AM/Prabhupada 0261 - አብዩ ጌታ እና ትሁቱ የአብዩ አገልጋይ በአንድ ደረጃ ላይ ናቸው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture -- Seattle, September 27, 1968

ፕራብሁፓድ፡ በአሁኑ ግዜ እነዚህ ወጣቶች የክርሽና ንቃትን በአገራችሁ በማስተማር ላይ ይገኛሉ፡፡ የእኔም ትሁት የሆነው መልእክቴ እናንተም ይህንን የመሰለ ትልቅ ሀብት የሆነው የህይወት በረከትን በጥሞና ተከታትላችሁ እንድትረዱት ነው፡፡ የሀሬ ክርሽናን የቅዱስ ስም በቀላሉ በመዘመር ብቻ ፍቅር የተሞላበትን የክርሽናን ትሁት የአገልግሎት መንፈስ እንዲያድርባችሁ ለማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ልክ የክርሽናም ፍቅር እያደረባችሁ ሲመጣ ችግራችሁ ሁሉ ሊጠፋ ይችላል፡፡ ይህም ማለት በአደበታችሁ ሙሉ በሙሉ በጣም ደስተኞች ትሆናላችሁ፡፡ ችግር እና ጭንቀትም ሁሉ ከሀሳባችሁ ይጠፋል፡፡ አንድ ሰው በወር ደሞዙ 6000 ዶላር ሊያገኝ ይችላል፡፡ ሌላው ሰው ደግሞ 200 ዶላር ሊያገኝ ይችላል፡፡ አንድ ሰውም በካልካታ ውስጥ አይቻለሁ፡፡ እርሱም በወር 6000 ዶላር ያገኝ ነበረ፡፡ ነገር ግን እራሱን ገድሎ ተገኘ፡፡ እራሱን ገደለ? ለምን? ይህም ይህ ከፍተኛ ደሞዝ ብቻ ሊያስደስተው ስለአልቻለ ነው፡፡ ሌላ ተጨማሪ ነገር አስፈልጎት ነበረ፡፡ ሰለዚህ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ላይ ታላላቅ የገንዘብ ገቢ ቢኖረንም ፍፁም የሆነውን ደስታ በገንዘቡ ልናገኝ አንችልም፡፡ ምክንያቱም በዚህ መንፈስ ውስጥ እያለን ሁላችንም የስሜቶቻችን አሽከሮች በመሆናችን ነው፡፡ ይህም የስሜቶቻችን አገልጋይነት ቀርቶ የክርሽና ስሜቶችን በትሁትነት ወደምናገለግልበት ደረጃ መራመድ ይገባናል፡፡ በዚህም ሂደት ሁሉ የቁሳዊ ዓለም ችግሮች እንደሚፈቱ የተረጋገጠ ነው፡፡ እናመሰግናለን፡፡ (አገልጋዮች እጅ ነሱ፡፡) ጥያቄዎች አሉ? አገልጋይ፡ ፕራብሁፓድ የክርሽና ስእል ፍፁም ነው፡፡ አይደለምን? ይህም ክርሽና እራሱ ነው፡፡ የክርሽናስ ትሁት አገልጋይ እንደ ክርሽና ፍፁም ነውን? ፕራብሁፓዳ፡ የትሁት አገልጋይ ምስል? አገልጋይ፡ አዎን የንፁህ አገልጋይ ምስል፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አዎን አገልጋይ፡ ልክ እንደ ክርሽና ስእል ፍፁም ነውን?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን አገልጋይ፡ ለምሳሌ እንደ ነረሽንግሀ ዴቭ እና እንደ ፕራህላድ መሀራጅ ስእል፡፡ ፕራላድ ነረሽንግሀ ዴቭ ባለበት ቦታ ሁሉ ይገኛል፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አዎን አብዩ ጌታ እና ትሁት አገልጋዮቹ በአንድ ማእረግ ላይ ናቸው፡፡ ሁላቸውም ቢሆኑ፡፡ አብዩ ጌታ ስሞቹ ፎርሙ ዓይነቱ ተጓዳኞቹ እና እቃዎቹ ሁሉ በጠቅላላ ፍፁም ሆነው ይገኛሉ፡፡ ”ናማ ጉና ሩፓ ሊላ ፓሪ“ እንደዚሁም ታሪኩም ጭምር ለምሳሌ አሁን ሰለ ክርሽና እያዳመጥን ነው፡፡ ይህን ከክርሽና ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡ ሰለ ክርሽና ስንዘመርም ”ሀሬ ክርሽና“ ይህም ሀሬ ክርሽና ድምፅ እራሱ ከክርሽና ተለይቶ ሊታይ አይችልም፡፡ ሁሉም እነዚህ ፍፁም ሆነው ሊገኙ ይችላሉ፡፡ ሰለዚህ ንፁህ እና ትሁት የሆነው የክርሽና አገልጋይ ከክርሽና ተለይቶ ሊታይ አይችልም፡፡ ይህም በአንድ ግዜ ውስጥ አንድ እና የተለያየ ሆነም ይገኛል፡፡ ”አቺንትያ ብሄዳ ብሄዳ ታትቫ“ ይህንንም ፍልስፍና በትክክል ልንረዳው ይገባል፡፡ ክርሽና አብዩ የመላእክት ጌታ ታላቅ ሀይል ያለው ነው፡፡ በውናችንም የምናየውም ነገር እና የሚሰማን ነገር ሁሉ የተለያዩት የክርሽና ሀይሎች ናቸው፡፡ ይህም ሀይል እና ሀይል አመንጪው ተነጣጥለው ሊታዩ አይችሉም፡፡ ሰለዚህ ሁሉም ፍፁም ደረጃ ላይ ናቸው፡፡ ነገር ግን ይኀው ሀይል በማያ ወይንም በድንቁርና ሲሸፈን የተለያየ ሆኖ ሊታየን ይችላል፡፡ ይኀው ነው፡፡