AM/Prabhupada 0230 - በቬዲክ የባህል ስርዓት ሕብረተሰብ በአራት የተከፈለ ነው፡፡

Revision as of 13:01, 8 June 2018 by Vanibot (talk | contribs) (Vanibot #0019: LinkReviser - Revised links and redirected them to the de facto address when redirect exists)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Lecture on BG 2.1-5 -- Germany, June 16, 1974

ይህ በኩሩክሼትራ ጦርነት ግዜ የነበረው የአርጁና እና የክርሽና ውይይት ነው፡፡ ምንም እንኳን ጦርነቱ እንዲጀመር ቢታወጅም የውይይታቸው ርዕስ እንዲህ ነበረ፡፡ አርጁናም እንዲህ እያለ እያሰበ “በዚያ ወገን ያሉት ሁሉ ዘመዶቼ ናቸው” እንዴት አድርጎ ጦርነቱን በመጀመር ሊገላቸው ይዘጋጅ? ክርሽናም እንዲህ መከረው “ሁሉም ጦረኛ ሀላፊነቱን መወጣት አለበት” “ ይህም የግላቸውን ጥቅም እና ማጣትን ሳያሰላስሉ ነው፡፡ ” በቬዲክ ስልጣኔ እና ባህል አራት አይነቶች የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ፡፡ ይህንንም በመላው ዓለም ህብረተሰቡ ተከፋፍሎ እናየዋለን፡፡ ይህም በተፈጥሮ ያለ ነው፡፡ ለምሳሌ በገላችን እንደምናየው ራስ አለ እጅ አለ ሆድ አለ እንዲሁም እግር አለ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በሕብረተሰብም ውስጥ እንደ መሪ ተብለው የሚታዩ ጭንቅላት ያላቸው ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ሌላው ዓይነት ህብረተሰብ ደግሞ ህብረተሰቡን ከአደጋ የሚጠብቁ ናቸው፡፡ ሌላው ሕብረተሰብ ደግሞ ህዝቡን ለመመገብ ግብርናን እና ምግብን የሚያቀርቡ ናቸው፡፡ እንደዚሁም ላሞችን የሚጠብቁ እና ንግድን የሚያከናውኑ ናቸው፡፡ ሌሎቹ ሰዎች ደግሞ በአዋቂነት ሊሰሩ የማይችሉ ወይንም ሕብረተሰቡን ከአደጋ ለመከላከል ያማይችሉ ወይንም ደግሞ በግብርና ከብት በማርባት እና በግብርና ሊሰማሩ የማይችሉ ሁሉ ሱድራ ተብለው ይታወቃሉ፡፡ ገላችንንም ሙሉ ለማድረግ እነዚህ ሁሉ አስፈላጊ እና ልናስወግዳቸው የማንችላቸው ናቸው፡፡ ገላንም ሙሉ ለማድረግ ጭንቅላት እጅ እንዲሁም ሆድ እና የምንራመድበት ወይንም የምንሰራበት እግር ያሰፈልገናል፡፡ አርጁና የመጣበት ቤተሰብ ህብረተሰቡን መጠበቅ እና መከላከል ከሚገባቸው የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ ሰለዚህም ለመዋጋት ጥርጥር ላይ እያለ አርጁና ለውጊያ አሻፈረኝ ማለት ሲጀምር በዚያን ግዜ ክርሽና ይህንን ምክር ሰጠው “መዋጋት ሀላፊነትህ ነው” በአጠቃላይ መዋጋት እና መግደል የሚደገፍ አይደለም፡፡ ነገር ግን ጠላት ሲኖር እና ጉልበተኛ ሲያጠቃ በዚያን ግዜ ይህንን ዓይነት ያለ አግባብ የሚመጣን ጠላት መግደል ለሀጥያት አያጋልጥም፡፡ በኩሩክሼትራም ጦርነት በዚያኛውም ወገን የነበሩት ሁሉ ያለ አግባብ ለአርጁና ወገን በጠላትነት የተሰለፉ ነበሩ፡፡ ይህ የብሀገቨድ ጊታ ውይይት መድረክ ሆኖ ነበረ፡፡ ዋናው ዓላማም አርጁናን ሰለ መንፈሳዊ እውቀት በደንብ ትእዛዙን ለመስጠት ነበረ፡፡ መንፈሳዊ ትምህረት ማለት በመጀመሪያ ደረጃ ነፍስ ምን እንደሆነች መረዳት ማለት ነው፡፡ ነፍስ ምን እንደሆነች ያልተረዳን ከሆነ የእኛ መንፈሳዊ እውቀት የት አለ? ብዙ ሰዎች በገላቸው በጣም የተመሰጡ ናቸው፡፡ ይህም የቁሳዊ ዓለም ኑሮ ይባላል፡፡ ነገር ግን መንፈስ ምን እንደሆነ የምታውቁ እና በዚህም እውቀት አንፃር በተግባር የምትሰማሩ ከሆነ ይህ መንፈሳዊነት ይባላል፡፡ አርጁና በጦርነቱ ላይ ለመዋጋት ተጠራጥሮ ነበረ፡፡ ይህም ከተዋጊዎቹ ጋራ በዝምድና ሰለሚቀራረብ ነበረ፡፡ በአርጁና እና በክርሽና መሀከልም ውይይት ነበረ፡፡ ይህም ውይይት የተካሄደው በጓደኝነት ደረጃ ነበረ፡፡ አርጁናም እንደተረዳው የጓደኝነት ውይይት ብቻ ችግሩን ሊፈታለት እንደማይችል ሰለተረዳው የክርሽና የድቁና አገልጋዩ በመሆን ትምህርቱን ለመረዳት ዝግጁ ሆነ፡፡ አርጁናም ሙሉ ልቦናውን ለክርሽና ለመስጠት በቃ፡፡ ሺስያስቴ ሀም ሻዲ ማም ፕራፓናም (ብጊ፡2 7) ”ውድ ክርሽና ሆይ እስከአሁን እንደ ጓደኛህ ሆኜ እወያይ ነበረ፡፡ አሁን ግን የአንተ የድቁና ተማሪ ለመሆን እመርጣለሁ፡፡“ "እባክህ በትእዝዝህ እየመራህ ከዚህ ግራ መጋባት አድነኝ፡፡ ምንስ ማድረግ ይገባኛል?" ውይይታቸውም ይህንን ደረጃ ላይ ሲደርስ ክርሽና ለአርጁና ይህንን ዓይነቱን ምክር ለመስጠት ጀመረ፡፡ አሁን እዚህ እንዲህ ተብሏል...... ማነው ለአርጁና የነገረው? ይህም የብሀገቨድ ጊታ ደራሲው ወይንም ተናጋሪው ነበረ .....በሀገቨድ ጊታም የተነገረው በክርሽና ነበረ፡፡ ይህም በክርሽና እና በአርጁና መሀከል የነበረው ውይይት ነው፡፡ የተፃፈውም በቭያሳዴቭ ነበረ፡፡ ከዚያም በኋላ መፅሀፍ ለመሆን በቃ፡፡ ለምሳሌ ንግግር ስናደርግ ሊቀዳ ይችላል፡፡ ከዚያም በኋላ ደግሞ ታትሞ እንደ መፅሀፍ ሊቀርብ ይችላል፡፡ ሰለዚህ በዚህ መጽሀፍ ውስጥ “ብሀገቫን ኡቫቻ” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ቭያሳዴቭ ፀሀፊው ነው፡፡ “እኔ እንደአልኩት“ አይልም የሚለውም ”ብሀገቫን ኡቫቻ“ ነው፡፡ ይህም ማለት ”አብዩ የመላእክት ጌታ እንዲህ አለ“ ማለት ነው፡፡