AM/Prabhupada 0304 - ማያ አብዩ ፈጣሪ አምላክን ልትሸፍነው አትችልም፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture -- Seattle, October 2, 1968

ፕራብሁፓድ፡ ቀጥል ታማላ ክርሽና፡ "ይህም በአንድ ግዜ የሚታየው የአንድነት እና የልዩ ነት ብህርይ በተለያዩ ግኑኝነቶች ውስጥ የሚታይ ነው፡፡" "ይህም በነፍሳት እና በአብዩ የመላእክት ጌታ መሀከል ነው፡፡" ፕራብሁፓድ፡ አሁን ሰለዚህ በአንድ ግዜ አንድነት እና ልዩነት ስለምንለው አሁን የጠቀስነውን የባህር ዳርቻ ያለውን የመሬትን ምሳሌ ውሰዱ፡፡ አንድ ሰው እንዲህ ሊል ይችላል፡፡ "ኦ ያንን የውሀ ወገን አየሁት" ሌላው ሰው ደግሞ "አይደለም እኔ የማየው የመሬቱን ወገን ነው፡፡" እንደዚሁም ሁሉ በአንድ ግዜ መሬቱ አንድነትም ልዩነትም ይዞ ይገኛል፡፡ የእኛም ደረጃ እንዲሁ ነው፡፡ እኛ ነፍስ እንደመሆናችን እንደ ክርሽና ወይንም አብዩ ጌታ መንፈስ ነን፡፡ እርሱም የተሟላ የነፍስ አቅዋም ሲኖረው እኔ ደግሞ የዚሁ ነፍስ ቅንጣፊ ወይንም ቁራሽ ሆኜ እገኛለሁ፡፡ ልክ እንደ ፀሀይ፡፡ የፀሀይ ኮከብ እና የፀሀይ መንፀባረቅ ይሰማናል፡፡ የሚያንፀባርቁት የፀሀይ ሞሎኪዩሎችም የፀሀይ ወገን ናቸው፡፡ የእነዚህም የአቶሚክ አካሎች ተሰባስበው የፀሀይን ነፀብራቅ ይሰጡናል፡፡ እኛም ልክ እንደ ፀሀይ የአቶሚክ አካሎች ስናንፀባርቅ እንገኛለን፡፡ ነገር ግን በሀይል እንደ ሙሉው የፀሀይ ኮከብ ልንሆን አንችልም፡፡ የሚያንፀባርቁት የፀሀይ ሞሎኪዩሎች እንደ የፀሀይ ኮከብ በሀይላቸው እኩል ሆነው አይገኙም፡፡ ነገር ግን በዓይነታቸው ተመሳሳይ ናቸው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እኛም በምድር የምንገኝ ነፍሳት የአብዩ አምላክ ወይንም የክርሽና የደቀቀው ቅንጣፊ አካል ሆነን እንገኛለን፡፡ ሰለዚህም እንደእርሱ እናንፀባርቃለን፡፡ ዓይነታችንም ተመሳሳይ ነው፡፡ ለምሳሌ የወርቅ ትንሽ ቁራሽም ወርቅ ሆኖ ይገኛል፡፡ ብረት አይደለም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እኛም እንደ አብዩ አምላክ ነፍስ ነን፡፡ በዚህም አንድነት አለን፡፡ ነገር ግን እኛ በሀይላችን ውስን እና ትንሽ ሰለሆንን..... ልክ እንደሰጠሁት ምሳሌ ማለት ነው፡፡ ይህ በባህር ዳርቻ የሚገኘው መሬት አነስተኛ ነው፡፡ አንዳንድ ግዜ በውሀ ተሸፍኖ እናየዋለን፡፡ ነገር ግን ትልቅ ሆኖ የሚታየው መሬት ውሀ ሲሸፍነው አይታይም፡፡ እንደዚህም ሁሉ ማያ (የቁሳዊ ዓለም ምትሀት) ልትሸፍን የምትችለው ይህንን የጌታን የቅንጣፊ አካል ነፍስን ነው፡፡ የአብዩ አማላክን ግን ማያ በምትሀቷ ልትሸፍነው አትችልም፡፡ ልክ እንደሰጠነው ምሳሌ እንደ ሰማይ እና እንደ የፀሀይ ጮራ፡፡ የፀሀይ ጮራ በደመና ሊሸፈን ይችላል፡፡ ነገር ግን ከደመናው በላይ በአይሮፕላን ብትሄዱ ይህም ከደመናው በላይ ማለት ነው እዚህም የፀሀይ ጮራ በሙሉ ሀይሉ እየተንፀባረቀ ታያላችሁ፡፡ ይህም ደመና መላ ፀሀይን ሊሸፍን አይችልም፡፡ እንደዚህም ሁሉ ማያ የአብዩ የመላእክት ጌታን በምትሀት ልትሸፍን አትችልም፡፡ ማያ ግን ትንሿን የአብዩ አምላክን ቁራሽ (ነፍስ) ለመሸፈን ትችላለች፡፡ የማያቫዲ ፍልስፍናም እንዲህ ይላል "አሁን በማያ ተሸፍኜ እገኛለሁ፡፡ ከዚህ ማያ ግን እንደተላቀቅሁ ወዲያውኑ ከአብዩ አምላክ ጋር አንድ እሆናለሁ፡፡" ከመላው ከአብዩ አምላክ ጋር የአንድነት ባህርይ አለን፡፡ ይህም እንደ ፀሀይ ጮራ እና እንደ የፀሀይ ኮከብ ማለት ነው፡፡ በዓይነታቸው ልዩነት የላቸውም፡፡ ፀሀይም ባለበት ቦታ ሁሉ የፀሀይ ጮራ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ጮራው አነስተኛ ብዛት ያለቸውን ሞሎኪዩሎች ይዞ ይገኛል፡፡ የፀሀይ ጮራ ሞሎኪዩሎች ብዛት ከፀሀይ ኮከብ ጋር ፈፅሞ ሊወዳደሩ አይችሉም፡፡ ይህ ነው በዚህ ምእራፍ ውስጥ በቼታንያ መሀፕራብሁ ተገልጾ የሚገኘው፡፡