AM/Prabhupada 0440 - የማያቫዲዎች ስህተታዊ ፍልስፍና እንደሚገልፀው ዓብዩ የመላእክት ጌታ ዓብይ የሆነ ሰው አይደለም ብለው ያምናሉ፡፡

Revision as of 03:46, 24 June 2015 by Visnu Murti (talk | contribs) (Created page with "<!-- BEGIN CATEGORY LIST --> Category:1080 Amharic Pages with Videos Category:Prabhupada 0440 - in all Languages Category:AM-Quotes - 1968 Category:AM-Quotes - L...")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Invalid source, must be from amazon or causelessmery.com

Lecture on BG 2.8-12 -- Los Angeles, November 27, 1968

ፕራብሁፓድ፡ ቀጥል አገልጋይ፡ “በሽቬታሽቫታራ ኡፓኒሻድ” እንደተገለፀው አብዩ የመላእክት ጌታ በቁጥር ሊቆጠሩ የማይችሉትን ነዋሪ ነፍሳት ሁሉ የሚንከባከበው እርሱው ነው፡፡ ይህም በያሉበት ደረጃ በሚሰሩት ስራ አኳያ እና ለስራ በአላቸው አቅም የተመጣጠነ ነው፡፡ ይኅው አብዩ የመላእክት ጌታ በቅንጣፊ አካሉ በእያንዳንዳቸው ነፍሳት ልብ ውስጥ ተቀምጦ አብሮ በመኖር ላይ ይገኛል፡፡ ይህንንም አብዩ የመላእክት ጌታ በውስጥም ሆነ በውጪ ሰፍሮ እንደሚኖር ለማየት የሚችሉት መንፈሳዊ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ እነዚህም መንፈሳዊ ሰዎች ብቻ ናቸው ፍጹም የሆነውን ዘለዓለማዊ ሰላም ሊያገኙ የሚችሉት፡፡ ይህም በዚህ የተጠቀሰው የቬዳዎች ፍጹም የሆነ እውቀት ለአርጁና ሲሰጥ እናየዋለን፡፡ በዚህም መንገድ ይኅው እውቀት በዓለም ላይ ለሚገኙ ሁሉ ሲተላለፍ እናያለን፡፡ እነዚህም ሰዎች እራሳቸውን እንደ ተመረ አዋቂ አድረገው ያቀርባሉ፡፡ ነገር ግን እውቀታቸው አነስተኛ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ አብዩ ጌታም የተናገረው እንዲህ ብሎ ነው፡፡ እራሱ እና አርጁና እንዲሁም በጦር ሜዳው የሚገኙት መላው ነገስታት እያንዳንዳቸው ዘለዓለማዊ ነዋሪ ነፍሳት ናቸው፡፡ አብዩ ጌታም ለዘለዓለም እነዚህን ነዋሪ ነፍሳት የሚንከባከብ ነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ዋነኛው ጥቅስ ምንድን ነበረ? አንብበው አገልጋይ፡ ”እኔ ያልኖረኩበት ወይንም አንተ እንዲሁም የምናያቸው ንጉሶች ሁሉ ያልኖሩበት ግዜ በፍጹም የለም...(ብጊ፡ 2.12)

ፕራብሁፓድ፡ ”እኔ ያልኖረኩበት ወይንም አንተ እንዲሁም የምናያቸው ንጉሶች ሁሉ ያልኖሩበት ግዜ በፍጹም የለም....“ እዚህም እንደምንረዳው ክርሽና እየተነተነ ”እኔ አንተ ንጉሶች ....“ እያለ ይናገራል፡፡ አንደኛ ደረጃ ሰው ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ሰው፡፡ ይህም የተሟላ ነው፡፡ ”እኔ አንተ እና ሌሎች“ ክርሽናም እንዲህ ብሏል ”እኔ አንተ እነሱ ያልኖሩበት ግዜ ....“ “እነዚህም በጦር ሜዳ ላይ የተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ ያልኖሩበት ግዜ የለም፡፡” ይህም ማለት ”ከዚህ በፊት እኔም አንተም እንዲሁም ሁሉም ሰዎች እያንዳንዳቸው በሕይወት የሚኖሩ ነበሩ፡፡“ እያንዳንዳቸው፡፡ የማያቫዲ ፍልስፍና በመጨረሻ ይህ ነዋሪ ነፍስ የግል የሆነ የሰው ፍጥረት መሆኑን ይክዳሉ፡፡ ታድያ ክርሽና እንዴት እንዲህ ሊል ይችላል? "እኔ አንተ እና እዚህ የተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ ያልኖርንበት ግዜ የለም” ይህም ማለት እኔ እንደ ግለ ሰብ ኖሬአለሁ፡፡ አንተም እንደ ግለሰብ ኖረሀል፡፡ እነዚህ በፊት ለፊት ያሉት ሰዎች በሙሉ እያንዳንዳቸውም እንደ ግለሰብ ኖረዋል፡፡ ያልኖርንበት ግዜ የለም፡፡ “አሁን የአንተ መልስ ምንድን ነው? ዲናዳያል?" ክርሽና የተቀላቀልንበት ግዜ ነበረ ብሎን አያውቅም፡፡ ሁላችንም እንደ ግለ ሰብ ሆነን ግን እንኖራለን፡፡ ከዚያም ቀጥሎ እንዲህ ብሏል፡፡ ”የማንኖርበት ግዜም አይኖርም...." ”የማንኖርበት ግዜም አይኖርም...." ይህም ማለት ከዚህ በፊት እንደ ግለሰብ ኖረናል፡፡ በአሁኑ ግዜ ምንም ጥርጥር ሳይኖረው እንደ ግለ ሰብ ሆነን እየኖርን ነው፡፡ ወደፊትን ቢሆን ደግሞ ግለሰብ በመሆን መኖራችንን አናቋርጥም፡፡ ታድያ ይህ ሰብአዊ ያለመሆን ፍልስፍና ከየት ነው የመጣው? ሶስት ግዜዎች ተገልፀዋል፡፡ ከዚህ በፊት አሁን እና ወደ ፊት፡፡ አይደለም? ለዘለዓለም እኛ በግለሰብነት ነዋሪዎች ነን፡፡ በዚህ መሰረት የአብዩ ጌታ ሰብአዊ አለመሆን የእኔ ሰብአዊ አለመሆን ወይንም የእናንተ ሰብአዊ አለመሆን እድሉ የትአለ? ክርሽና በግልጽ ተናግሮታል፡፡ “እኔም አንተም እነዚህ ሁሉ እያንዳንዳቸው ንጉሶች ያልኖሩበት ግዜ የለም፡፡” ከዚህ በፊት ሕይወት አልነበረንም ማለት አይቻልም፡፡ ከዚህ ትውልድ በፊትም እያንዳንችን በግለሰብነት የኖርንበት ግዜ ነበር፡፡ በአሁኑ ግዜም እያንዳንዳችን በግለሰብነት እንደምንሞር ጥርጥር የለውም፡፡ እናንተ የእኔ ተማሪዎች ናችሁ፡፡ እኔም የእናንተ መምህር ነኝ፡፡ እናንተ የእራሳችሁ ግለሰብነት አላችሁ፡፡ እኔም እንደዚሁ የእራሴ ግለሰብነት አለኝ፡፡ ከእኔም ጋር የማትስማሙ ከሆነ ትታችሁኝ ለመሄድ ትችላላችሁ፡፡ ይህ ነው የእናንተ ግለሰብነት፡፡ ክርሽናን የማትወዱ ከሆነ በክርሽና ንቃት ላይ ላትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ ይህ ነው ግለሰብነታችሁ፡፡ ይህም ግለሰብነት የሚቀጥል ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ክርሽና የማይወዳችሁ ከሆነ የክርሽና ንቃታችሁን ሊከለክላችሁ ይችላል፡፡ ገና ለገና የመንፈሳዊ ዓለም ህግጋቶችን ተከተላችሁ እና ክርሽና የግድ እናንተን የመቀበል ግዳጅ የለውም፡፡ እንዲህ ብሎም ካሰበ “እርሱ ተንኮለኛ ነው ልቀበለው አልችልም” ካለ ሊያሰወግዳችሁ ይችላል፡፡ ሰለዚህ ክርሽናም ግለሰብ ነው፡፡ እኛም ገለሰብነት አለን፡፡ ሁላችንም ግለሰብነት አለን፡፡ ግለሰብነት የሌለበት ፍልስፍና ከየት መጣ? ይህም ሊሆን አይችልም፡፡ ክርሽናን የማታምኑ ከሆነ ደግሞ የቬዳ ስነጽሁፎችንም አታምኑም ማለት ነው፡፡ ከሁሉም በላይ አብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና እንደ አብዩ ባለስልጣን የምንቀበለው ነው፡፡ እርሱንም የማናምነው ከሆነ እንዴት አድረገን በክርሽና ንቃታችን ለመራመድ እንችላለን? ይህም የሚቻል አይሆንም፡፡ ይህም በባለ ስልጣኖች የተደመደመ ነው፡፡ ከባለስልጣኖችም መመሪያ በላይ እናንተ እራሳችሁ ምክንያታችሁን እና ሙግታችሁን ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡ በሁለት ፓርቲዎች መሀከል ስምምነት አለ ለማለት ትችላላችሁን? አይኖርም፡፡ ሂዳችሁ ማጥናት ትችላላችሁ፡፡ በመንግስት ደረጃ በቤተሰብ ደረጃ በህብረተሰብ በአገር ደረጃ ሁልግዜ ሰምምነት የሌለበት ነገር ሊኖር ይችላል፡፡ በስብሰባም ላይ ሆነ በአገር ላይ ለምሳሌ በመንግስት ስብሰባ ላይ ሁሉም የሀገሩን ፍላጐት ለማሳካት ይሞክራል፡፡ መሪው ግን ከግለሰብነቱ አንፃር ሊያይ ይችላል፡፡ አንዱ እንዲህ ብሎ ያስብ ይሆናል፡፡ “የአገሬ ደህንነት ከዚህ አንፃር ቢሆን ጥሩ ይሆናል፡፡” ይህ ካልሆነ እንዴት በፕሬዝዳንት ምርጫ ግዜ ላይ ለምን ብዙ ውድድር እናያለን? ሁሉም ሰው እንዲህ ሊል ይችላል፡፡ “አሜሪካ ኒክሰንን ይፈልጋል” ሌላው ሰው ደግሞ እንዲህ ይላል “አሜሪካ እኔን ትፈልጋለች” ታድያ ለምን ሁለት ተመራጭ? አሜሪካ እና አንተ አንድ ከሆናችሁ እና ግላዊ ሰብአዊነት ከሌለ ለምን ሁለት ተመራጭ? የኒክሰን አስተያተት የተለየ ነው፡፡ የሌላውም ተመራጭ አስተሳሰብ የተለየ ነው፡፡ ይህም የአስተያየት ልዩነት በስብሰባ ላይ በሴኔት ላይ በኮንግረስ ላይ በተባበሩት መንግስታት ሁሉ ይታያል፡፡ እያንዳንዱ የሚሟገተው የእራሱን አስተያየት ከፍ ለማድረግ ነው፡፡ ይህ ካልሆነማ ለምን በአለም ላይ የተለያዩ ባንዲራዎች እናያለን? ግለሰብነት የሌለበት የትም ቦታ ለማየት አይቻልም፡፡ ሰብዓዊነት በሁሉም ቦታ ተመስርቶ እናየዋለን፡፡ በሄድንበትም ቦታ ሁሉ ሰብአዊነት ግለሰብነት የተመሰረተ ሆኖ እናየዋለን፡፡ ይህንንም መቀበል ይኖርብናል፡፡ ምክንያታችንን ሙጉታችንን በማቅረብ ይህንን ባለ ስልጣን መቀበል ይገባናል፡፡ በዚህም መንገድ ጥያቄው ሁሉ ይመለሳል፡፡ አለበለዛ ግን አስቸጋሪ ይሆናል፡፡