AM/Prabhupada 0199 - እነዚህ ተንኮለኛ አስተያተት ሰጪዎች ክርሽናን ለማራቅ ይሞክራሉ፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on BG 13.8-12 -- Bombay, September 30, 1973

እውቀት ፊሎሶፊ ከሌለው ስሜታዊ ነው: ፊሎሶፊ ደግሞ:የሃይማኖታዊ አቀራረብ ከሌለው የአእምሮ ግምት ሁኖ ይቀራል: እነዚህ ሁለቱ ሳይያያዙ በአለም ላይ እየተካሄዱ ነው: ብዙ የሃይማኖት ድርጅቶች አሉ:ነገርግን ፍልስፍና የላቸውም: ስለዚህ እነዚህ የሃይማኖት ድርጅቶች: ለአሁኑ ለተማረው ሰው የሚስቡ አይደሉም: ክርስቲያን:እስላም: ሂንዱ ቢሆኑም መከተል እያቆሙ ነው: እነዚህም ሰዎች የሃይማኖት ፎርማሊቲ:ስርአቶችን ብቻ አይፈልጉም: በፍልስፍና አንፃር ሁሉንም ነገር ማወቅ ይፈልጋሉ: ይህም ብሃገቨድ ጊታ ነው:ብሃገቨድ ጊታ በክርሽና ብሃክቲ የተመሰረተ ፍልስፍና ነው: ብሃገቨድ ጊታ ማለት:ክርሽና ብሃክቲ:የፍቅር መንፈሳዊ አገልግሎት:የክርሽና ንቃት ማለት ነው:ይህ ብሃገቨድ ጊታ ነው: የብሃገቨድ ጊታ ትምህርትም:“ማን ማና ብሃቫ ማድ ብሃክቶ ማድ ያጂ ማም ናማስኩሩ:(ብጊ 18 65) ይህ ብሃገቨድ ጊታ ነው:”ሁልግዜ አስታውሰኝ“ ክርሽና ንቃት ንፁህ እና ቀላል ነው: ”ማን ማና ብሃቫ ማድ ብሃክቶ ማድ ያጂ ማም ናማስኩሩ (ብጊ18 65) በሁሉም ቦታ ላይ: ክርሽና ስለ እርሱ አንደበት: በደንብ ገልጾልናል: “አሀም አዲር ሂ ዴቫናም (ብጊ 10 2) ”እኔ የመላእክቶች ሁሉ መነሻ ነኝ“ ”ማታህ ፓራታራም ናንያት ኪንቺድ አስቲ ድሃናንጃያ" (ብጊ 7 7) "አሀም ሳርቫስያ ፕራብሃቮ ማታህ ሳርቫም ፕራቫርታቴ ኢቲ ማትቫ ብሃጃንቴ ማም ቡድሃ ብሃቫ ሳማንቪታሃ" (BG 10.8)(ብጊ 10 8) ሁሉም ነገር ተሰጥቷል: ”ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጅያ ማም ኤካም (ብጊ 18 66) ማም አሃም “እኔ” ማለት ነው: እንደዚሁም ሁሉ በእያንዳንዱ ምእራፍ:በእያንዳንዱ ጥቅስ:ክርሽና “እኔ” ብሎ ተናግሯል “ማዪ አሳክታ ማናህ ፓርትሃ ዮጋም ዩንጃን ማድ አሽራያሃ” “ማያ አሳክታ ማለት “ለእኔ በጣም ቅርበት ያለው ማለት ነው” አሳክታ ማናህ “አእምሮው ከእኔ የማይለይ”:ይህም ዮጋ ማለት ነው: “ዮጊናም አፒ ሳርቬሻም ማድ ጋቴናንታራትማና:ማድ ጋታ” እንደገና “ማት” ተጠቅሷል:(ብጊ 6 47) ”ማድ ጋተናንታራትማና ሽራድሃቫን ብሃጃቴ ዮ ማም ሳ ሜ ዩክታታሞ ማታሃ“ ስለዚህ ሁሉም ነገር:ተተኩሮበታል:ክርሽና:ነገር ግን እነዚህ ተንኮለኛ ገለጻ ሰጪዎች ክርሽናን እየቀነሱ ይገኛሉ: ይህም ተንኮለኛነት:በህንድ አገር ብዙ ችግር አምጥቶአል: እነዚህ ተንኮለኛ:ገለጻ ሰጪዎች:ክርሽናን ለማስወገድ ይፈልጋሉ: ስለዚህም ይህ የእኛ የክርሽና እንቅስቃሴ ማህበር የተቋቋመው እነዚህን ተንኮለኞች ለመቋቋም ነው: ይህ መቋቋም ነው:“ክርሽናን ያለ ክርሽና መፍጠር ትችላላሁን? ይህ ስሜት አይሰጥም”