AM/Prabhupada 0267 - ቭያሳዴቭ ስለ ክርሽና ገለፃ ሰጥቷል፡፡



Lecture on BG 2.10 -- London, August 16, 1973

ሰለዚህ ክርሽና ብሀክቲ ማለት እንደዚያ ነው፡፡ ይህም የቁሳዊ ዓለም ስሜታዊ ፍላጎታችንን በቁጥጥር ስር ማዋል ማለት ነው፡፡ ልክ ክርሽና ስሜቶቹን ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር ሀይል እንዳለው በተመሳሳይ የክርሽና ትሁት አገልጋይ የሆኑ ሁሉ ስሜቶቻቸውን ሙሉ በሉሙሉ የመቆጣጠር ሀይል አላቸው፡፡ ህርሺኬሻ ይህም ልክ እንደ ”ያሙና አቻርያ“ መምህር ይመሰላል፡፡ ፀሎቱን ያደርጋል ንግግር ያደርጋል ”ያድ አቫድሂ ማማ ቺታሀ ክርሽና ፓዳራቪንዴ ናቫ ናቫ ድሀማኒ ኡድያታም ራንቱም አሲት“ የክርሽናን የሎተስ ዕፅዋት በመሰለው እግሩ ጠለላ በማግኘቴ የመንፈሳዊ ደስታ እየተሰማኝ እገኛለሁ፡፡ ”ያድ አቫድሂ ማማ ቺታሀ ክርሽና ፓዳራቪንዴ ክርሽና ፓዳራቪንዴ“ የሎተስ ዕፅዋት የመሰለ እግሩን ጠለላ በማድረግ ” የእኔ ቺታ ወይንም ልቤ ወደ ሎተስ ዕፅዋት ወደመሰለው የክርሽና እግር ተስቦ ይገኛል“ ”ዳድ አቫድሂ ባታ ናሪ ሳንጋሜ“ ከዚያም ግዜ ጀምሮ የወሲብ ሕይወት በሀሳቤ ውስጥ በገባ ቁጥር ” ብሀቫቲ ሙክሃ ቪካራሀ“ እጠላዋለሁ እተፋበታለሁ ይህ ክርሽና ብሀክቲ ነው፡፡ ክርሽና ብሀክቲ እንዲህ ነው፡፡ ”ብሀክቲ ፓሬሻኑብሀቫ ቪራክርቲር አንያትራ ስያት“ በዚህ ዓለም ላይ ያለ በጣም የሚስብ ነገር ቢኖር የወሲብ ግኑኝነት ነው፡፡ ይህም የቁሳዊው ዓለም መሰረት ነው፡፡ እነዚህ ሌት ተቀን ሲሰሩ የሚገኙት ሁሉ የመጨረሻው ዓላማቸው የወሲብ ግኑኝነታቸውን ለመደሰት ነው፡፡ ”ያን ማይትሁናዲ ግርሀ“ ብዙም ለሚመጣ አደጋ እራሳቸውን እያጋለጡ ይገኛሉ፡፡ ካርሚዎች ተብለው ይታወቃሉ፡፡ በከባድ ስራ ላይም ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ የሕይወትስ የመጨራሻው ደስታቸው ምንድን ነው? ይህም የወሲብ ግኑኝነት ነው፡፡ ”ያን ማይቱናዲ ግርሀሜድሂ ሱክሀም ሂ ቱቻም“ በጣም የሚያፀይፍ ሕይወት ነው ነገር ግን የደስታቸው ምንጭ ይኅው ነው፡፡ ይህ የቁሳዊ ዓለም ኑሮ ነው፡፡ ክርሽና ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ አንዳንድ ተንኮለኞች ስዕሎችን ሲስሉ ይገኛሉ፡፡ የሚስሉትም ስዕሎች ክርሽና ጎፒዎችን አቅፎ የሚያሳይ ነው ፡፡ ይህ በሰዎች የተወደደ ነው፡፡ አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ነግሮኝ ነበረ፡፡ ማን ነበር? እነዚህም አትሪስቶች ክርሽና ፑተናን ሲገል የሚያሳይ ስዕል ሲስሉ አይገኙም፡፡ ወይም ክርሽና ካምሳን ሲገል .... ክርሽና የተለያዩ ስዕሎች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ተንኮለኞች እነዚህ የመሳሰሉትን ስዕሎች ሲስሉ አይታዩም፡፡ የሚስሉት ስዕል ግን ክርሽና ከጎፒዎቹ ጋር የነበረውን ግኑኝነት ብቻ ነው፡፡ አንድ ክርሽናን ለመረዳት የማይችል ሰው ክርሽና ማን እንደሆነ የማያውቅ የትኛው ቭያሳዴቭ ነው ሰለክርሽና በዘጠኝ መፃህፍት ገልፆ ተንትኖ ክርሽናን ለማስረዳት ከዚያም በአስረኛው መፅሀፍ ሰለ ክርሽና መወለድ ለመግለፅ የጀመረው? እነዚህ ተንኮለኞች ግን በቀጥታ ወደ ራስ ሊላ ስዕል ዘለው ለመግባት ይሻሉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ክርሽናን መረዳት ያሰፈልጋል፡፡ ለመጀመሪያ ግዜ ከአንድ ትልቅ ሰው ጋር ለመቅረብ ከፈለግህ በመጀመሪያ ሰለ እርሱ በደንብ ለመረዳት ጥረት ማድረግ አለብህ፡፡ ከዚያም ሰለ ቤተሰቡ እና በቅርብ የሚያደርገውን ሁሉ ለመረዳት ትችላለህ፡፡ እነዚህ ተንኮለኞች ግን በቀጥታ ዘለው ወደ ራስ ሊላ ለመግባት ይፈልጋሉ፡፡ ከዚህም አለመረዳት ይመጣል፡፡ ሰለዚህም አንዳንድ ግዜ “ክርሽና ግብረገብ የለውም” ብለው ያወራሉ፡፡ ክርሽና እንዴ ያለ ግብረገብ ሊኖር ይችላል? ክርሽናን በመቀበል እና ይክርሽናን ቅዱስ ስም በመዘመር ግብረ ገብ የሌለው ሰው ሁሉ መልካም ግብረገብ እየያዘ ሲመጣ እናያለን፡፡ ይህም እንዲህ ሆኖ ክርሽና ግብረገብ የለውም ይላሉ፡፡ ይህ ሞኝነት ነው፡፡ የክርሽናን ቅዱስ ስም በመዘመር ግብረገብነት የሌለው ሁሉ ስርዓት ለመያዝ ይበቃል፡፡ ይህ የክርሽና ግብረገብነት መኖር ወይም አለመኖር በተንኮለኛ ፕሮፌሰሮች ሲነገር ይታያል፡፡