AM/Prabhupada 0361 - እነርሱ የእኔ ጉሮዎች “መምህራን” ናቸው እንጂ እኔ የእነርሱ ጉሩ አይደለሁም፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on BG 7.3 -- Bombay, March 29, 1971

ይህንንም የትሁት አገልግሎት ለጌታ የምንሰጥ ከሆነ እና ቅዱስ ስሙንም የምንዘምር ከሆነ ማለት ይህንንም ለመዘመር ቀላል የሆነ የክርሽናን ቅዱስ ስም የምንቀበል ከሆነ ክርሽናን መረዳት እንችላለን፡፡ ለምሳሌ እነዚህን ልጆች የመዘመሩን ስርዓት አስተምረናቸዋል፡፡ እነርሱም በትህትና ተቀብለውት ይገኛሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተመደበላቸው አገልግሎት ቢያከናውኑ ቀስ በቀስ ክርሽናን ለመረዳት ይችላሉ፡፡ እንደምታይዋቸውም በዚህ ንቃት የዳበሩት አገልጋዮች በደስታ ሲደንሱ እናያቸዋልን፡፡ ይህም የሚያሳየን ምን ያህል ክርሽናን እንደተረዱት ያሳየናል፡፡ ይህም ስርዓት በጣም ቀላል ነው፡፡ ማንም ሰው ከመሳተፍ ሊከለከል አይችልም፡፡ ”አንተ ሂንዱ ስለአልሆንክ የሀሬ ክርሽናን ቅዱስ ስም መዘመር አትችልም“ አንልም፡፡ ዬይ ክርሽና ታትቫ ቬታ ሴይ ጉሩ ሆይ (ቼቻ፡ ማድህያ 8.128) ምንም እንኳን አንድ ሰው ሂንዱ ሙስሊም ወይንም ክርስትያን ቢሆንም እንኳን ለመሳተፍ ይችላል፡፡ አንድ ሰው የክርሽናን ሳይንስ ማዋቅ ይገባዋል፡፡ ይህም ብሀገቨድ ጊታ ነው፡፡ በዚህም እውቀት የመንፈሳዊ አባት ለመሆን ይችላል፡፡ ይህ ልጅ እና ይህቺ ልጃገረድ አሁን ተጋብተዋል፡፡ እኔም ወደ አውስትራልያ ልልካቸው ነው፡፡ ልጁ ከአውስትራልያ መጥቶ ነበር፡፡ ልጅቷ ደግሞ ከስዊድን መጥታ ነበረ፡፡ አሁን ጋብቻ መስርተዋል፡፡ በሲድኒ ያለውን ቅርንጫፋችንንም ለማስተዳደር በቅርቡ ይሄዳሉ፡፡ አሁን በቅርቡ በሁለት ወይንም በሶሶስት ቀን ውስጥም ልልካቸው አስቤአለሁ፡፡ ይህንንም ቅርንጫፍ ይንከባከባሉ ስብከታቸውንም ይቀጥላሉ፡፡ ይህም የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ በእነርሱ እርዳታ እየተስፋፋ ይገኛል፡፡ እኔ ብቸኛ ነኝ ነገር ግን እነርሱ እየረዱኝ ነው፡፡ እነርሱም የእኔ ጉሩዎች ናቸው፡፡ እኔ የእነርሱ ጉሩ አይደለሁም፡፡ (ጭብጨባ) ምክንያቱም የእኔን የጉሩ መሀራጅ ትእዛዝ እንድፈጽም በመርዳት ላይ ሰለሚገኙ ነው፡፡ ይህም በጣም ደስ የሚያሰኝ የሕብረት ስራ ነው፡፡ አንድ ሰው ወደ አውስትራሊያ ይሄዳል ሌላው ደግሞ ወደ ፊጂ ደሴት ይሄዳል ሌላው ደግሞ ወደ ሆንግ ኮንግ ይሄዳል ሌላው ደግሞ ወደ ቼኮዝሎቫክያ ይሄዳል ወደ ራሽያ ለመሄድም ጥረት በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ ወደ ቻይናም የመሄድ እድሉ ሳይኖረን አይቀርም፡፡ በሙከራም ላይ እንገኛለን፡፡ ሁለት ልጆችም ወደ ፓኪስታን ልከናል፡፡ አንድ ወደ ዳቻ አንድ ደግሞ ወደ ካራቺ ልከናል (ጭብጨባ) ሰለዚህ እነዚህ ልጆች እና አሜሪካኖቹ ልጆች እየረዱኝ ይገኛሉ፡፡ ቅር ያለኝ ነገር ቢኖር ግን ህንዶች ለሲህ አገልግሎት እየቀረቡ አይገኙም፡፡ ጥቂት አሉ ብዙ ባይሆኑም፡፡ ወደ ፊት መምጣት ይገባቸዋል፡፡ በተለይ የወጣቱ ህብረተሰብ ወደ እዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባት ይገባቸዋል፡፡ ከዚያም ይህንን የክርሽናን ንቃት በዓለም ላይ ሁሉ ማስፋፋት ይገባቸዋል፡፡ የህንዶች አብይ ስራ ይህ ነው፡፡ ቼይታንያ መሀፕራብሁ እንዲህ ብሎ ነበረ፡፡ ”ብሀራታ ብሁሚቴ ሆይላ ማኑስያ ጃንማ ያራ ጃንማ ሳርትሀካ ካሪ ካራ ፓራ ኡፓካር“ (ቼቻ አዲ 9.41) ይህ ”ፓራ ኡፓካር“ ማለት የክርሽናን ንቃት በመላው ዓለም ለማስፋፋት የበጎ ተግባር ማድረግ ማለት ነው፡፡ በአሁኑም ግዜ ይህ ከሁሉም በላይ የሆነ የበጎ ተግባር ነው፡፡ መላውንም ህብረተሰብ በፖሊቲካ በህብረተሰብ በባህል በሀይማኖት እና በሁሉም ዘረፍ ወደ ክርሽና ያቀራርባል፡፡ ክርሽናም መሀከል ነው፡፡ ይህም እርግጠኝነት ያለው ነው፡፡ እርምጃን እየተደረገ ነው፡፡ በጥረታችንም የምንቀጥልበት ከሆነ ወደ ፊት እየተራመድን እንደምንሄድ የተረጋገጠ ነው፡፡