AM/Prabhupada 0520 - እየዘመርን እያዳመጥን እየደነስን እና እየተደሰትን እንገኛለን፡፡ ለምን

Revision as of 13:06, 8 June 2018 by Vanibot (talk | contribs) (Vanibot #0019: LinkReviser - Revised links and redirected them to the de facto address when redirect exists)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Lecture on BG 7.1 -- Los Angeles, December 2, 1968

ይህ ቁሳዊ ዓለም የክርሽና ግዛት ነው፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ነገር የክርሽና ሀብት ነው፡፡ በዚህ ዓለም ማንም ሰው ባለ ንብረት አየደለም፡፡ እንዲህ አይነቱ አስተሳሰብ “ይህ የአሜሪካ መሬት የእኛ ነው” የሚለው አስተሳሰብ ስህተተኛ ነው፡፡ እኛ የምንም ነገር ባለ ሀብት አይደለንም፡፡ ይህም ለማንም ሰው ሁሉ ነው፡፡ ለምሳሌ ከብዙ ዓመታት በፊት ወደ 400 ዓመታት በፊት አሜሪካ የህንዶች ወይንም የቀይ ህንዶች ነበረች፡፡ በሆነ መንገድ ይህው አሜሪካ በሌሎች ተወሮ ተገኘ፡፡ ሌሎችስ ወደፊት እዚሁ አሜሪካ ውስጥ መጥተው እንደሚወሩ ማን ያውቃል? ይህ ሁሉ የውሸት ባለ ሀብትነት ነው፡፡ የሁሉም ነገር ባለ ሀብት ክርሽና ብቻ ነው፡፡ ክርሽናም እንዲህ ብሏል “ሳርቫ ሎካ ማሄሽቫራም” (ብጊ፡ 5.29) “እኔ የፕላኔቶች ሁሉ የበላዩ ተቆጣጣሪ እና ባለሀብት ነኝ፡፡” ስለዚህ የሁሉም ነገር ባለሀብት ክርሽና ነው፡፡ ክርሽና የሁሉም ነገር ባለሀብት እንደሆነ ነግሮናል፡፡ ሰለዚህ ሁሉም ነገር የእርሱ መኖርያ ቦታ እና ግዛት ነው፡፡ ይህ ቁሳዊ ዓለም የክርሽና ግዛት ከሆነ ለምን ቀይሮ መሄድ ያስፈልገናል? ሰለዚህም እንዲህ ብሎናል፡፡ “ያድ ጋትቫ ና ኒቫርታንቴ ታድ ድሀማ ፓራማም” (ብጊ፡ 15.6) ፓራማም ማለት አብይ ማለት ነው፡፡ በዚህም ድሀማ (የክርሽና ግዛት)የክርሽና መኖርያ እና የክርሽና ፕላኔቶች አሉ፡፡ ነገር ግን ይህ የቁሳዊው ዓለም ፓራማ ወይንም አብዩ መኖርያ አይደለም፡፡ እዚህ ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ መወለድ መሞት መታመም እና ማርጀት ናቸው፡፡ ነገር ግን ወደ አብዩ የክርሽና የግል መኖርያ ብትሄዱ “ጐሎካ ቭርንዳቫና ቺንታማኒ ድሀማ” (ብሰ፡5 29) እዚህም ዘለዓለማዊ ኑሮ የደስተኛ ኑሮ እና እውቀት የተሞላበት ኑሮ ይኖረናል፡፡ ይህስ እንዴት ልንደርስበት እንችላለን? እዚህም እንዲህ ተገልጿል... ክርሽና እንዲህ ብሏል “ማዪ አሳክታ ማናሀ” ይህም በቀላሉ የክርሽናን ቅርበት እና ፍቅር በመገንባት ነው፡፡ ይህ ነው ቀላሉ ስርዓት ይህ ሁሉ የምናደርገው ለምንድን ነው? በመዘመር በማዳመጥ እና በመደነስ የምንደሰተው ለምንድን ነው? ይህም ስሜት ከማይሰጡ የቁሳዊ ዓለም ስራዎች ለመራቅ እና ወደ ክርሽና ለመቅረብ ነው፡፡ ስርዓቱ ይህ ነው፡፡ ይህ የክርሽና ንቃት ነው፡፡ ሀሳባችንን ሁሌ ወደ አንድ ነገር እንዲቀርብ ማድረግ ይገባናል፡፡ ነገር ግን ሀሳባችንን ወደ ስሜት የማይሰጥ ዓለማዊ ነገር የምናቀርበው ከሆነ ይኅው ችግራችን ከትውልድ ትውልድ ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህም “ጃንማ ምርትዩ ጃራ ቭያድሂ” (ብጊ፡ 13.9) መወለድ መሞት ማርጀት እና መታመም በዚህም እንሰቃያለን፡፡ ደጋግመንም እንሰቃያለን፡፡ ሳይንሳችን ወይንም ይህ የቁሳዊ ዓለም ሳይንስ ወይንም ሌላ ነገር ሊያድነን አይችልም፡፡ ከእነዚህ መከራዎች ማንም ሰው መፍትሄ ሊሰጠን አይችልም፡፡ ነገር ግን ትክክለኛውን መፍትሄ ወይንም ዘለቄታ ያለውን መፍትሄ ወይንም ዘለዓለማዊ ሕይወትን ማግኘት ከፈለግን ለዚህ ወደ ክርሽና በፍቅር መቅረብ ይገባናል፡፡ ይህም በጣም ቀላሉ መንገድ ነው፡፡ “ማዪ አሳክታ ማናሀ ፓርትሀ ዮጋም ዩንጃን” ትክክለኛውም ዮጋ ማለት ይኅው ነው፡፡ ሌሎቹ ዓይነቶች ዮጋዎች ሁሉ ለክርሽና ንቃት ብቁ እንድትሆኑ ሊረዷችሁ የሚችሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ሁሉ ዮጋ ልምምድ የክርሽና ንቃታችሁን ለማዳበር የማትችሉ ከሆነ የምታደርጉት የዮጋ ልምድ ሁሉ ከንቱ የሆነ ልምምድ ነው፡፡ በዚህም ስርዓት ከቁሳዊው ዓለም ነፃ መሆን አይቻልም፡፡ ይህንንም ፍጥነት የሌለው የዮጋ ስርዓት ብትከተሉ በዚህ ዘመን ውስጥ ውጤታማ የሚያደርጋችሁ አይደለም፡፡ በአሁኑ ዘመንም ብቻ ሳይሆን ከ5000 ዓመታት በፊትም ይህ የማይቻል ነገር ነበረ፡፡ የጂምናስቲካችሁን ስርዓት በትጋት ትከታተሉ ይሆናል ነገር ግን ይህ ውጤታማ ሊያደርጋችሁ አይችልም፡፡ ይህም የዮጋ ስርዓት በክርሽና በመጨረሻው ምእራፍ ላይ የተገለፀው ነው፡፡ በሰባተኛው ምእራፍም ተገጿል፡፡ በስድስተኛውም ምእራፍ እንዲህ ብሎ ገልጾልናል፡፡ “ዮጊናም አፒ ሳርቬሻም” (ብጊ፡ 6.47) “አንደኛ ደረጃ ዮጊ የሚባለው ሀሳቡ ሁሉ ሁልግዜ በእኔ በክርሽና የተመሰጠው ነው፡፡” ይህ የክርሽና ንቃት ይባላል፡፡