AM/Prabhupada 0340 - እኛ በተፈጥሮ መሞት የሚገባን አይደለንም፡፡ ነገር ግን በተፈጥሮ ሞትን ለማየት ተገደናል፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on BG 9.1 -- Melbourne, June 29, 1974

“ናሞ ማሃ ቫዳንያያ ክርሽና ፕሬማ ፕራዳያቴ:ክርሽናያ ክርሽና ቼይታንያ:ናምኔ ጎውራ ትቪሼ ናማሃ” (ቼቻ ማድህያ 19.53) ሽሪላ ሩፓ ጎስዋሚ:ሽሪ ቼይታናያ ማሃ ፕራብሁን ፕራያግ ውስጥ ሲያገኛቸው: በህንድ አገር ውስጥ ፕራያግ የሚባል ቦታ አለ: ሽሪ ቼይታንያ ማሃ ፕራብሁም:የሳንያሳ የመነኩሴ ስርአቱንም እንደ ጨረሰ: ወደ ፕራያግ እና ወደ ሌላ ቅዱስ ቦታዎች ሂዶ ነበር: ሽሪላ ሩፓ ጎስዋሚም የመንግስት ሚኒስቴር ነበረ: ሁሉን ግን እርግፍ አድርጎ ለመንፈሳዊ አለም ብሎ ተወ:የሀሬ ክርሽናንም እንቅስቃሴ ከሽሪ ቼይታንያ ጋር ገጠመ: መጀመሪያ ላይም እንደተገናኙ:ይህንን ጥቅስ አቀረበ:“ናሞ ማሃ ቫዳንያያ” “ቫዳንያያ” ማለት “በጣም የገነነ ነው ማለት ነው” የተለያዩ የአምላክ ወገኖች በአለም ላይ ይመጣሉ:ነገር ግን ሩፓ ጎስዋሚ እንዲህ አለ: ይህ የአምላክ ወገን ቼይታንያ ማሃ ፕራብሁ በጣም የገነነ ነው: “ናሞ ማሃ ቫዳንያያ” ለምንድነው በጣም የገነነው? ክርሽና ፕሬማ ፕራዳያቴ:“ክርሽናን በዚህ በክርሽና ንቃት እንቅስቃሴህ እየሰጠህ ነው” ክርሽናን መረዳት በጣም አስቸጋሪ ነው: ክርሽናም በብሃገቨድ ጊታ እንዲህ ብሏል:“ማኑሽያናም ሳሃሽሬሹ ካሽቺት ያያቲ ሲድሃዬ (ብጊ 7.3) ”ከብዙ ሚሊዮን ሰዎች መሃከል:በዚህ ዘመን ብቻ ሳይሆን:ከዚህ ዘመንም በፊት“ ማኑሽያናም ሳሃሽሬሹ:”ከብዙ ሚሊዮን ህዝብ መሃከል “ካሽቺት ያያቲ ሲድሃዬ” አንድ ሰው ብቻ ከልቡ ነጹህ እና ፍጹም መሆን ይፈልጋል: በጠቅላላው አነጋገር:ፍጹም መሆን ምን እንደሆነም አያውቁትም:ህይወት ማሳካት ምን እንደሆነ አያውቁትም: ይህም ማለት መወለድን:መሞትን:ማረጅን:መታመምን ማቆም ማለት ነው:ይህ ነው ህይወትን ማሳካት ማለት: ሁሉም ለማሳካት ይሞክራል:ነገርግን ይህ ምን እንደሆነ አልተረዱም: ህይወት ማሳካት ማለት:ከእነዚህ አራት ነፃ መሆን ማለት ነው: ምንድን ናቸው? መወለድ:መሞት:ማረጅ: መታመም:ሁሉም ማንም መሞት አይፈልግም:ግን ይህ ግዳጅ ነው:መሞት አለብን: ይህ ያልተሳካ ሁኔታ ነው:እነዚህ ተንኮለኞች:ይህን አይረዱም:መሞት ያለ ነው ይላሉ:ይህ ልክ አይደለም: ምክንያቱም ነፍስ ዘላለማዊ ናት:መሞትም የለብንም:ግን ተፈጥሮ ይህንን ፈጥሯል: ይህም መቆም አለበት: