንቃቱን በትጉህነት የሚቀጥል ከሆነ እንዲህ ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ "ሺፕራም ብሀቫቲ ድሀርማትማ ሻሽቫክ ቻንቲም ኒጋቻቲ" በመጀመሪያ ደረጃ ስህተት ሊኖር ይችላል፡፡ ቁም ነገሩ ግን ራስን እንዲህ ብሎ መጠየቁ ነው፡፡ "ከስህተቴ በመታረም ትምህርት ወስጃለሁ ወይ?“ ይህንንም ስህተት ለማረም ውስን መሆን ይገባናል፡፡ ”በተግባር እንጂ ሀሳባችንን ብቻ መተማመን የለብንም“ እዚህም የተሰጠን መመሪያ ይኅው ነው፡፡ ሀሳባችንን ብቻ መተማመን የለብንም፡፡ የእኔ መንፈሳዊ መምህር ወይም ጉሩ ማሀራጅ እንዲህ ይለን ነበር፡፡ ”ከእንቅልፋችሁ እንደተነሳችሁ ስህተት የተሞላበትን ሀሳባችሁን በጫማ መቶ ግዜ ደብድቡት“ የመጀመሪያው የቀን ተግባራችንም ይህ መሆን ይገባዋል፡፡ ከዚያው ማታ ወደ አልጋ ስትሄዱ ይህንኑ የተሳሳተ አንደበታችንን በመጥርጊያ ዱላ መቶ ግዜ ቀጥቅጡት፡፡ በዚህም መንገድ የተሳሳተ አንደበታችሁን ልትገሩት ትችላላችሁ፡፡ አለበለዛ ግን ሀሳባችን አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም ሀሳባችንን በጫማ እና በመጥረጊያ ዱላ መቀጥቀት ”ታፓስያ“ ወይንም በፍላጎት የሚያምረንን ነገር ለተሻለ ነገር መተው ማለት ነው፡፡ ሀሳባችንን ለመቆጣጠር የሚያዳግተን ሰዎች ሁሉ ይህንን ”ታፓስያ“ መለማመድ ይኖርብናል፡፡ ይህም የስህተት አንደበታችንን በጫማ እና በመጥረግያ ዱላ መደብደብ ማለት ነው፡፡ በዚህም መንገድ የተሳሳተ አንደበት ወይም ሀሳብን ለመቆጣጠር እንችላለን፡፡ ”ስዋሚ“ ወንም መነኩሴ ማላት ሀሳቡን ለመቆጣጠር የሚችል ማለት ነው፡፡ ”ቫቾ ቬጋም ክሮድሀ ቬጋም ኡዳራ ቬጋም ኡፓሽታ ቬጋም ማናሳ ቬጋም“ ”ክሮዳ ቬጋም ኤታን ቬጋን ዮ ቪሳሄታ ዲሂራሀ ፕርትሂቪም ሳ ሺስያት“ ቁጥር 11 ይህም የሩፓ ጎስዋሚ መመሪያ ነው፡፡ ”ቫቾ ቬጋም“ ይህም መቆጣጠርን መቻል ማለት ነው፡፡ ”ክራንዳና ቬጋም“ ማለት ደግሞ መቆጣጠርን አለመቻል ማለት ነው፡፡ ልክ እንደ ልጅ ራሳቸውን ለመቆጣጠር የማይችሉ ማለት ነው፡፡ ልጅ ግን ምህረት ሊደረግለት ይችላል፡፡ ነገር ግን አንድ ለአቅም አዳም የደረሰ ሰው በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ እያለ ራሱን ለመቆጣጠር ያማይችል ከሆነ ተስፋ የለውም ማለት ነው፡፡ ተስፋ የሌለውም ስለሚሆን ራስን ለመቆጣጠር መቻል አስፈላጊ ነው፡፡ ”ቫቾ ቬጋም ክሮዳ ቬጋም ኡዳራ ቬጋም ኡፓስትሀ ቬጋም“ ከሁሉም በላይ የሆነው ደግሞ ”ኡዳራ ቬጋም እና ጂቫ ቬጋም“ ናቸው፡፡ ”ጂቫ ቬጋም“ ምላስን መቆጣጠር መቻል ማለት ነው፡፡ ብሀክቲቪኖድ ታኩር እንደገለፁልን ”ከስሜቶቻችን ሁሉ“ ”አንዱ ስሜታችን አደገኛ ነው፡፡“ ”ታራ ማድህዬ ጂህቫ አቲ ሎብሀሞይ ሱዱርማቲ ታኬ ጄታ ካትሂና ሳምሳሬ“ ከስሜቶቻችን ሁሉ ምላሳችንን መቆጣጠር አስቸጋሪ ነው፡፡