AM/Prabhupada 0523 - “አቨታር” ማለት ከከፍተኛ ፕላኔቶች ወደ እዚህ ዓለም የሚወርድ ማለት ነው፡፡

Revision as of 06:06, 29 November 2017 by Sahadeva (talk | contribs) (Text replacement - "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->" to "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Lecture on BG 7.1 -- Los Angeles, December 2, 1968

ማድሁቪሳ፡ ፕራብሁፓድ በኢንካርኔሽን እና በአቫታር መሀከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ “አቫታር” እራሱ ኢንካርኔችን ማለት ነው፡፡ (የሰው ፎርም ይዞ መወለድ) ኢንካርኔችን በእናንተ ዲክሽነሪ ማለት “የሰው ገላን መቀበል” ነውን? ነገር ግን “አቫታር” በእርግጥ የተለያዩ አቨታሮች አሉ፡፡ አቨታር ማለት የሚመጣ ወይንም ከበላይ ወደ ምድር የሚወርድ ማለት ነው፡፡ ትክክለኛ ቃሉም “አቫታራና” ነው፡፡ ይህን ማለት የሚወርድ ማለት ነው፡፡ አቫታር ማለት ከከፍተኛ ፕላኔት ወደ ምድር የሚወርድ ማለት ነው፡፡ እነዚህም የሚወርዱት እንደ ተራ የዚህ ምድር ነፍሳት አይደሉም፡፡ የሚመጡትም ከመንፈሳዊ ዓለም ነው፡፡ “አቨታራ” ይባላሉ፡፡ የእነዚህም አቨታሮች ደረጃ የተለያየ ነው፡፡ እንደዚህም ተብለው ይታወቃሉ፡፡ ሻክትያቬሽ አቨታር ጉና አቨታር ሊላ አቨራር ዩጋ አቨታር ተብለው በተለያየ ደረጃ ይታወቃሉ፡፡ ሰለዚህ አቨታር ማለት ከመንፈሳዊው ዓለም በቀጥታ የሚመጣ ማለት ነው፡፡ ኢንካርኔሽን ማለት ደግሞ በእርግጥ ይህ የአቨታር ቃል ወደ ኢንካርኔሽን ተተርጉሞ እናየዋለን፡፡ ነገር ግን የኢንካርኔሽን ቃል ሲተረጐም አንድ ገላን የሚቀበል ማለት ይመስለኛል፡፡ አይደለምን? ሰለዚህ ኢንካርኔሽን ሁሉም ቁሳዊ ገላ ተመልሶ ሲይዝ ነው፡፡ ነገር ግን “አቨታር” የቪሽኑ (አብዩ አምላክ) አቨታር እና የአገልጋዮችም አቨታር ይኖራሉ፡፡ የተለያዩ የአቨታር ደረጃዎች አሉ፡፡ ይህንም በትንተና በጌታ ቼታንያ ትምህርቶች መፅሀፍ ውስጥ ታነቡታላችሁ፡፡ ይህም በቅርቡ እየታተመ ነው።