AM/Prabhupada 0147 - ተራ የሆነ ሩዝ ታላቁ ወይንም አብዩ ሩዝ ተብሎ ሊጠራ አይችልም፡፡



Lecture on BG 7.1 -- Hong Kong, January 25, 1975

ድቮቲዎች ፈጣሪ እንዳለ ያውቃሉ:እርሱም “ብሃገቫን” ነው: ፈጣሪ ብሃገቫን ይባላል: ብሃገቨድ ጊታ የተነገረውም በክርሽና ነው:ሁሉም ሰው ያውቃል: በብሃገቨድ ጊታም:በአንዳንድ ቦታ: "ብሃገቫን ኡቫቻ“ ተብሎ ተጠቅሷል: ብሃገቫን እና ክርሽና አንድ ሰው ነው:”ክርሽናቱ ብሃገቫን ስቫያም“ (ሽብ 1 3 28) ብሃገቫን:የዚህም የብሃገቫን ቃል ዝርዝር ተሰጥቷል:

”አይሽቫርያስያ ሳማግራስያ ቪራያስያ ያሻሳህ ሽሪያህግናና ቫይራግያዮሽ ቻይቫ ሳናም ብሃጋ ኢቲንጋና“ (ቪሽኑ ፑራና 6 5 47)

ብሃጋ:ከብሃግያቫን ቃልም ”ብሃግያን“ እንረዳለን: ብሃግያ:ብሃግያቫን:ይህ ቃል ከብሃጋ የመጣ ነው:ብሃጋ ማለትም ሀብት ማለት ነው: ሃብት ማለትም ብዙ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ማለት ነው:አንድ ሰው እንዴት ነው ሀብታም ተብሎ ሊጠራው የሚችለው? ገንዘብ ካለው:አእምሮ ካለው:ቁንጅና ካለው: ዝና ካለው:እውቀት ካለው:ስግብግብነት ከሌለው:ይህ ነው ብሃገቫን የሚባለው: እዚህም ብሃገቫን ስንል:ብሃገቫን ”ፓራም ኢሽቫራ“ ነው: ሁለት ሁለት አይነት ቃላቶች አሉ:”ኢሽቫራ እና ፓራምኢሽቫራ“ ”አትማ እና ፓራምአትማ“ ”ብራህማን እና ፓራ ብራህማን“ የመጀመሪያው ተራ ሲሆን የሚቀጥለው ደግሞ አብይ ነው: ለምሳሌ:ምግብ ስናዘጋጅ:የተለያየ ሩዝ ማዘጋጀት እንችላለን: ሩዝ ይኖራል:የተለያዩ የሩዝ አይነቶችም ይኖራሉ:አና: ፓራማና:ፑሽፓና:ኪቾራና:እንደሚባሉት: አብዩ አና:ፓራማና ይባላል:ፓራማ ማለት አብይ ወይንም ታላቅ ማለት ነው: አና ሩዝ አለ:ነገር ግን አብይ ሆነ ማለት ነው: የሩዝ ብትን: አብይ አይባልም:ሩዝ ብቻ ይሆናል: ሩዝን ክሲራ ጋር ስታዘጋጁት ግን:ይህም ከወተት ጋር እና ከሌላ ጥሩ ነገሮች ጋር:ይህም “ፓራማና” ይባላል: እንደዚሁም ሁሉ:የነፍስ እና የብሃገቫን ብህርዮች አንድ ናቸው: ብሃገቫን ገላ አለው:እኛም ገላ አለን: ብሃገቫን ነዋሪ ነው እኛም ነዋሪዎች ነን: ብሃገቫን የመፍጠር ችሎታ አለው:እኛም የመፍጠር ችሎታ አለን: ልዩነታችን ግን:እርሱ በጣም አብይ ነው:”ኤኮ ባሁናም ቪዳድሃቲ ካማን“ ብሃገቫን ይህንን ሁሉ ዩኒቨርስ ለመፍጠር ሲፈልግ:ከማንም እርዳታ አይፈልግም: ሰማይን ይፈጥራል:ከሰማይም ቀጥሎ ድምጽን ይፈጥራል: ከድምጽ ቀጥሎ አየር:ከአየር ቀጥሎ እሳት: ከእሳት ቀጥሎ ውሃ:ከውሃ ቀጥሎ ደግሞ አፈር አለ: