AM/Prabhupada 0645 - አንድ ሰው ክርሽናን በትክክል የተረዳ ከሆነ በቭርንዳቫን ውስጥ እንደሚኖር ሰው ይቆጠራል፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on BG 6.1 -- Los Angeles, February 13, 1969

ፕራብሁፓድ፡ እሺ ጥያቄህ ምንድን ነው?

አገልጋይ፡ ክሺሮዳክሻይ ቪሽኑ ነፍሳት ባልሆኑ ፍጥረታት እንደ ድንጋይ ውስጥም ይኖራልን?

ፕራብሁፓድ፡ ምን አልክ?

አገልጋይ፡ክሺሮዳክሻይ ቪሽኑ ነፍሳት ባልሆኑ ፍጥረታት በቁሳዊ ነገሮች ውስጥም ይኖራልን?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን በአተም ውስጥም ሳይቀር፡፡

አገልጋይ፡ የሚገኘውም በአራት እጅ ባለው ፎርሙ ነውን?

ፕራብሁፓድ፡ ኦ በእርግጥ

አገልጋይ፡ የእርሱ..?

ፕራብሁፓድ፡ በየሄደበትም ቦታ ካለው ንብረቱ በሙሉ ይሄዳል፡፡ ”አኖር አኒያን ማሀቶ ማሂያን“ አብዩ አምላክ ከታላላቆች ሁሉ ታላቅ ነው፡፡ ከትንንሾችም ሁሉ ትንሹ ነው፡፡ ይህም ቪሽኑ ነው፡፡ “አንዳንታራ ስትሀ ፓራማኑ ቻያንታራ ስትሀም” (ብሰ፡5 35) ፓራማኑ ማለትም አቶም ማለት ነው፡፡ አቶምን እንዴት ትንሽ እንደሆነ ለማየት አትችሉም፡፡ አብዩ አምላክ በአቶምም ውስጥ የገኛል፡፡ በሁሉም ቦታ ይገኛል፡፡

ታማላ ክርሽና፡ ፕራብሁፓድ አንድ ግዜ እንደነገርከን ክርሽና ባለበት ቦታ ሁሉ ቭርንዳቫን አለ፡፡ እኔም ለማወቅ የፈለግሁት ክርሽና በልባችን ውስጥ የሚኖር ከሆነ በልባችን ውስጥም...

ፕራብሁፓድ፡ አዎን አንድ በዚህ ንቃት እራሱን ያወቀ ሰው በቭርንዳቫና ውስጥ እየኖረ ነው፡፡ እራሱን በንቃቱ ያወቀ ሰው ሁልግዜ በቭርንዳቫን ውስጥ የሚኖር ሰው ነው፡፡ ቼይታንያ መሀፕራብሁም እንዲህ ብሏል፡፡ አንድ ሰው ክርሽናን ተረድቶ በንቃት ላይ ያለ ሰው ሁልግዜ በቭርንዳቫን ውስጥ እየኖረ ነው፡፡ በሌላ ስፍራም አይገኝም፡፡ ልክ ክርሽና ወይንም ቪሽኑ በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ እንደሚኖረው በውሻም ልብ ውስጥም ይኖራል፡፡ ታድያ እንደ ውሻ ነው ማለት ነው? እርሱ ግን የሚኖረው በቫይኩንትሀ ነው፡፡ ምንም እንኳን በውሻው ልብ ውስጥ ቢኖርም እርሱ የሚኖረው ግን በቫይኩንትሀ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አገልጋይ ለየት ያለ ቦታ የሚኖር ይመስል ይሆናል፡፡ ይህም ከቭርንዳቫና ራቅ ብሎ የሚገኝ ሊሆን ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን የሚኖረው በቭርንዳቫና ውስጥ ነው፡፡ ይህም የተረጋገጠ ሀቅ ነው፡፡ አዎን፡፡