AM/Prabhupada 0327 - ህያው ነፍሳችን የምትገኘው በዚህ ቁሳዊ ገላችን እና በዓለማዊው የመንፈስ ገላችን ውስጥ ተሸፍና ነው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Room Conversation -- April 20, 1976, Melbourne

ካርሎስ ጃርቪስ:ቅድም እንደነገርከኝ ከሆነ:በቀን ከ1000 ዶላር በላይ:በመጽሃፍ ሽያጭ ታገኛለህ:ፕራብሁፓድ:አዎን ካርሎስ ጃርቪስ:ሃሳብህ ወደ ህዝብ እንዲተላለፍ ከፈለግህ:ለምን እነዚህን መጽሃፍቶች ሽጠህ ገንዘብ ትሰበስባለህ? ፕራብሁፓድ:ካልከፈልክበት አታነበውም:በነፃ ከሰጠሁህ እንዲህ ትላለህ: ”አሃ ይህ ስሜት የማይሰጥ መሆን አለበት:በነፃ እየሰጡት ነው ያሉት“ ትላለህ: ካርሎስ:በነፃ መስጠት ሳይሆን:ምናልባት:ለመጽሃፉ የሚሸፍነውን ወጪ ያህል አስከፍላቸው: ፕራብሁፓድ:ሲከፍሉ:መጽሃፉ ምን መልእክት እንዳለው ለመረዳት ይሞክራሉ: ”ምንድን ነው እነዚህ መጻህፍቶች የሚሉት” እስኪ ልየው?“ በነጻ ካገኘኅው ግን:በመደርደርያህ ላይ ለመቶ አመታት ሊቀመጥ ይችላል: አልፎ ተርፎም:እነዚህን መፃህፍቶች ደግመን ማተም አለብን:ማን ለዚህ ይከፍላል:እኛ ገንዘብ የለንም: ካሮል ጃርቪስ:ታድያ መንገድ ላይ ተሰብስቦ የተረፈው ገንዘብ ሁሉ ወዴት እየሄደ ነው? ፕራብሁፓድ:እንቅስቃሴያችንን እያስፋፋን ነው:ቅርንጫፎችም እየከፈትን ነው: መጻህፍቶችም እየአተምን ነው:የብሃክቲቬዳንታ የመጽሃፍቶች ትረስትም አቋቁሜአለሁ: ያም የእኔ ኑዛዜ ነው:የእኔም ኑዛዜ:50 % የተሰበሰበው ገንዘብ:ወደ መጽሃፍ ማተሚያ ቤት መሄድ ይገባዋል: ሌላው 50% ደግሞ:እንቅስቃሴውን ለማስፋፋት መሄድ አለበት: ስለዚህ ምንም አለማዊ ትርፍ የለውም: ካሮል ጃርቪስ:አንድ ተጨማሪ ጥያቄ ብጠይቅህ? መልእክትህ ምንድን ነው? ፕራብሁፓድ:የእኛ መልእክት:መላ ህዝብ:ገላቸውን እንደ እራሳቸው አድርገው ይቆጥሩታል:ይህ ግን ትክክለኛ አስተሳሰብ አይደለም: ነፍስ ወይንም ሰውየው ግን ከገላው ውስጥ ነው: ልክ አንተ ሸሚዝህ እና ኮትህ እንዳልሆንክ እና:ከውስጥ እንደሆንክም ሁሉ: እንደዚሁም ሁሉ:ነዋሪ ነፍስ:ጎልቶ በሚታየው ገላ እና:አእምሮን እንደመሰለ ስስ ገላ ውስጥ ነው ያለችው: ስስ ገላ ማለት:ሃሳብ:አእምሮ:እና የእኔነት ባህርይ ናቸው: ጎልቶ የሚታው ገላ ደግሞ:የሚከተሉትን ይዞ ይገኛል: መሬት:ውሀ:እሳት:አየር እና ክፍት ቦታ:እንዚህ 5 ነገሮች ናቸው:በጠቅላላ 8 ይሆናሉ ማለት ነው: ይህ የአምላክ ዝቅተኛ ሃይሉ ነው: የከፍተኛው የአምላክ ሃይል ደግሞ:በእነዚህ 8 ነገሮች ውስጥ የገኛል:5 ጎላ ያሉት እና 3 ስስ የሆኑትን አካሎች: እንደዚህም ማጥናት አለብን:ልክ ያንን ልጅ እንደነገርኩት: ትልቅ ማሽን በሰማይ የሚበር መፍጠር ትችላላችሁ እንደ ጃምቦ 747:ነገር ግን ለምን ፓይለቱንም አትፈጥሩም?