AM/Prabhupada 0566 - የአሜሪካን አገር መሪዎች ይህንን ስርዓታችንን ቢረዱልን



Press Interview -- December 30, 1968, Los Angeles

ጋዜጠኛ፡ ጋንዲ ያደረገው ይህንን ነው?

ፕራብሁፓድ፡ ምን አልክ? ጋንዲ ምን ያውቃል ስለዚህ? እርሱ የፖለቲካ ሰው ነበረ፡፡ ስለ መንፈሳዊ ባህሉ ግን የሚያውቀው አልነበረም፡፡

ጋዜጠኛ፡ እኔ እንደ አነበብኩት ከሆነ እድሜው 36 ሲሆን መነኩሴ ሆኖ ነበረ፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ይሆናል በእርግጥ ትንሽ የሂንዱ የባህል ሀሳቦች ነበሩት፡፡ ያም ጥሩ ነበረ፡፡ መነኩሴነት ጀምሮ ነበር ይህም ጥሩ ነበረ፡፡ ቢሆንም ግን ጋንዲ የበለፀገ የመንፈሳዊ እውቀት አልነበረውም፡፡ አያችሁን? የፖለቲካ ሰው ወይም የመንግስት ባለስልጣን ግን ነበረ፡፡ ይኅው ነው፡፡

ጋዜጠኛ፡ አዎን፡፡ በጣም ወኔ ያለው ሰው ነበር፡፡ እንደምናየው መልሱ የሚያሞግስ ነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ በአሁኑ ሰዓት እናንተ ብትተባቡሩኝ በአገሪቱ ውስጥ ብዙ ነገር ለመለወጥ እንችላለን፡፡ ነዋሪዎች ሁሉም ደስተኛ ይሆናሉ፡፡ ሁሉም ነገር ጥሩ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ በጣም ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ይህም የምትተባበሩን ከሆነ ነው፡፡ ብዙ ሰው እየተባበረ አይገኝም፡፡ እነዚህ ልጆች ግን በሩህሩህነታቸው ወደ እኔ መጥተው ሲተባበሩኝ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ይህ እንቅስቃሴ ወደፊት እየተራመደ ይገኛል፡፡ ቢሆንም ግን እንቅስቃሴው ዝግ ብሎ የሚገፋ ይመስላል፡፡ ቢሆንም ግን የአሜሪካ መንግስት የመንግስት ባለስልጣኖች ቢመጡ እና ይህንን እውቀት ቢረዱ ተረድተውም ይህንን ስርዓት ለማስተማር ቢበቁ ይህ አገር በዓለም በጣም ደስ የሚያሰኝ አገር ሊሆን ይችል ነበር፡፡

ጋዜጠኛ፡ በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ለምን ያህል ግዜ ተሳትፈሀል?

ሀያግሪቫ፡ ለሁለት ዓመት ተኩል ያህል ተሳትፌአለሁ፡፡

ጋዜጠኛ፡ ሁለት ዓመት ተኩል? ቅር የማይልህ ከሆነ እድሜህ ስንት ነው?

ሀያግሪቫ፡ እድሜዬ 28 ነው፡፡

ጋዜጠኛ፡ 28 ዓመት በዚህን ግዜ ውስጥ ይህ እንቅስቃሴ በጣም ቀይሮሀል ለማለት ይቻላልን?

ሀያግሪቫ፡ አዎን ይህም በጥልቅ ነው፡፡ (ሳቅ)

ጋዜጠኛ፡ እንዲያው በተግባራዊ መንገድ ስናየው ስዋሚ የጠቀሰው የወሲብ ጉዳይ እንዴት ነው? ይህ ምን ያህል አስቸግሮሀል? ከዚህስ በመራቅ እንደተነጋገርነው ውጤታማ ሆኖ ያገኘኅው ነገር አለ? ምክንያቱም እኔ እንደማየው ይህ ለወጣቶች በጣም ትልቅ የሆነ ችግር ሊሆን የሚችል ነው፡፡

ሀያግሪቫ፡ እንደምናውቀው ምኞቶች አሉን፡፡ እያንዳንዳችን የተለያዩ ምኞቶች አሉን፡፡ ይህም የወሲብ ፍላጎት ከምኞቶቻችን ሁሉ በጣም ሀይል ያለው ምኞት ሆኖ ይገኛል፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አዎን

ሀያግሪቫ፡ እነዚህም ምኞቶቻችንን መስመር አስይዘናቸው እንገኛለን፡፡ መስመራቸውን ከግል ጥቅም ወደ ክርሽና አገልግሎት መርተናቸዋል፡፡

ጋዜጠኛ፡ አዎን እርሱን ተረድቻለሁ፡፡ ጥያቄዬ ግን ይህ ተጋባራዊ ውጤት አምጥቷል ወይ፡፡ ወይንም ይህ በስራ ላይ ውሏል ወይ?

ሀያግሪቫ፡ አዎን ይህ በስራ ላይ ውሏል፡፡ ቢሆንም ግን በጥብቅ መከታተልን ይጠይቃል፡፡ በጣም የሚያስቸግር ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይ በመጀመሪያ ግዜ አስቸጋሪ ነው ከዚያ በኋላ ግን በተግባር ለማዋል አያዳግትም፡፡ ይህንንም በተግባር ላይ ለማዋል ውስን መሆን ያስፈልጋል፡፡ በተግባር እንዲውልም ፍላጎት እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡

ጋዜጠኛ፡ እሺ ይህንን በትክክል ለመረዳት እፈልጋለሁ፡፡ እንደተረዳሁትም እርግፍ አድርጋችሁ የተዋችሁት ነገር ሆኖ አታዩትም፡፡

ሀያግሪቫ፡ አይደለም የተሻለ ነገር ስላገኘን ነው፡፡

ጋዜጠኛ፡ አዎን እኔም እርሱን ነው የምለው

ፕራብሁፓድ፡ የተሻለ ነገር ተቀበልን ማለት ነው፡፡

ጋዜጠኛ፡ አዎን ጥርስ ነክሶ አቆማለሁ ማለት ሳይሆን ማለት ነው፡፡ “አልነካውም አልነካውም” ሳይሆን የተሻለ አማላጭ ስላለ ነው፡፡

ሀያግሪቫ፡ ደስተኛ ለመሆን ፍላጎቱ አለን ይህንንም በቀላሉ ለመተው አይቻልም፡፡ ነገር ግን የሰው ልጅ እንደመሆናችን የተሻለ ነገር ሲገኝ የቀድሞውን ልንተወው እንችላለን፡፡ ስለዚህ አንድ ጥሩ ነገርን ለመተው ሌላ የተሻለ ነገርን ማግኘት ይጠበቅብናል፡፡