AM/Prabhupada 0201 - ሞትን እንዴት ለማቆም እንደሚቻል፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on CC Madhya-lila 20.102 -- Baltimore, July 7, 1976

ሁላችንም እውቀትን እየፈለግን ነው:ነገር ግን ብዙ ያልተገለጹልን ነገሮች አሉ: ስለዚህም ሳናታን ጎስዋሚ:እንዴት መንፈዋዊ አባትን መቅረብ እንደሚገባን:በተግባራዊ አርአያው አሰተምሮናል: ለማስተማር ብሎም:“እንደዚህ እየተሰቃየሁ እገኛለሁ”:እያለ:በውዴታ አርአያው አሳይቶናል ሚንስተርም ነበረ:ምንም ስቃይም የነበረው ሰው አልነበረም:በተመቸ ሁኔታ ላይም የነበረ ሰው ነበረ: ይህንንም አስረድቶናል:“ግራምያ ቭያቫሃሬ ፓንዲታ ታይ ሳትያ ካሪ ማኒ” “ብዙ ጥያቄዎች እኔ ልመልሳቸው የማልችል አሉ:መፍትሄም አላገኘሁም” “ነገርግን ሰዎች የተማርህ ነህ ይሉኛል:እኔም በሞኝነት እቀበለዋለሁ” ማንም ሰው ወደ ጉሩ ካልሄደ:የተማረ ሰው ሊሆን አይችልም: “ታድቪግናናርትሃም ሳ ጉሩም ኤቫ ብሂጋቼት” (ሙኡ1 2 12) ስለዚህም የቬዲክ መመሪያዎች:የሚገልጹልን:መማር ከፈለግን ወደ ስልጣን ያለው ጉሩ መሄድ አለብን:አስመሳይ ጉሩ ሳይሆን ማለት ነው: “ታድ ቪድሂ ፕራኒፓቴታ ፓሪፕራሽኔና ሴቫያ ኡፓዴክሽያንቲ ቴ ግያናም ግያኒናስ ታትቫ ዳርሺናሃ” (ብጊ 4 34) ጉሩ ማለት ፍጹም የሆነውን እውነት ያየ ማለት ነው:ይህ ነው ጉሩ ማለት: “ታትቫ ዳርሺና” ታትቫ ማለት ፍጹም የሆነ እውነት ማለት ነው:ዳርሺና ማለት ደግሞ በውን ያየ ማለት ነው: ይህ የእኛ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ:የተቋቋመው ለዚህ አላማ ነው:ፍጹም የሆነ እውነትን ለማሳየት: ፍጹም የሆነ እውነትን ለመረዳት:የህይወትን ችግሮች ለማወቅ እና መፍትሄዎችን ለመፍጠር ነው: እነዚህ የእኛ ርእሶች ናቸው: የእኛ ርእሶች ስለ አለማዊ ነገር አይደለም: የኛ መልእክት:ስለ:መኪና አግኝቶ: አፓርትመንት ይዞ:ጥሩ ሚስት ይዞ:ሁሉም ችግራችሁ ይፈታል ማለት አይደለም: ይህ የህይወት ችግሮች መፍትሄ አይደለም:ዋናው ችግር ሞትን ማቆም ነው:ያ ዋናው ችግር ነው: ነገር ግን ይህ አስቸጋሪ ርእስ ስለሆነ:ማንም ሰው አይነካውም: “ሞት:በሰላም እንሞታለን” ነገር ግን ማንም ሰው በሰላም አይሞትም: አንድ ጩቤ አንስቼ “አሁን በሰላም ሙት” ብል:(ሳቅ)ምንም የሰላም ሞት አይኖረውም:ለቅሶውን የቀጥላል: እና ይህ ሰሜት የማይሰጥ መልስ ነው:አንዱ እንዲህ ቢል “በሰላም እሞታለሁ” ማንም በሰላም አይሞትም:ይህ አይቻልም: ስለዚህ ሞት ችግር ነው:ትውልድም ችግር ነው: በእናት ሆድ እያለ:ማንም ሰላም የለውም: “ገላው የተጠቀለለ ነው:አየር ያነሰበት ሁኔታ:አሁን አሁን በእናትም የመገደል አደጋ አለው” እንደዚሁም ሁሉ:የሞት እና የትውልድ ሁኔታ ሰላም የሚባል ነገር የለውም: ከዚያ ደግሞ እርጅና:ልክ እንደ እኔ በዚህ እድሜዬ:ብዙ ችግር አይቻለሁ: ስለዚህ እርጅና እና ህመም:ሁሉም ልምድ አለው:ትንሿ ራስ ምታት እንኳን ችግር ለመስጠት ትበቃናለች: ስለዚህ ዋናው ችግራችን:መወለድ:መሞት:ማርጀች:እና መታመም ነው: ይህ ቃልም በክርሽና ተጠቅሷል:“ጃንማ ምርትዩ ጃራ ቭያድሂ ዱክሃ ዶሻኑ ዳርሻናም (ብጊ 13 9) አስተዋይ ሰው ከሆናችሁም:እነዚህን አራት የህይወት ችግሮች እንደ አደገኛ አድርጋችሁ መውሰድ አለባችሁ: ሰለዚህም ችግሮች መፍትሄ የላቸውም:ስለዚህ ይርቋቸዋል:እኛ ግን እነዚህን ጥያቄዎች በጣም አጥብቀን እንከታተላቸዋለን: ይህ ነው የእኛ እና የሌሎች እንቅስቃሴዎች: የኛ እንቅስቃሴ:እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ተቋቁሟል: