AM/Prabhupada 0321 - እራሳችሁን ሁል ግዜ እንዴት ከዓብዩ ጌታ የሀይል ማመንጫ ጋር ለመገናኘት እንደምትችሉ ጥረት አድርጉ፡፡



Lecture on SB 1.15.28 -- Los Angeles, December 6, 1973

ቼይታንያ ማሃፕራብሁ እንደ ሃላፊነታችሁ ስራ መፈጸም ይገባችኋል ብሏል: እንደታዘዘው:”አፓኒ አቻሪ“ ከዚያም ሌላውን ማስተማር ይገባችኋል: እራሳችሁም በተግባር ካላሳያችሁ:ቃላቶቻችሁ ምንም ዋጋ አይኖራቸውም: ”ኤቫም ፓራምፓራም ፕራምታም“ (ብጊ 4.2) ከዋናው የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ድርጅት ጋር የተያያዛችሁ ከሆነ:ኤሌክርትሪክ ማግኘት ትችላላችሁ አለበለዛ ግን የኤሌክትሪክ ገመድ ማንጠልጠል ምን ዋጋ ይኖረዋል? ገመዱ ብቻ ምንም ሊጠቅማችሁ አይችልም:ከማከፋፈያው ጋር መያያዝ ያስፈልጋችኋል: የተያያዘው ከተቆረጠም የገመዱ መንጠልጠል ዋጋ አይኖረውም: ስለዚህም የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ማለትም:እራሳችንን ከዋናው የማከፋፈያው ድርጅት ማገናኘት ማለት ነው: እንደዚሁም ሁሉ በየሄዳችሁበት:ብርሃን ይኖራል: ከልተገጣጠማችሁ ደግሞ:ብርሃን ሊኖር አይችልም: አምፖሉ አለ:ኮረንቲ ክሩም አለ:ማብሪያ ማጥፊያውም አለ:ሁሉም ነገር አለ: አርጁናም እንዲህ ነው የተሰማው:”እኔ ያው እራሱ አርጁና ነኝ“ ”በኩሩክ ሼትራ የተዋጋሁ እኔ ራሱ አርጁና ነኝ“ ”በጣም ታላቅ ተዋጊ ተብዬ የምጠራ ሰው ነበርኩኝ:ይህም እራሱ የእኔ ደጋን ነው:ቀስቶቼም እራሳቸው የእኔ ቀስቶች ናቸው“ ”አሁን ግን ዋጋ ቢስ እንደሆንኩ ይሰማኛል:ክርሽናም አጠገቤ ስለሌለ:እራሴን ለመከላከል አልቻልኩም“ “ክርሽናም አጠገቤ የለም” እንዲህም እያለ:ክርሽና የነገረውን ሁሉ ማስታወስ ጀመረ: ይህም በኩሩክሼትራ ጦርነት ላይ እያለ: የተማረውን ነው: ክርሽና ከቃሉ በምንም አይለይም:ይህ ፍጹም እውነት ነው: ክርሽና 5000 አመት በፊት የተናገረውን:አሁን መከተል ብትጀምሩ:ወዲያውኑ ከክርሽና ጋር መግናኘት ትችላላችሁ: ይህ ነው ስርአቱ:አርጁናንም እዩት:እንዲህም አለ:”ኤቫም ቺንታያቶ ጂሽኖ ክርሽና ፓዳ ሳሮሩሃም“ ክርሽናን ሲያስታውስ እና:በጦር ሜዳም ላይ የተቀበለውንም መመሪያ ሲያስታውስ: ወዲያውኑ አንደበቱ በሰላም ”ሻንታ“ ተሞላ:ከጭንቀቱም ወረደ:ይህ ነው ስርአቱ: ከክርሽና ጋር የጠበቀ ግንኙነት አለን:ይህም ዘለአለማዊ ነው:ይህም ሰውሰራሽ አይደለም: እንደዚሁም እራሳችንን ከክርሽና ጋር ሁልግዜ የምናያይዝ ከሆነ:በህይወታችን ምንም ረብሻ አይኖርም: ”ሰላምተኛ“ “ያም ላብድህቫ ቻፓራም ላብሃም ማንያቴ ናድሂካም ታታሃ” ይህንንም የሰላም መድረክ ካገኛችሁ:የንቃቱ ትቁ ትርፍ:ወይንም ትልቁ ገቢ ነው: “ያም ላብድቫ ቻ" ከዚህም የተለየ:ሌላ ምኞትም ሊኖራችሁ አይችልም: ከፍትኛም ገቢ ወይንም ትርፍ እንዳላችሁ ሁኖ ይሰማችኋል: ”ያም ላብድህቫ ቻፓራም ላብሃም ማንያቴ ናድሂካም ታታሃ ያስሚን ስትሂታሃ“ በዚህም ደረጃ ላይ ሁናችሁም ከረጋችሁ:”ጉሩናፒ ዱህኬና“ (ብጊ 6.20-23) በጣም ከባድ የሚባለው እንኳን አደጋ:ሊረብሻችሁ አይችልም: ይህም ሰላም ነው:ትንሽ በቆረቆረን ግዜም የምንረበሽ ከሆነ ግን:ይህ ሰላም አይደለም: በክርሽና ንቃትም የረጋችሁ ከሆነ:በትልቅም አደጋ ቢሆን ልትረበሹ አትችሉም: ይህ ነው የክርሽና ንቃት ብቁነት: አመሰግናለሁ: