AM/Prabhupada 0116 - ይህንን ብርቅ እና አስፈላጊ ሕይወታችሁን አታባክኑ፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture with Allen Ginsberg at Ohio State University -- Columbus, May 12, 1969

ነፍስ በእውን አለች:ይህም ገላ ያደገው በዚሁ በነፍሳችን መድረክ ላይ ነው: ይህም ነፍስ ከአንድ ገላ ወደ አንድ ገላ እየተዘዋወረ ይገኛል:ይህም ኢቮልዩሽን ይባላል: ይህም የኢቮልዩሽን ሥርአት በ 8400000 የተለያዩ ፍጥረታት ውስጥ እየተላለፈ ይገኛል: የባህር ፍጥረታት:የወፎች:የአውሬዎች:የተክሎች:እንዲሁም ብዙ ሌሎች ፍጥረታት: አሁን ታድያ እኛ:የዳበረ የሰው ልጅን አንደበት ይዘናል:በትክክልም መጠቀም አለብን: ይህ ነው የእኛ የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ: ህብረተሰቡን በማስተማር ላይ እንገኛለን:ይህንንም በጣም አስፈላጊ የሆነውን:የሰው ልጅን ህይወት አታባክኑ: ይህንንም የሰው ልጅነት እድል ካባከናችሁት:ራስን እንደ መግደል ይቆጠራል: ይህ ነው የእኛ መልእክት:ራሳችሁን አትግደሉ: ይህንን የክርሽናን ንቃት ተከታተሉ:መመሪያ ስርአአቱም በጣም ቀላል ነው: ልክ እንደ ዮጋ ሲስተም እና:እንደ ግምታዊ ፍለስፍና አቀራረብ:ከበድ ያለ ስርአት መከተል አያስፈልጋችሁም: ይህ ከበድ ያለ ስርአት በዚህ ዘመን አዳጋች ነው: የምናገረውን የእራሴ ስሜት ሳይሆን:የታላላቁ መምህራኖቻችንን እና ትላልቅ ባህታውያን:የሰጡንን ልምድ እና ምሳሌን ነው: እንደዚህም ብለውናል:“ካለው ናስት ኤቫ ናስት ኤቫ ናስት ኤቫ ጋቲር አንያትሃሃ” ማንነታችሁን ማወቅ ከፈለጋችሁ:የወደፊት ኑሮአችሁን ማወቅ ከፈለጋችሁ: አምላክ ማን እንደሆነ ማወቅ ከፈለጋችሁ:የእናንተስ ከአምላክ ጋር ያለው ግኑኝነት ምን እንደሆነ:ለማወቅ ከፈለጋችሁ: እነዚህ ነገሮች ሁሉ ሊገለጽላችሁ የሚችለው:ይህንን ማንትራ በመዘመር ነው: ሀሬ ክርሽና: ሀሬ ክርሽና: ክርሽና ክርሽና: ሀሬ ሀሬ: ሀሬ ራማ: ሀሬ ራማ: ራማ ራማ: ሀሬ ሀሬ ይህም ተግባራዊ ነው:የምናስከፍለውም ነገር የለም: የሚስጥር ማንትራ ሰጥቼህ:50 ዶላር አስከፍልሃለሁ እያልንም አንደልልም: ይህ ለሁሉም ክፍት ነው:ውሰዱት:ያ ነው የእኛ መልእክት: ህይወታችሁም እንዳታባክኑት: እየለመንናችሁ ነው: ይህንን ማንትራ ውሰዱ:የፈለጋችሁበትም ቦታ ላይ ዘምሩት: መከተል የሚያስፈልጋችሁም:ምንም አስቸጋሪ ህግጋት የለውም: መቼም ቢሆን:የትም ቢሆን:በምንም ሁኔታ ላይ እያላችሁም ቢሆን: ዘምሩ: ልክ ከግማሽ ሰአት በፊት ዘምረን እንደነበረው: በማንኛውም ሁኔታ እያላችሁ ስትዘምሩ ደስተኛ ትሆናላችሁ:ስለዚህ ቀጥሉበት: ይህን ሀሬ ክርሽና ማንትራ ዘምሩ:የተሰጣችሁም በነፃ ነው: ነገር ግን:የሀሬ ክርሽና ማንትራ ምን እንደሆነ በፍልስፍና ለማወቅ ብትፈልጉ ግን: በእውቀት:እና በሎጂክ:ማወቅ ብትፈልጉም: ለዚህም ብዙ ቮልዩሞች የሚሆኑ መፃህፍቶች አሉን: እንዲያው በስሜታዊ ግፊት ብቻ:ወጥተን የምንዘምር እና የምንደንስ እንዳይመስላችሁ:አይደለም:እኛ መሰረት ያለው የበስተኋላ ምክንያት አለን: እና ይህንን:የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ:በደንብ ለመረዳት ሞክሩ: እኔም አገራችሁ የመጣሁት:ይህንኑ ጥሩ መልእክት ለማስተላለፍ ነው: ምክንያቱም:እናንተ ይህን ብትቀበሉ:ይህንንም የክርሽና ንቃት ሳይንስ በደንብ ተረድታችሁ ብትቀበሉት: የሌላውም አለም ሊከተለው ይችላል:የአለም ገፅም ሊቀየር ይችላል:ይህ የተረጋገጠ ነው: