AM/Prabhupada 0619 - የ“ግሪሀስታ አሽራም” ወይንም የትዳር ኑሮ ዓላማ የመንፈሳዊ ህይወታችንን እንዴት አድርገን እንደምናዳብር መጣር ማለት ነው፡፡

Revision as of 13:07, 8 June 2018 by Vanibot (talk | contribs) (Vanibot #0019: LinkReviser - Revised links and redirected them to the de facto address when redirect exists)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Lecture on SB 1.7.24 -- Vrndavana, September 21, 1976

ማቲር ና ክርሽኔ ፓራታሀ ስቫቶ ቫ ሚትሆ ብሂፓድዬታ ግርሀ ቭራታናም (ሽብ፡ 7.5.30) ግርሀ ቭራታናም ማቲር ና ክርስኔ እነዚያም ቃል ገብተው እንዲህ ያሉት “እኔ በዚህ በቤተሰብ ኑሮ እፀናለሁ” “በዚህም ኑሮ እራሴን አሻሽላለሁ፡፡” ግርሀ ቭራታናም... ግርሀ ቭራታ ግርሀስትሀ እና ግርሀ ቭራታ የተለያዩ ናቸው፡፡ ግርሃስትሀ ማለት ግርሀስትሀ አሽራም (መንፈሳዊ የትዳር ኑሮ ) ማለት ነው፡፡ ይህም አንድ ሰው ከባል ከሚስት እና ከልጆች ጋር በአንድ ላይ እየኖረ ዋናው ዓላማቸው ግን የመንፈሳዊ ሕይወታቸውን ለማሻሻል ነው፡፡ ይህም የመንፈሳዊ የትዳር ኑሮ “ግርሀስትሀ አሽራም“ ይባላል፡፡ ነገር ግን የመንፈሳዊ ዓላማ የሌለው እና ስሜቶቹን ሁሉ ለማስደሰት ብቻ የሚጥር ሰው በዚህም ምክንያት ቤቱን እያሳመረ ሚስቱን እና ልጆቹን እያሳመረ ስሜቱን ለማርካት የሚኖር ሰው ”ግርሀ ቭራታ ወይንም ግርሀሜዲ“ ይባላል፡፡ በሳንስክሪት ቋንቋ የተለያዩ ትርጉም ይዘው የሚገኙ የተለያዩ ቃሎች ይገኛሉ፡፡ ግሪሀ ቭራታ የሆኑትም የክርሽና ንቃት ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ”ማቲር ና ክርስኔ ፓራታሀ ስቫቶ ቫ“ ፓራታሀ ማለት በጉሩ ትእዛዝ ወይንም በባለ ስልጣን ትእዛዝ ማለት ነው፡፡ “ስቫቶ ቫ” ስቫታሀ ማለት ድግሞ አውቶማቲካሊ ማለት ነው፡፡ አውቶማቲካሊ በትእዛዝ ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ቃል የገባው እንዲህ ብሎ ነው፡፡ ”እንዲህ ሆኜ ለመቆየት እፈልጋለሁ፡፡“ ግርሀ ቭራታናም ማቲር ና ክርስኔ ፓራታሀ ስቫቶ ቫ ሚትሆ ብሂፓድዬታ ሚትሀህ በኮንፍረንስ ሳይሆን በስብሰባ እና ውሳኔ በመስጠት ነው፡፡ ”የክርሽና ንቃት እንዲኖረን ከተፈለገ“ ይህ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ በግል የሚደረግ ነገር ነው፡፡ ለክርሽና ሙሉ ልቦና ለመስጠት የምንችለው አንድ በአንድ በግላችን ነው፡፡ ለምሳሌ በአይሮፕላን ወደ ሰማይ ስንሄድ አንድ በአንድ ነው፡፡ አንድ አይሮፕላንም ችግር ቢገጥመው ሌላ አይሮፕላን ሊያድነው አይችልም፡፡ እንደዚሁም ሁሉም አንድ በአንድ ነው፡፡ ”ፓራታሀ ስቫቶ ቫ“ እያንዳንዱ ሰው በግሉ የክርሽና ንቃትን ኮስተር ብሎ መውሰድ አለበት፡፡ ”ክርሽና ልቦናዬን እንድሰጥ ስለሚፈልግ እሰጠዋለሁ፡፡“ ክርሽናም እንዲህ ብሏል፡፡ ”ሳርቫ ድሀርማን ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ (ብጊ፡ 18.66) “ስለዚህ ልቦናዬን እሰጣለሁ፡፡” እንዲህም አይደለም “አባቴን ልቦናውን ሲሰጥ እኔም እሰጣለሁ፡፡” ወይንም “ባሌ ልቡን ሲሰጥ እኔም እሰጣለሁ፡፡” ወይንም “ሚስቴ ልቧን ስትሰጥ እኔም እሰጣታለሁ፡፡" እንዲህ የሚሆን አይደለም፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው በግሉ ልቦናውን ለክርሽና መስጠት አለበት፡፡ ከዚህም ማንም ሰው ሊገደብ አይችልም፡፡ ሊገደብ አይችልም፡፡ ”አሆይቱኪ አፕራቲሀታ“ ለክርሽና ሙሉ ልቦናህን ለመስጠት ከፈለግህ ማንም ሰው ሊገድብህ አይችልም፡፡ ”አሆይቱኪ አፕራቲሀታ ያያ አትማ ሱፕራሲዳቲ“ ይህም በግል ሲደረግ ነው፡፡ በጋራ ሲደረግ ጥሩ ነው ነገር ግን ልቦና መስጠት አንድ በአንድ በግል መደረግ የሚኖረበት ነው፡፡