AM/Prabhupada 0123 - በግድ ለአብዩ ጌታ ልቦና መስጠት ትልቅ በረከት ነው፡፡

Revision as of 06:05, 29 November 2017 by Sahadeva (talk | contribs) (Text replacement - "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->" to "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Lecture-Day after Sri Gaura-Purnima -- Hawaii, March 5, 1969

አገልጋይ፡ በዚህ ዓለም ላይ ውስን ነፍሳት ሰለመሆናችን ክርሽናን በግድ በእርሱ ጥላ ስር እንድንሆን ለመጠየቅ እንችላለንን?

ፕራብሁፓዳ፡ አዎን ይህንን መጠየቅ ትችላላችሁ፡፡ አንዳንድ ግዜም እርሱ እራሱ ሲያስገድደን እናያለን፡፡ አንዳንድ ግዜ ጌታ ክርሽና የእርሱን ጠለላ ከመፈለግ በቀር ሌላ መጠለያ እንዳይኖረን አድርጎ ሲያስገድደን ይታያል፡፡ አዎን ይህ ታድያ ልዩ ምርቃት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ይህ ልዩ በረከት ነው፡፡ የእኔ መንፈሳዊ አባት በመስበክ ላይ እንድሰማራ ፈልጎ ነበር፡፡ እኔ ግን ፈቃደኛ አልነበርኩም፡፡ ቢሆንም ግን በመስበክ እንድሰማራ አስገድዶኝ ነበር፡፡ አዎን ይህንንም እኔ በተግባር ያየሁት ነው፡፡ እኔ መነኩሴ ሆኖ በመሰበክ ላይ ለመሰማራት ምንም ሀሳቡ እና ፍላጎቱም አልነበረኝም፡፡ ቢሆንም ግን የመንፈስ አባቴ ፍላጎቱ ይኀው ነበር፡፡ ምንም ዝንባሌ አለነበረኝም ነገር ግን እርሱ አስገድዶኝ ነበር፡፡ ይህም በተግባር ላይ ዋለ፡፡ ይህ ልዩ በረከት ነው፡፡ በዚያን ግዜ ግን ሲያስገንደኝ እንዲህ በማለት አስብ ነበር፡፡ "ይህ ምንድን ነው? ምን መጣብኝ?" የፈፀምኩት ስህተት አለ ወይንስ ምንድን ነው? ግራም ተጋብቼ ነበር፡፡ ከጥቂት ግዜ በኃላ ግን ይህ ለእኔ ትልቅ በረከት እንደመሆኑ ለመረዳት በቅቻለሁ፡፡ አያችሁን? ክርሽና አንድ ሰው ሙሉ ልቦናውን እንዲሰጥ ሲያስገድደው ይህ በረከት እንደሆነ መረዳት ይገባናል፡፡ ነገር ግን በአጠቃላይ ይህንን ሲያደርግ አይታይም፡፡ ነገር ግን ክርሽና ትሁት ልቦና የሚሰጠው አገልጋዩን ሲያስገድደው እናያለን፡፡ ይህም የተረፈ የዓለማዊ የደስታ ፍላጎት በስሜቱ ውስጥ ስለሚገኝ ነው፡፡ በዚህም ግዜ ሲያስገድደን ይታያል፡፡ ይህም ሞኝ ሰው የማይረዳው ነገር ቢኖር የዚህ የቁሳዊው ዓለም ተፈጥሮ ምንም ዓይነት ደስታ እንደማይሰጠው ነው፡፡ ይህም በዚህ ደረጃ እያለ በትሁትነት የእኔን በረከት ይፈልጋል፡፡ ይህ ሞኝነት ነው፡፡ ሰለዚህም ምንም ዓይነት የቁሳዊ ዓለም ሀብት ወይም ቁሳቁስ ቢኖረው እኔ እሰብረለታለሁ፡፡ በዚህም ግዜ ሌላ አማራጭ ሰለማይኖረው ወደ እኔ ሙሉ ልቦናውን ለመስጠት ይዘጋጃል፡፡ ይህም በብሀገቨድ ጊታ እና በሽሪማድ ብሀገቨታም ተገልጿል፡፡ ”ያስያሀም አኑግርህናሚ ሃሪስዬ ታድ ድሀናም ሳኔይህ“ ክርሽና እንዲህ ብሏል “ለአንድ ሰው ምርቃቴን ለመስጠት ሰፈልግ” “በድህነት የተሞላ እንዲሆን አደረገዋለሁ” “በቁሳዊ ዓለም የስሜታዊ ደስታ የሚያገኝበትን መንገዶች ሁሉ እዘጋበታለሁ” አያችሁ? ይህም በሽሪማድ ብሀገቨታም ውስጥ ተጠቅሶ ይገኛል፡፡ ምክንያቱም በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ መላው ህብረተሰብ ገንዘብን በማሳደድ ንግድ በማቋቋም አገልግሎት በመስጠት ደስታ የሚያገኙበትን መንገድ ሲሹ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ግዜ ክርሽና ይህንን ዓይነት ንግድ ወይንም አገልግሎት እንዲደናቀፍ ያደርግበታል፡፡ ይህንን ትወዱታላችሁን? (ሳቅ) በዚህም ግዜ ይህ ሰው ለክርሽና ሙሉ ልቦናውን በመስጠት ክርሽናን መጠለያ ከማድረግ በላይ ሌላ እቅድ ሊኖረው አይችልም፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ግዜ ንግዳችን እየሰመረልን ካልመጣ ወይንም የገቢያችን ምንጭ ሲደናቀፍ በዚህ ማዘን እንጀምራለን፡፡ “ክርሽና በእኔ ሰለጨከነብኝ ይህ ሊሳካልኝ አልቻለም” ነገር ግን ይህ ከእርሱ የመጣ በረከት መሆኑን መረዳት ይገባናል፡፡ ይህም ልዩ የሆነ ምርቃት ነው፡፡ በዚህ መንገድ ይህንን መረዳት ይገባናል፡፡