AM/Prabhupada 0581 - በሽሪ ክርሽና አገልግሎት ላይ የተሰማራችሁ ከሆነ በየግዜው ሌላ አዲስ የሆነ አገልግሎት እንድታደርጉ ያበረታታችኋል፡፡



Lecture on BG 2.21-22 -- London, August 26, 1973

ያን ማይትሁናዲ ግርሀሜድሂ ሱክሀም ሂ ቱቻም (ሽብ፡ 7.9.45) ይህም የቁሳዊ ዓለም ኑሮ ማለት የወሲብ ኑሮ ማለት ነው፡፡ ይህም "ቱቻም" ወይንም የሚያፀይፍ ተብሎ ይታወቃል፡፡ አንድ ይህንን በደንብ የተረዳ ሰው ከቁሳዊው ዓለም ነፃ የወጣ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን የአንድ ሰው የወሲብ ፍላጎቱ ያልጠፋ ካልሆነ ከዚህ ዓለም ነፃ የመውጣቱ ግዜ የዘገየ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው ይህንን በትክክል ከተረዳ እና የወሲብ ፍላጎቱንም እርግፍ አድርጎ የተወው ከሆነ ምንም እንኳን በዚህ ገላ ውስጥ ቢሆንም ከዚህ ቁሳዊ ዓለም ነፃ የወጣ ነው፡፡ እንዲህም ተብሎ ይታወቃል "ጂቫን ሙክታሀ ኡችያቴ" ኢሀ ያስያ ሃሬር ዳስዬ ካርማና ማናሳ ጊራ ኒክሂላስቭ አፒ አቫስትሃሱ ጂቫን ሙክታሀ ሳ ኡችያቴ ታድያ ከዚህስ የወሲብ ፍላጎት እንዴት አድርገን ለመላቀቅ እንችላለን? "ኢሀ ያስያ ሃሬር ዳስዬ“ ይህም በቀላሉ ሽሪ ክርሽናን ለማገልገል ፍላጎት ሲኖረን ነው፡፡ በዚህ ስርዓት ከዚህ ፍላጎት ለመውጣት ይቻላል፡፡ አለበለዛ ግን የማይቻል ይሆናል፡፡ ከአብዩ ጌታ አገልግሎት ውጪ ፍላጎታችን ወደ ሌላ ነገር ከሆነ ግን ማያ ሀሳብ እና አእምሮዋችንን የሚጎትት ነገር ትፈጥራለች፡፡ ”ይህንንስ ለምን ሞክረህ አትደሰትበትም?“ ስለዚህ ያሙና አቻርያ እንዲህ ብሏል፡፡ ”ያድ አቫድሂ ማማ ቼታሀ ክርሽና ፓራራቪንዴ“ ናቫ ናቫ ራሳ ድሀማኒ ኡድያታም ራንቱም አሲት ታድ አቫድሂ ባታ ናሪ ሳንጋሜ ስማርያማኔ ብሀቫቲ ሙክሀ ቪካራሀ ሱስትሁ ኒስትሂቫናም ቻ ”ያድ አቫድሂ“ ከዚያን ግዜ ጀምሮ ”ማማ ቼታሀ“ ነፍስ እና ሕይወቴን እንዲሁም ንቃቴን ሁሉ የሎተስ እፅዋት ለመሰለው የሽሪ ክርሽና እግር አገልግሎት አበርክቻለሁ፡፡ ይህ ጥቅስ የተሰጠው በያሙና አቻርያ ነው፡፡ እርሱም የነገስታት ሁሉ ንጉስ ነበረ፡፡ እነዚህም ዓይነት ሰዎች በአጠቃላይ ከግብረገብ ውጪ የሆነ ስራ ውስጥ ገብተው ሲታዩ ይገኛሉ። (በተለይ ከወሲብ አንፃር) ነገር ግን ከግዜ በኋላ መንፈሳዊ እና ትሁት አገልጋይ ለመሆነ በቃ፡፡ ስለዚህ በእራሱ ልምድ የተማረውን እንዲህ ብሎ ይገልፅ ነበረ፡፡ "ሀሳቤን ከሽሪ በክርሽና ትሁት አገልግሎት ካሰማራሁት በኋላ" ያድ አቫድሂ ማማ ቼታሀ ክርሽና ፓዳራቪንዴ ... ናቫ ናቫ መንፈሳዊ ትሁት አገልግሎት ማለት ደግሞ በየግዜው አዲስ ነው፡፡ ተደጋጋሚ እና አሰልቺ አይደለም፡፡ በመንፈሳዊነት እራስን ያወቁ ሁሉ ክርሽናን ለማገልገል የሚችሉበትን ዘዴ ያገኙታል። አዲስ በሎጂክ የመረዳት ባህርይ "ናቫ ናቫ ራሳ ድሃማኒ ኡድያታም ራንቱም አሲት" በዚህ በቁሳዊ ዓለም ግን በስሜታዊ ደስታ ስንሰማራ አሰልቺ እና ተደጋጋሚ ይሆናል፡፡ "ፑናህ ፑናሽ ቻርቪታ" ስለዚህም ትናደዳላችሁ፡፡ ነገር ግን በክርሽና ትሁት አገልግሎት ላይ የምትሰማሩ ከሆነ በየግዜው አዲስ የሆነ መበረታታትን ታገኙበታላችሁ፡፡ ነገር ግን አሰልቺ እና ተደጋጋሚ ሆኖ ካገኛችሁት ግን ይህ ምልክት ይሆናችኋል፡፡ ይህም ማለት በትሁት መንፈሳዊ አንደበት ሳይሆን በቁሳዊ አንደበት እያገለገላችሁ ነው ማለት ነው፡፡ ይህም እንዲያው ለወጉ የሚደረግ አገልግሎት ነው ማለት ነው፡፡ ነገር ግን አዲስ የሆነ ሀይል ባገለገላችሁ ቁጥር የምታገኙ ከሆነ በዚህን ግዜ በንፁህ መንፈሳዊ አንደበት ማገልገላችሁን መረዳት ይገባችኋል፡፡ ይህ ነው ፈተናው፡፡ ያላችሁም ደስተኛነት ይጨምራል እንጂ አይቀንስም፡፡