AM/Prabhupada 0344 - የሽሪማድ ብሀገቨታም የሚያስተምረን እንዴት ብሀክቲን ወይንም የፍቅር አገልግሎትን ለጌታ እንደምናቀርብ ነው፡፡

Revision as of 06:06, 29 November 2017 by Sahadeva (talk | contribs) (Text replacement - "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->" to "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Lecture on SB 3.26.11-14 -- Bombay, December 23, 1974

ቭያሳዴቭ፡ መላ የቬዲክ ስነጽሁፎችን ጽፎ ከጨረሰም በኃላ የልቡ የደረሰ ሆኖ አልተሰማውም ነበረ፡፡ አራቱን መሰረታዊ ቬዳዎችን ፅፎ ነበረ፡፡ ከዚያም ፑራናዎችን ፅፎ ነበረ፡፡ ፑራናዎች የቬዳ ስነፅሁፎችን ደግፈው የሚያብራሩ ናቸው፡፡ ከዚያም ቬዳንታ ሱትራን ፃፈ፡፡ ይህን የቬዲክ እውቀት የመጨረሻ መደምደሚያው ነው፡፡ “ቬዳንታ ሱትራ” እንዲሁም ፅፎ የልቡ አልደረሰም ነበረ፡፡ ከዚያም የመንፈሳዊ መምህሩ ናራዳ ሙኒ እንዲህ ብሎ ጠየቀው፡፡ “ይህንን ሁሉ ለሰው ልጅ ሕብረተሰብ የሚያገለግል እውቀትን በብዙ መፃህፍቶች ላይ ጽፈህ ልብህ ያለረካው ለምንድነው” ብሎ ጠየቀው፡፡ ቭያሳዴቭብ እንዲህ አለ፡፡ “አዎን ብዙ መፃህፍቶችን እንደፃፍኩኝ ተረደቻለሁ፡፡ ነገር ግን ልቤ አልረካም፡፡ ምክንያቱ ግን ለምን እንደሆነ ልረዳ አልቻልኩም፡፡” ከዚያም ናረዳ ሙኒ እንዲህ አለው፡፡ “ልብህ ያልረካበት ምክንያቱ ስለ አብዩ የመላእክት ጌታ እንቅስቃሴዎች ባለመግለፅህ ነው፡፡” ሰለዚህም ልብህ አለረካም፡፡ በመፅሀፍቶችህ የገለጽከው ሰለ ውጪ ነገሮች ነው፡፡ ነገር ግን የአብዩ ጌታ የውስጣዊ ውይይቶችን አልገለፅክም፡፡ በዚህም ምክንያት ልብህ አልረካም፡፡ አሁን ይህንን መግለፅ ይገባሀል፡፡ ይህንንም በመሰለ በመንፈሳዊ አባቱ ናራዳ ሙኒ ትእዛዝ የቭያሳዴቭ የመጨረሻው ስነፅሁፉ የሽሪማድ ብሀገቨታም ነበረ፡፡ “ሽሪማድ ብሀገቨታም አማላም ፑራናም ያድ ቫይሽናቫናም ፕሪያም” ሰለዚህም ቫይሽናቫዎች ሽሪማድ ብሀገቨታምን እንደ “አማላ ፑራናም” አድርገው ተቀብለውታል፡፡ “አማላ ፑራናም” ማለት... አማላም ማለት ያልተበከለ ማለት ነው፡፡ ሌሎቹ ፑራናዎች ሁሉ ሰለ ካርማ ግያና ዮጋ የሚገልፁ ናቸው፡፡ ሰለዚህም “ሳማላም” ወይንም በቁሳዊ መንፈስ የተበከሉ ናቸው ማለት ነው፡፡ ሽሪማድ ብሀገቨታም ግን ስለ “ብሀክቲ” ብቻ ሰለሚገልጽ አማላም ተብሎ ይታወቃል፡፡ ብሀክቲ ማለት ከአብዩ ጌታ ጋር በቀጥታ መገናኘት ማለት ነው፡፡ ብሀክታ እና ብሀጋቫን፡፡ የሁለቱ ልውውጥ ደግሞ ብሀክቲ ይባላል፡፡ ብሀገቫን እና ብሀክታዎች አሉ፡፡ ይህም ልክ እንደ ጌታ እና እንደ አገልጋይ ይቆጠራል፡፡ የእነዚህም የጌታ እና የአገልጋይ ግኑኝነት በአገልግሎት የተመሰረተ ነው፡፡ አገልግሎት መስጠት በተፈጥሮዋችን ያለ ነው፡፡ ሁል ግዜም አገልግሎት ስንሰጥ እንገኛለን፡፡ ነገር ግን ህሊናችን እና እውቀታችን (ቺታ) በዓለማዊ ነገሮች ሰለተበከለ የምንሰጠው አገልግሎት ሁሉ ወደ ተለየ መንገድ ሆኗል፡፡ አንዳንድ ሰው የሚሰጠው አገልግሎት ሁሉ ለቤተሰቡ ለማህበሩ ለሕብረተሰቡ ወይንም ለአገሩ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይንም ለሰው ልጅ ህብረተሰብ ወይንም ለሌላ ተገልጋይ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን እነዚህ አገልግሎቶች ሁሉ በቁሳዊ ዓለም መንፈስ የተበከሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን የምናቀርበው አገልግሎት ሁሉ በክርሽና ንቃት የዳበረ ከሆነ አገልግሎቱ ፍፁም ጥሩ ይሆናል፡፡ ይህም ፍፁም ጥሩ የሆነ ሕይወት ነው፡ ሰለዚህ ይህ የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ የሰው ልጅን ሕብረተሰብ ወደ ፍፁም ጥሩ የሆነ መድረክ ላይ ለማድረስ ነው፡፡ ይህም ለአብዩ ጌታ አገልግሎትን በመስጠት ነው፡፡ እናመሰግናለን፡፡