AM/Prabhupada 0175 - ድሀርማ ማለት ቀስ በቀስ ቁራዎችን ወደ ዝይ ወይንም ስዋን መቀየር ማለት ነው፡፡



Lecture on SB 1.8.33 -- Los Angeles, April 25, 1972

ማንኛውም ስነጽሁፍ:ከአምላክ ጋር ያልተገናኘ ከሆነ:“ታድ ታድ ቫያስያም ቲርትሃም” ይህም የሚታየው ልክ እንደ ቁራዎች እንደሚደሰቱበት ቦታ ነው: ቁራዎች የሚደሰቱበት ቦታ የት ነው? ይህም በቁሻሻ ቦታ ነው: ነጭ ስዋኖች ደግሞ የሚደሰቱበት በጠራ ውሃ:አትክልትና እና ወፎች ባሉበት አካባቢ ነው: እንደዚሁም ሁሉ በእንስሳዎች ደረጃ እንኳን ልዩነት አለ: የስዋን ደረጃ እና የቁራ ደረጃ:የተፈጥሮ ክፍልፍል አለው: ስዋን ወደ ቁራ አይሄድም:ቁራም ደግሞ ወደ ስዋን ቦታ አትሄድም: በሰው ፍጥረትም ደግሞ እንደ ስዋን ደረጃ ያሉ እና እንደ ቁራ ደረጃ ያሉ ሰዎች አሉ: የስዋን ደራጃ ያሉ ወደ እዚህ ይመጣሉ:ምክንያቱም ሁሉም ነገር ንጽህና ያለው ነው: ጥሩ:ፍልስፍና:ምግብ:ትምህርት:ልብስ:አስተሳሰብ: ሁሉም ጥሩ ሁኖ ይገኛል: የቁራ ደረጃ ሰዎች:ክለብ:ፓርቲ:የራቁት ዳንስ የመሳሰሉት ቦታዎች ለመሄድ ይመርጣሉ: ይህ የክርሽና ንቃተ ማህበር ግን የተቋቋመው እንደ ስዋን ደረጃ ላሉ ሰዎች ነው: ለቁራ ደረጃ ለሆኑ ሰዎች አይሆንም: ነገር ግን:እንደ ቁራ የሆኑትን ሰዎች:ወደ ስዋንነት መቀየር እንችላለን:ይህ ነው የእኛ ፍልስፍና: ቁራ የነበረው እንደ ስዋን እንዲዋኝ እናደርገዋለን: ይህ ነው የክርሽና ንቃት: ስዋኖች እንደ ቁራ ሲሆኑ:ይህም የአለማዊ ኑሮ ነው: ክርሽናም እንዲህ ብሏል:“ያዳ ያዳ ሂ ዳሃርማስያ ግላኒር ብሃቫቲ (ብጊ4 7) ህያው ነፍስ በዚህ ገላ ውስት ተጠምዶ:ስሜቱን ለማርካት ይጥራል: በየአዲስ ህይወቱም የገላ ገላ እየቀያየረ ይገኛል:ይህ ነው ሁኔታው: ድሃርማ ማለት ደግሞ ቁራዎችን ወደ ስዋን መመለስ ማለት ነው:ይህ ድሃርማ ነው: ልክ አንድ ሰው:ያልተማረ:ባህል የሌለው:ሊሆን ይችላል:ነገር ግን ወደ ተማረ እና ባህላዊ ሰው ለመቀየር ይችላል: ይህም በትምህርት እና:በልምምድ ነው:ስለዚህ ይህም እድል ለሰው ህይወት አለ: ውሻን ድቮቲ ለማድረግ ማስተማር አልችልም: ሊደረግም ይቻላል:ግን እኔ ለዚህ ሃይል የለኝም:ይህም በቼይታንያ ማሃብራብሁ ተደርጓል: አንድ ግዜም ጃሪካንድ በሚባል ጯካ ያልፍ ነበር:እዚህም ነብሮቹን:እባቦቹን:አጋዘኖቹን:እና የተለያዩትን እንስሶች:ደቮቲ አደረጋቸው: እንደዚህም ይህ በቼይታንያ ማሃብራብሁ ተችሎ ነበረ:ምክንያቱም እርሱ አምላክ ነው:የፈለገውንም ማድረግ ይችላል:እኛ ይህን ማድረግ አንችልም: ቢሆንም ግን እኛ በሰው ልጅ ህብረተሰብ ውስጥ መስራት እንችላለን:ምንም እንኳን የሰው ልጅ የወደቀ ቢሆንም: የእኛን ትእዛዝ ከተከተለ:መቀየር ይችላል: ይህ ድሃርማ ይባላል:ድሃርማ ማለት አንድን ወደ ነበረበት መንፈሳዊ ደረጃ መመለስ ማለት ነው: ያም ድሃርማ ነው:የተለያየ ዲግሪ ሊኖረው ይችላል: የነበርንበት ደረጃ እኛ የአምላክ መንፈዋዊ ወገን እና ፍንጥቃዊ ነን: ይህንንም ስንረዳ:እኛ የአማላክ ወገን እና ፍንጥቃዊ:ያ የእኛ ትክክለኛ ስፍራችን ነው: ይህም ብራህማ ብሁታ ይባላል:(ሽብ4 30 20) የብራህማን ደራጃችንን ለይተን ማወቅ እና መገንዘብ ማለት ነው: