AM/Prabhupada 0567 - ይህንን ባህል ለመላ ዓለም ለማቅረብ እመኛለሁ፡፡

Revision as of 06:06, 29 November 2017 by Sahadeva (talk | contribs) (Text replacement - "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->" to "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Press Interview -- December 30, 1968, Los Angeles

ጋዜጠኛ፡ እዚህ ምን ያህል ቆይተሀል?

ፕራብሁፓድ፡ እዚህ የመጣሁት በሴፕቴምበር 1965 ነው፡፡ ከዚያም በሜይ 1967 ለቅቄ ወደ ህንድ አገር ሂጄ ነበረ፡፡ ከዚያም የዛሬ ዓመት በዲሴምበር 1967 እንደገና ተመልሼ መጣሁ፡፡

ጋዜጠኛ፡ እሺ ወደ እዚህስ ለምን ምክንያት ነበር የመጣኅው?

ፕራብሁፓድ፡ ምክንያቱም ይህንን ባሕል ለመላ ዓለም ለመስጠት ሰለፈለግሁ ነው፡፡ አሜሪካ ከሌሎች አገሮች ሲወዳደር ወደ ፊት የሄደ ነው፡፡ እዚህም አሜሪካ ውስት ይህ ባሕል ተቀባይነት ካለው ለመላው ዓለም ለማስተማር የቀለለ ይሆናል፡፡ የእኔ ሀሳብብም ይኅው ነው፡፡ ተስፋም ሰላለኝ የሚሳካም ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ወጣት አሜሪካኖች ይህንን እንቅስቃሴ ኮስተር ብለው ወስደውት ይገኛሉ፡፡ መፃህፍቶችን እና መጋዚኖችን እያተምንም እንገኛለን፡፡ እነርሱም በደንብ እየፃፉ ይገኛሉ፡፡ እኔ እድሜዬ የገፋ ሰው ነኝ፡፡ በቅርቡ ልሞት እችላለሁ፡፡ ነገርግን ሀሳቡን ተክየዋለሁ፡፡ ይህም እንደሚካሄድ ተስፋ አለኝ፡፡ ህዝቡም እንደሚቀበለው ተስፋ አለኝ፡፡ ልምምዱ ሁሉ ተካሂዷል፡፡ ጥሩ ተደርጐ ከተከፋፈለም ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንደሚኖረው ተስፋ አለኝ፡፡ እነዚህም ልጆች ወደ እኔ የመጡት ሁሉ ይህንን እንቅስቃሴ ኮስተር ብለው ተቀብለውታል፡፡ ሰለዚህ ተስፋ አለኝ፡፡

ጋዜጠኛ፡ መጽሄቱንም አይቸዋለሁ በጣምም ያምራል፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ”ወደ አብዩ መመለስ“ የሚለውን ነው?

ጋዜጠኛ፡ አዎን በጣም ቆንጆ መጽሄት ነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አመሰግናለሁ፡፡

ጋዜጠኛ፡ በጣም ቆንጆ፡፡ ለመሆኑ የት ነው የታተመው?

ፕራብሁፓድ፡ የታተመው ኒው ዮርክ ውስጥ ነው፡፡

ጋዜጠኛ፡ በኒው ዮርክ በቅርቡ የታተመውን ነበር ያየሁት .... ቆንጆ መጽሄት ነው፡፡ በእንቅስቃሴው ውስጥ በግምት ምን ያህል ተከታዮች አሉ?

ፕራብሁፓድ፡ በአሁኑ ግዜ ከመቶ ትንሽ አነስ ያለ ተማሪዎች አሉኝ፡፡ እነዚህም የጥብቅ መመሪያዎቻችንን የሚከተሉ ናቸው፡፡

ጋዜጠኛ፡ አንድ መቶ

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ይህም በተለያዩ ቅርንጫፎች ነው፡፡ በአሁኑ ግዜ ወደ 13 የሚሆኑ ቅርንጫፎች አሉኝ፡፡ አንዳንዶቹ ተማሪዎቼ በለንደን እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

ጋዜጠኛ፡ በለንደን ውስጥ?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን በጣም ጥሩ ስራ እየሰሩ ነው፡፡ ሁሉም በትዳር ላይ ያሉ ናቸው፡፡ እንዲጋቡ አደረግኋቸው፡፡ አዎን ዳርኳቸው፡፡ ሁሉም ወጣቶች ናቸው፡፡ ሁሉም ከ30 ዓመት በታች ናቸው፡፡ ትልቁ 28 ዓመቱ ነው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ 25 ወይንም 24 ቢሆኑ ነው፡፡ ከ30 ዓመት ግን አያልፉም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ልጃገረዶቹ እንደዚሁ ናቸው፡፡ ይኅው ይህችን እንደምታያት፡፡ አየሀት? እንደዚሁም እቀበላቸው እና በትዳራቸውም እንዲደሰቱ አደርጋለሁ፡፡ አስተሳሰባቸውም እንዲህ ነው፡፡ ይህን ጉራ የተሞላበት ኑሮ አይፈልጉም፡፡ በቀላሉም ለመኖር ይችላሉ፡፡ ይህም ለገላቸው በትንሹ የሚያስፈልጋቸውን ነገር በመቀበል ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን አስተሳሰባቸው ከፍ ያለ የክርሽና ንቃት ያለው ነው፡፡ ስለዚህ እኔ ተስፋ ያለኝ ከሞትኩም በኋላ ይህ እንደሚቀጥል ነው፡፡ ምክንያቱም እኔ የ73 ዓመት እድሜው የገፋ ሰው ነኝ፡፡ በማናቸውም ግዜ ልሞት እችላለሁ፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት እንቅስቃሴው እንደሚቀጥል ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡ እነዚህም ልጆች ይቀጥሉበታል፡፡ ሰለዚህም ይህ ተልእኮዬ የተሳካ ነው ብዬ እገምታለሁ፡፡ እኔም የመጣሁት ይህንኑ ሀሳብ ይዤ ነው፡፡ የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ መጀመር የሚገባው ከአሜሪካ ነው፡፡ ምክንያቱም በአሜሪካ ውስጥ ተቀባይነት ያለው ነገር በሙሉ ሰዎች የመከተል አዝማምያ ይኖራቸዋል፡፡ አሜሪካም በስልጣኔ እንደተራመደች አገር ሰለምትታይ ነው፡፡ አሜሪካ በድህነት የተጠቃች አገር አይደለችም፡፡ ስለዚህም በቀላሉ ሊረዱት እና ሊቀበሉት ይችላሉ፡፡ ከዚህም በላይ በጣም ግራ የተጋቡ ወጣቶች አሉ፡፡