AM/Prabhupada 0595 - የተለያየ ነገር ለማግኘት ወደ ፕላኔትዋ ጥገኛ ለመሆን ያስፈልጋችኋል፡፡



Lecture on BG 2.23 -- Hyderabad, November 27, 1972

በመንፈሳዊ ሰማያት ብራህማን ተብሎ የሚታወቀው የብርሀን ነፀብራቅ "ቺን ማትራ" ይባላል በዚህም ነፀብራቅ ውስጥ ብዙ የተለያዩ ነፍሳት አይገኙም፡፡ ይህም ብራህማን እንደ ሰማይ የሚመሰል መንፈስ የተሞላበት ብቻ ነው፡፡ በዚህ ቁሳዊ ዓለም የሚገኘውም ሰማይ ቁስ አካል ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ ሰማይ ውስጥ ብዙ የተለያየ ነገር አይታይም፡፡ ብዙ የተለያ ቁሳዊ አካላት ለማየት ግን ወደ ቁሳዊው ፕላኔት መምጣት ያስፈልጋል፡፡ በፕላኔት ውስጥ ገብቶ ከለላ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህም ወይ ወደ እዚህ መሬት ፕላኔት መምጣት ነው ወይንም ደግሞ ወደ ጨረቃ ወይንም ወደ ፀሀይ መሄድ ነው፡፡ በመንፈሳዊው ሰማያት የሚገኘው የብራህማን ነፀብራቅ የሚመነጨው ከክርሽና ገላ ነው፡፡ "ያስያ ፕራብሀ ፕራብሃቫቶ ጃጋድ አንዳ ኮቲ" (ብሰ 5 40) ልክ የፀሀይ ነፀብራቅ ከፀሀይ እንደሚመነጭ ሁሉ እና በዚህም ፀሀይ ውስጥ የፀሀይ ጌታ እንደሚኖር ሁሉ እንደዚሁም ሁሉ የመንፈሳዊ ዓለም አለ፡፡ የብራህማንም የብርሀን ነፀብራቅ አለ፡፡ ይህም ሰብአዊ ባህርይ የሌለው ነው፡፡ በዚህም በብራህማን የብረሀን ነፀብራቅ ብዙ የመንፈሳዊ ፕላኔቶች አሉ፡፡ እነዚህም መንፈሳዊ ፕላኔቶች "ቫይኩንትሀ ሎካ" ተብለው ይታወቃሉ፡፡ ከእነዚህም ሁሉ ቫይኩንትሀ ሎካዎች አብዩ መንፈሳዊ ፕላኔት ክርሽና ሎካ ተብሎ ይታወቃል፡፡ በዚህም አብይ ፕላኔት ውስጥ ከሚገኘው ከአብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና ገላም የብራህማን የብርሀን ነፀብራቅ ይመነጫል፡፡ ያስያ ብራብሀ ፕራብሀቮ ጃጋድ አንዳ ኮቲ (ብሰ 5 40) ሁሉም ነገር የሰፈረው በዚሁ በብራህማን ነፀብራቅ ውስጥ ነው፡፡ "ስቫም ክሀልቭ ኢዳም ብራህማ" በብሀገቨድ ጊታም እንዲህ ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ "ማት ስትሀኒ ሳርቫ ብሁታኒ ናሀም ቴሹ አቫስትሂታ" (ብጊ፡ 9.4) ሁሉም ነገር ያረፈው በአብዩ የመንፈሳዊ የብረሀን ጮራ ውስጥ ነው፡፡ ይህም የብራህማን ጮራ ይባላል፡፡ በዚህም በቁሳዊ ዓለም ውስጥ በቁጥር የማይገመቱ ፕላኔቶች ሁሉ ያረፉት በፀሀይ ጮራ ውስጥ ነው፡፡ የፀሀዩ ጮራ ሰብአዊነት የሌለው የፀሀይ ነፀብራቅ ወይንም ሀይል ነው፡፡ በዚህም በፀሀይ ጮራ ውስጥ በሚልዮን የሚቆጠሩ ፕላኔቶች በመንሳፈፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ በፀሀይም ጮራ ምክንያት በምድር ላይ ሁሉም ነገር እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ከአብዩ ሽሪ ክርሽናም ገላ የብራህማን ጮራ በመንፈሳዊው ዓለም ሲወጣ ይገኛል፡፡ ሁሉም ነገር ያረፈውም በዚሁ በብራህማን ጮራ ውስጥ ነው፡፡ ከዚህም የተለያዩ ሀይሎች ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ከፀሀይ ጮራ የተለያዩ ሀይላት እና ቀለማት ይገኛሉ፡፡ እነዚህም ሀይሎች በዚህ በቁሳዊ ዓለም ውስጥ ፍጥረታትን ደጋግመው እንዲፈጠሩ ያደርጋል፡፡ ይህንንም በውን የምናየው ነው፡፡ ፀሀይ በሌለበት በምእራባውያን አገሮች በረዶ ጥሎ እናያለን፡፡ በዛፍ ውስጥም የሚገኙ ቅጠላ ቅጠሎች ሁሉ ይረግፋሉ፡፡ ይህም በበልግ ግዜ ነው፡፡ የሚተርፈውም እንጨት ግንድ እና ጭራሮች ብቻ ይሆናል፡፡ በፀደይ ወቅት ግዜም ብዙ የፀሀይ ጮራ ስለሚገኝ ተክሎች ሁሉ አረንጓዴ ሆነው ይታያሉ፡፡ በዚህ ቁሳዊው ዓለም ውስጥ የፀሀይ ጮራ ብዙ ለውጥ እንደሚያመጣም ሁሉ ከአብዩ የመላእክት ጌታም የሚመነጨው የብርሀን ጮራ የሁሉም ፍጥረታት ሁሉ የመጀመሪያው መነሻ ነው፡፡ ያስያ ብራብሀ ፕራብሃቫቶ ጃጋድ አንዳ ኮቲ (ብሰ 5 40) ከዚህም ከብራህማን ጮራ መነሻ በመሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ብራህማንዳስ ወይንም ዩኒቨርሶች ሲፈጠሩ እናያለን፡፡