AM/Prabhupada 0216 - ክርሽና በአንደኛ ደረጃ የሚታይ ነው፡፡ ትሁት አገልጋዮቹም በአንደኛ ደረጃ የሚታዩ ናቸው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on SB 1.7.47-48 -- Vrndavana, October 6, 1976

የቫይሽናቫ ባህርይ ማለት ይህ ነው፡፡ “ፓራ ዱክሃ ዱክሂ” ቫይሽናቫ “ፓራ ዱክሀ ዱክሂ” ነው፡፡ ይህ የቫይሽናቫ ባህርይ መለክያ ነው፡፡ ሰለ እራሱ መከራ ግድ አይሰጠውም፡፡ ነገር ግን ቫይሽናቫ የሌሎችን ጭንቀት እና መከራ ሲያይ እራሱ በጣም የጠለቀ ጭንቀት ውስጥ ይገባል፡፡ የቫይሽናቫ ባህርይ ይኅው ነው፡፡ ፕራህላድ መሀራጅም እንዲህ ብሎ ነበር፡፡ “ናይቮድቪጄ ፓራ ዱራትያያ ቫይታራንያስ ትቫድ ቪርያ ጋያና ማሃምርታ ማግና ቺታሀ” “ሾቼ ታቶ ቪሙክታ ቼታሳ ኢንድሪያርትሀ ማያ ሱክሀያ ብሀራም ኡድቫሀቶ ቪሙድሀን” (ሽብ፡ 7 9 43) ፕራህላድ መሀራጅ በአባቱ በጣም ተጎሳቁሎ ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን አባቱ ለመገደል በቃ፡፡ እንደዚህም ተጎሳቁሎ በአብዩ ጌታ ናራሺንግሀ ዴቫ የፈለገውን እንዲቀርብለት ቢጠየቅም ምንም ነገር ለግሉ ለመቀበል ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ “ሳ ቫይ ቫኒክ” ብሎም መለሰ፡፡ ጌታዬ ሆይ የተወለድነው የቅብዝብዝ (ራጃ ጉና) እና የድንቁርና (ታሞ ጉና) ባህርይ ይዘን ነው፡፡ ራጃ ጉና እና ታሞ ጉና፡፡ እነዚህ አሱራዎች (ሰይጣናውያን) በዝቅተኛው የራጃ ጉና እና የታሞ ጉና ባህርዮች የተጠቁ ናቸው፡፡ (ቅብዝብዝነት እና ድንቁርና) እነዚያ ዴቫታ (መንፈሳውያን) ደግሞ በሳትቫ ጉና ወይንም በጥሩ መንፈስ የታደሉ ናቸው፡፡ በዚህ ምድር ላይ ሶስት ዓይነት ባህርዮች አሉ፡፡ “ሳትቫ ጉና” “ትራይ ጉናማዪ ዳይቪሂ ኤሻ ጉና ማዪ” (ብጊ፡7 14) በዚህ ቁሳዊ ዓለም ላይ እነዚህ ሶስቱ ባህርዮች ይገኛሉ፡፡ ሳትቫ ጉና ራጆ ጉና እና ታሞ ጉና፡፡ በሳትቫ ጉና (ጥሩ ባህርይ)የተመረቁት አንደኛ ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ አንደኛ ደረጃ ማለትም አንደኛ ደረጃ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ላይ ማለት ነው፡፡ በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ አይደለም፡፡ መንፈሳዊ ዓለም የተለየ ነው፡፡ መንፈሳዊ ዓለም “ኒርጉና” ይባላል፡፡ ምንም ዓይነት የቁሳዊ ዓለም ባህርይ አይገኝበትም፡፡ በመንፈሳዊ ዓለም አንደኛ ደረጃ ሁለተኛ ደረጃ ሶስተኛ ደረጃ የሚባል ነገር የለም፡፡ ሁሉም ዓንደኛ ደረጃ ላይ ነው፡፡ ይህም ፍፁም የሆነ ደረጃ ነው፡፡ ክርሽና አንደኛ ደረጃ ላይ ነው፡፡ አገልጋዮቹም አንደኛ ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ ዛፎቹም አንደኛ ደረጃ ላይ ወፎቹም አንደኛ ደረጃ ላሞቹም አንደኛ ደረጃ ጥጃዎቹም አንደኛ ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ ሰለዚህም ይህ ዓለም ፍፁም ጥሩ የሆነ ነው እንላለን፡፡ ተወዳዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ሶስተኛ ደረጃ አራተኛ ደረጃ ብሎ ነገር የለም፡፡ ሁሉም ነገር አንደኛ ደረጃ ላይ ነው፡፡ “አናንዳ ቺንማያ ራሳ ፕራቲብሀ ቪታብሂህ” (ብሰ፡ 5 37) ሁሉም ነገር የተመሰረተው በአናንዳ ቺንማያ ራሳ ነው፡፡ ክፍፍልነት ወይንም የደረጃ ልዩነት የለም፡፡ ምንም እንኳን አንዱ በ ዳስያ ራሳ (በማገለገል) ደረጃ ቢገኝም ወይንም በሳክያ ራሳ (በጓደኝነት) ደረጃ ክርሽናን የሚቀርብ ቢሆንም ወይንም ቫትሳልያ ራሳ (በወላጅነት) ወይንም በማድሁርያ ራሳ (በፍቅረኝነት) እንኳን ክርሽናን ቢቀርቡም ሁሉም በአንደኝነት ደረጃ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ በእያንዳንዳቸው የደረጃ ልዩነት የለም ቢሆንም ግን የተለያየ ዓይነት አገልግሎት አለ፡፡ እኔ ይህንን አይነት ግኑኝነት አንተ ደግሞ ያንን ዓይነት ግኑኝነት ከክርሽና ጋር ትፈልግ ይሆናል፡፡ ይህ የተፈቀደ ነው፡፡ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ ሰዎች በሶስቱ ባህርዮች የተጠቁ ናቸው፡፡ ፕራህላድ ማሀራጅም የሂራንያካሺፑ ሰይጣናዊ ሰው ልጅ እንደመሆኑ እራሱን በቅብዝብዝ መንፈስ እና በድንቁርና ባህርይ እንደተሞላ አድርጎ ያሰብ ነበር፡፡ ነገር ግን እርሱ ቫይሽናቫ ነበረ፡፡ እርሱ ከዓላማዊ ባህርዮች ሁሉ በላይ ነበረ፡፡ ቢሆንም ግን ቫይሽናቫ በጥሩ መንፈሱ የኮራ ሆኖ አይገኝም፡፡ እንዲያውም ጥሩ መንፈስ ያለኝ ሰው ነኝ ብሎም አያስብም፡፡ በመንፈሴ የበለፀግሁ ነኝ ህልውናዬ የዳበረ ነው እያለም አያስብም፡፡ ሁሌ የሚያስበው ግን “እኔ ከሁሉም በታች ነኝ“ በማለት ነው፡፡ ”ትርናድ አፒ ሱኒቼና ታሮር አፒ ሳሂሽኑና አማኔና ማናዴና ኪርታኒያህ ሳዳ ሃሪህ“ (ቼቻ፡ አዲ 17 31) ይህ ነው ቫይሽናቫ ማለት፡፡