AM/Prabhupada 0188 - የመላ ሕይወት ችግሮች ሁሉ የበላይ መፍትሄ፡፡



Lecture on SB 2.3.17 -- Los Angeles, July 12, 1969

ቪሽኑጃን:ፕራብሁፓድ:አምላክ ኦሪጂናሉ ፈጣሪ እና መነሻ እንደሆነ ተናግረሃል: ሆኖም እያለ:ሰዎች ይህን ፈጣሪ ማን እንደሆነ ሳያውቁ:እንዴት ብለው ነው ማን እንደሚቆጣጠራቸው ሊረዱት የሚችሉት: ማንም ሰው ክርሽናን ስለማያውቅ እና እርሱ የፍጥረት ሁሉ መነሻ መሆኑን ስለማያውቁ: እንዴት ብለው ነው የሚቆጣጠራቸው እንዳለ ማወቅ የሚችሉት? በክርሽና ሁሉም ነገር እንደሚከናወን:እንዴት ነው ለማወቅ የሚችሉት? ፕራብሁፓድ:አነተ በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዳለህ የምታውቀው እንዴት ነው?እንዴት ታውቃለህ? ቪሽኑጃን:መንግስት ህግጋቶች አላቸው:ፕራብሁፓዳ:እኛም ህግጋቶች አሉን: “አናዲ ባሂርሙክሃ ጂቫ ክርሽና ብሁሊ ጌላ አቴቫ ክርሽና ቬዳ ፑራኔ ካሪላ” ክርሽናን ስለረሳኅው:ክርሽና ብዙ የቬዲክ መፃህፍቶችን ትቶልሃል: ስለዚህም ብዙ ግዜ ስሜት የማይሰጥን ስነጽሁፎች በማንበብ ግዜያችሁን አታባክኑ እላለሁ አእምሮአችሁን ወደ ቬዲክ መፃህፍት ማድረግ አለባችሁ:ከዚያም ልትረዱ ትችላላችሁ: ለምንድን ነው እነዚህ መጽሃፍቶች የቀረቡት? ህጋዊ መሆን እንዳለብን ለማስታዋስ ነው: ነገር ግን እነዚህን የማንጠቀም ከሆነ ግን:ህይወታችንን እናባክናለን: ይህ ስብከት የምናደርገው:መፃህፍቶች የምናትመው:ስነጽሁፎች:መጋዚኖች:የክርሽና ንቃተ ማህበራችን: ይህ ሁሉ እንዴት በአምላክ ቁጥጥር ስር እንዳለን የሚያስታውሰን ነው:ማነው አብይ ተቆጣጣሪው? እንዴት ህይወታችን ለመበልፀግ ይችላል?ከዚህ አለም ቁጥጥርስ እንዴት መውጣት እንችላለን? እንዴት ነጻነት ያለው ኑሮ መያዝ እንችላለን?ይህ ነው የእኛ እንቅስቃሴ: የዚህም የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴያችን ለዚሁ አላማ ነው:አለበለዛ የዚህ እንቅስቃሴ አላማው ምንድን ነው: ሌላ “ኢዝም” ለጊዜው ሰውን ለማስደነቅ የተፈጠረ አይደለም: ይህ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴያችን:የህይወት ችግሮች ሁሉ:መፍትሄ ነው: ይህ መዘመርም:መልእክቱን የምናገኝበት የልባችን ጎዳና ነው: “ቼቶ ዳርፓና ማርጃናም” (ቼቻ አንትያ 20 12) ልባችንን ማጠብ ማለት ነው: ከዚያም ይህ መልእክት ሊደርሳችሁ ይችላል: የእኛ ስርአትም ሳይንቲፊክ ነው:ስልጣን ያለውም ነው:ይህንን ስርአት የሚከተልም ሁሉ:ቀስ በቀስ ሊረዳ ይችላል:ከዚያም ከፍተኛ ደራጃ ላይ ሊደርስ ይችላል: ይህ ጥርጣሬ የለውም: