AM/Prabhupada 0438 - የላም እበት ደርቆ እና ዓመድ እስኪሆን ድረስ ከተቃጠለ በኋላ ለጥርስ መቦረሻ አገልግሎት ላይ ይውላል፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on BG 2.8-12 -- Los Angeles, November 27, 1968

በአዩር ቬዳ ስነፅሁፍ ውስጥ የላም እበት ደርቆ ተቃጥሎ እና ወደ ዓመድ ተቀይሮ ልክ እንደ የጥርስ መፋቅያ ዱቄት እንደሚያገለግል ተገልጿል፡፡ ለጥርስ ዱቄት እንደ አንቲሴፕቲክ ባህርይ እንዳለውም ተገልጿል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ብዙ መመሪያዎች በቬዲክ ስነጽሁፎች ውስጥ ተጠቅሰዋል፡፡ አንዳንድ ግዜም የተቃረኑ ሆነው ይመስላሉ፡፡ ነገር ግን የተቃረነ ድምደማ የላቸውም፡፡ ምክንያቱም በመንፈሳዊ መድረክ ላይ ስለአሉ ነው፡፡ ልክ አባት ለልጁ እንደሚለው፡፡ “ልጄ ሆይ ይህንን ምግብ ውሰድ፡፡ በጣም ጥሩ ነው፡፡” ልጁም የአባቱን ስልጣናዊ ደረጃ ሰለሚረዳ ምግቡን ይወስዳል፡፡ ልጁም አባቱን በእምነት ያዳምዋል፡፡ እንዲህን በእርግጠኝነት ያሰላስላል “አባቴ መርዛማ የሆነ ነገር ሊሰጠኝ አይችልም፡፡“ ሰለዚህም አይኑን ጨፍኖ የተሰጠውን ይቀበላል፡፡ ይህንንም የሚያደርገው ምግቡን ንፁህ ይሁን ወይንም የተበከለ ይሁን ምንም ሳይመረምረው ነው፡፡ በዚህም ዓይነት ስልጣን እምነት እንዲኖረን ያሰፈልገናል፡፡ በመንግስት የስራ ፈቃድ ያለው ሆቴልም በመሆኑም ወደ ሆቴሉ ትገቡ ይሆናል፡፡ እዚህም ሆቴል ውስጥ ምግቡን ስትመገቡ ጥሩ መሆኑን ንጹህ መሆኑን እና ከመበከል ነጻ መሆኑን ተረድታችሁ ነው፡፡ ታድያ ይህንን ልታስቡ የምትችሉት በምን ምክንያት ነው? ይህም ስልጣን ያላቸው መሆኑን ሰለምናውቅ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ሆቴል በመንግስት እውቅና እና ፈቃድ ያለው ነው፡፡ ሰለዚህም በአገልግሎታቸው እምነት ይኖረናል፡፡ እንደዚሁም ”ሻብዳ ፕራማና“ ማለት ልክ መረጃ እንደተገኘ ማለት ነው፡፡ ይህም መረጃ በቬዲክ ስነጽሁፎች እንደ ተገለፀው ነው፡፡ ይህም ”ይህ እንዲህ ነው” ከተባለ መቀበል ብቻ ነው ያለብን፡፡ ይኅው ነው፡፡ በዚህም ስርዓት እውቀታችን ትክክለኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም የምንቀበልበት መነሻ ፍፁም ትክክለኛ በመሆኑ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ክርሽና.....ክርሽና እንደ አብዩ የመለእክት ሁሉ ጌታ ሁሉም የተቀበለው ነው፡፡ ሰለዚህ የሚነግረን ሁሉ ትክክለኛ እና ፍፁም እውነት ነው፡፡ እንደ አለ መረጃውን መቀበልም ይገባናል፡፡ አርጁናም በመጨረሻ እንዲህ ብሎ ነበረ፡፡ “ሳርቫም ኤታድ ርታም ማንዬ” (ብጊ፡ 10 14) “ውድ ክርሽና ሆይ የተናገርከውን ሁሉ ሙሉ በሙሉ እቀበለዋለሁ፡፡” መመሪያችን ይህ መሆን አለበት፡፡ ለምን ላላስፈላጊ ምርምር ብዙ ግዜ እናባክናለን? ይህም መረጃው ሁሉ ስልጣን ካላቸው የተሰጠን ከሆነ ለምን በምርምር ግዜ እናባክናለን? ሰለዚህ ግዜያችንን ላለማባከን ካላስፈላጊም ችግር እንድንድን ይህንን ባለ ስልጣን ወይንም ትክክለኛ ባለ ስልጣን መቀበል አለብን፡፡ የቬዲክ ስርዓት ይህን የመሰለ ነው፡፡ ስለዚህም ቬዳ ቭያስ እንዲህ ብሎ ነግሮናል፡፡ “ታድ ቪግናናርትሀም ሳ ጉሩም ኤቫብሁጋቼት” (ሙኡ፡ 1 2 12)