AM/Prabhupada 0548 - ሁሉንም ነገር ለሀሪ መስዋዕት የምታደርጉበትን ደረጃ ላይ ድረሱ፡፡



Lecture -- New York, April 17, 1969

አራድሂቶ ያዲ ሀሪስ ታፓሳ ታታሀ ኪም (ናራዳ ፓንቻራትራ) እኛ የምንሰግድለት ለጎቪንዳ ነው፡፡ “ጎቪንዳም አዲ ፑሩሻም” ይህም አብዩ የመላእክት ሁሉ ጌታ እና ሀሪ ተብሎ የሚታወቀውን ነው፡፡ የቬዲክ ስነፅሁፎችም እንዲህ ይላሉ፡፡ “አራድሂቶ ያዲ ሃሪህ” የአብዩ የመላእክት ጌታን ሽሪ ሀሪን የምትሰግድበት ደረጃ ስትደርስ “ታፓሳ ታታሀ ኪም” በዚህን ግዜ ዮጋ የጽጽት የግል ቅጣት ወይንም ለመንፈሳዊ እርማጃ ምቾትን ማጓደል አያስፈልግም፡፡ ወይንም ይህ ወይንም ያ መስዋእት ማድረግ ወይንም ባህላዊ ስርአቶችን ማድረግ ሁሉ አያስፈልግም፡፡ ሁሉንም ነገር ለሃሪ እንደ መስዋእት የምናቀርብለት ደረጃ ላይ ከደረስንም ወደ እነዚህ ችግር ውስጥ ሁሉ መግባት አያስፈልግም፡፡ "አራድሂቶ ያዲ ሀሪስ ታፓሳ ታታሀ ኪም" እና "ናራድሂቶ ያዲ ሀሪስ ታፓሳ ታታሀ ኪም" አንተ ምቾትህን በማጓደል እራስህን በፀፀት በመቅጣት መስዋእትንም በማድረግ እና ባህላዊ ስርዓቶችን ስታገናውን ትታያለህ፡፡ ነገር ግን ሀሪን የማታውቅ ከሆነ ሁሉም ነገር ዋጋ ቢስ ይሆናል፡፡ "ናራድሂቶ ያዲ ሃሪህ ናራድሂታህ" ሀሪን የምትሰግድለትም ደረጃ ካልደረስክ ይህ ሁሉ ነገር ከንቱ እና ፋይዳ የሌለው ሆኖ ይገኛል፡፡ "ታትሀ ኪም" "አንታባሂር ያዲ ሀሪስ ታፓሳ ታታሀ ኪም" ሀሪንም በውስጥህ ሁልግዜ የምታየው ከሆነ እንዲሁም ሀሪን ሁልግዜ በውስጥም በውጪም የምታየው ከሆነ "ታድ ቫንቲኬ ታድ ዱሬ ታድ" ያ ጥቅስ ምንድን ነበረ? ኢሾፓኒሻድ? ታድ አንታሬ ......ዱሬ ታድ አንቲኬ ሳርቫስያ ሀሪ በሁሉም ቦታ ያለ ነው፡፡ ስለዚህ ሀሪን በሁሉም ቦታ የሚያይ ሁሉ “አንቲኬ” በቅርቡ ወይንም በሩቅ ቦታ ሁሉ በውስጥ ወይንም በውጪ ሀሪን የሚያይ ሁሉ በሄደበት ሁሉ ከሀሪ በስተቀር ሌላ ነገር ማየትን አይችልም፡፡ ይህስ እንዴት ሊሆን ይችላል? "ፕሬማንጀና ቹሪታ ብሀክቲ ቪሎቻኔና“ (ብሰ፡5 38) ይህም ከአብዩ ጌታ ጋር በፍቅር የተዋሀደ ሲሆን ነው፡፡ ይህም ከሀሪ በስተቀር ሌላ ነገር ለማየት አይችልም፡፡ ይህ ነው የእርሱ ራእይ እንደዚህም ሁሉ ”አንታርባሂር ያዲ ሀሪ“ ሀሪ ወይንም ክርሽናን ሁልግዜ በውስጥም በውጪም ልታዩት የምትችሉ ከሆነ ”ታፓሳ ታታሀ ኪም“ ይህ ሌላው ምቾትን ማጓደል ወይንም ራስን በፀፀት መጉዳት ምን አስፈለገ? ምክንያቱም ሀሪን በማሰብ እናንተ ከፍተኛው ደረጃ ላይ ስለምትገኙ ነው፡፡ ናንታ ባሂር ያዲ ሃሪስ ታፓሳ ታታሀ ኪም ሀሪን ደግሞ በውስጥም በውጪም ለማየት የማትችሉ ከሆነ ይኅው ምቾት ማጓደላችሁ ጥቅሙ የት ላይ ነው? ሰለዚህ ጥዋት ጥዋት እንዲህ እያልን እንዘምራለን፡፡ ”ጎቪንዳም አዲ ፑሩሻም ታም አሀም ብሀጃሚ“ ሌላም ስራ የለንም፡፡ ማድረግ የሚገባንም በቀላሉ ጎቪንዳን ማስደሰት ብቻ ነው፡፡ ይህም አብዩ የመላእክት ጌታ ነው፡፡ ከዚያም ሁሉም ነገር የተሟላ ይሆናል፡፡ እርሱም የተሟላ ነው፡፡ ስግደቱም የተሟላ ነው፡፡ አገልጋዮቹም የተሟሉ ናቸው፡፡ ሁሉም ነገር የተሟላ ነው፡፡ እናመሰግናለን፡፡