AM/Prabhupada 0640 - ተክኮለኛው ሰው እራሱን እንደ ዓብዩ አምላክ በማቅረብ ሊያታልል ይችላል፡፡ ይህንንም ዓይነቱን ፊቱ ላይ መምታት ነው፡፡

Revision as of 13:08, 8 June 2018 by Vanibot (talk | contribs) (Vanibot #0019: LinkReviser - Revised links and redirected them to the de facto address when redirect exists)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Lecture on BG 2.30 -- London, August 31, 1973

“ኤይ ሩፔ” በዚህ ትእይንተ ዓለም ውስጥ በብዙ ሚልዮን እና ትሪልዮን የሚቆጠሩ ነፍሳት ይገኛሉ፡፡ እነዚህም ነፍሳት በተለያዩ እና 8,400,000 ዓይነት የፍጥረታት ፎርሞች እየተቀያየሩ ሲሞቱ ሲወለዱ ይገኛሉ፡፡ ይህም አሳዛኝ ነው፡፡ ይህም በቀላሉ የተደጋጋሚ መወለድ መሞት መወለድ መሞት ነው፡፡ ከእነዚህም ሁሉ አንድ ሰው እድሉ ከሆነ ከዚህ መከራ የመውጣት እድል ሊሰጠው ይችላል፡፡ “ጉሩ ክርሽና ፕራሳዴ ፓይ ብሀክቲ ላታ ቢጅ” በጉሩ እና በክርሽና በረከት ምክንያት የትሁት አገልግሎትን ዘር ሊያገኝ ይችላል፡፡ እንዲሁም አዋቂ ከሆነ አዋቂም መሆነ አለበት፡፡ አለበለዛ እንዴት ይህንን ዘር ሊያገኝ ይችላል? ይህንንም ዘር ውሀ የሚያጠጣው ከሆነ... ለምሳሌ ጥሩ ዘር ያገኘን ከሆነ መትከል እና ውሀ ማጠጣት ያስፈልገናል፡፡ በዚህም ስርዓት ሊያድግ ይችላል፡፡ እንደዚህም ሁሉ በትልቅ እድሉ ወደ እዚህ ወደ ክርሽና ንቃቱ የሚመጣ ሰው ሁሉ ይህንን የትሁት አገልግሎት ዘር ውሀ በማጠጣት መንከባከብ አለበት፡፡ ይህስ ውሀ ምንድን ነው? "ሽራቫና ክርታና ጃሌ ካራዬ ሴቻና“ (ቼቻ ማድህያ 19.152) ይህም ስለ ክርሽና መስማት እና መዘመርም ልክ ዘርን እንደ ውሀ ማጠጣት ይቆጠራል፡፡ ከብሀገቨታም ክፍል ውስጥም አትቅሩ፡፡ ምክንያቱም ይህ መስማት እና መዘመር የትሁት አገልግሎትን ዘር ውሀ እንደማጠጣት ነው የሚቆጠረው፡፡ ይህንንም የተደነገገ ስርዓት በማድረግ ከማዳመጥ አለመቅረት ነው፡፡ ይህም በጣም አስፈላጊ ስርዓት ነው፡፡ ”ሽራቫናም ኪርታናም ቪሽኖ (ሽብ፡ 7.5.23) ይህ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ይህም ማዳመጥ ማለት ነው፡፡ ሽራቫናም ኪርታናም ማለት ሌላ ነገርን ማዳመጥ ማለት አይደለም፡፡ አይደለም፡፡ ”ሽራቫናም ክርታናም“ እነዚህ ተንኮለኞች ይህንን “ካሊ ኪርታናም” የሚባል ነገር ፈጥረዋል፡፡ በሻስትራ ካሊ ኪርታና ሺቫ ክርታና የሚባል ነገር ሰምተን አናውቅም፡፡ ክርታና ማለት አብዩ ሽሪ ክርሽናን ማመስገን ማለት ነው፡፡ ይህ ኪርታን ይባላል፡፡ ሌላ አይነት ኪርታና የለም፡፡ ነገር ግን ይህንን “ካሊ ኪርታን” የሚባል ቃል ፈጥረዋል፡፡ ውድድር ላይ ናቸው፡፡ “ካሊ ኪርታና” የሚባል ነገር በየትኛው ሻስትራ ውስጥ ነው የሚገኘው? "ዱርጋ ኪርታናስ“ ? እነዚህ ሁሉ ስሜት የማይሰጡ ናቸው፡፡ ክርሽና ብቻ መሆን አለበት፡፡ “ሽራቫናም ኪርታናም ቪሽኖህ ስማራናም ፓዳ ሴቫናም” (ሽብ፡ 7.5.23) ክርሽና እንዲሰገድለት ያስፈልጋል፡፡ ክርሽና እንዲሰማ ያስፈልጋል፡፡ ክርሽና እንዲዘመርለት ያስፈልጋል፡፡ ክርሽና እንዲታወስ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም መንገድ በክርሽና ንቃታችሁ ወደፊት እየገፋችሁ ትመጣላችሁ፡፡ እናመሰግናለን፡፡ ሀሬ ክርሽና፡፡