AM/Prabhupada 0659 - በትሁትነት እና በትጉህነት ሁሌ የምታዳምጡ ከሆነ ክርሽናን በትክክል ልትረዱት ትችላላችሁ፡፡



Lecture on BG 6.13-15 -- Los Angeles, February 16, 1969

ፕራብሁፓድ፡ ቀጥል፡፡

አገልጋይ፡ ፕራብሁፓድ እንደገለፅከው ከሆነ ክርሽና እኛ ልንረዳው የምንችለው የገላ ወገኖች የሉትም ብለሀል ይህም ማለት እኛ ልንረዳቸው የማንችላቸው ዓይኖች ወይንም ሌላ ፎርሞች የሉትም ብለሀል ታድይ እንዴት አድርገን ነው በስእል እና በሙርቲ ፎርም ያሉትን የክርሽና የገላ ክፍሎች ለመረዳት የምንችለው?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ይህንን አስተምሬአለሁ፡፡ ለዚህም ክርሽናን ማገልገል ብቻ ነው የሚገባን፡፡ በዚህም እራሱን ሊገልጽልን ይችላል፡፡ ክርሽናን ከታች ወደ ላይ በምርምር ልንረዳው አንችልም፡፡ ክርሽናን በፍቅር ስታገለግሉት እራሱን ሊገልጽላችሁ ይችላል፡፡ ይህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተገልጾልናል፡፡ ይህንንም በ10ኛው ምዕራፍ ታገኙታላችሁ፡፡ ቴሻም ኤቫኑ ካምፓርትሀም አሀም አግያና ጃም ታማሀ ናሻያሚ አትማ ብሀቫ ስትሆ ግያና ዲፔና ብሀስቫታ (ብጊ፡ 10.11) ”እነዚያም በእኔ የፍቅር አገልግሎት የተሰማሩትን ሁሉ የእኔን የደስተኛነት በረከት ለመግለጽ“ ቴሻም ኤቫኑካምፓርትሀም አሀም አግያና ጃም ታማሀ ናሽያሚ ”እውቀት በተሞላበት ብርሀን ያለቸውን የጨለማ ድንቁርና ሁሉ አጠፋላችዋለሁ፡፡“ ክርሽና በውስጣችን ይገኛል፡፡ የትሁት አገልግሎትንም ስርዓት እየተከተላችሁ ክርሽናን በትጉህነት እና በጥሞና የምትከታተሉት ከሆነ በ18ኛው ምዕራፍ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ እንደምታገኙት ”ብሀክትያ ማም አብሂጃናቲ“ (ብጊ፡ 18.55) ”አንድ ሰው እኔን በትክክል ሊረዳኝ የሚችለው ትሁት የአገልግሎት ስርዓትን በመከተል ነው“ ብሀክትያ ይህስ ብሀክቲ ምንድን ነው? ብሀክቲ ወይንም ትሁት አገልግሎት ማለትም ”ሽራቫናም ክርታናም ቪሽኖ“ (ሽብ፡ 7.5.23) ውስጥ እንደተጠቀሰው ነው፡፡ ይህም ሰለ ቪሽኑ በስማትን እና መዘመርን ነው፡፡ ይህም የብሀክቲ መጀመሪያ ነው፡፡ ስለ ክርሽናም በጥሞና እና በትሁትነት የምታዳምጡ ከሆነም ክርሽናን ልትረዱት ትችላላችሁ፡፡ ክርሽናም እራሱን ሊገልጽላችሁ ይችላል፡፡ ሽራቫናም ክርታናም ቪሽኑ ስማራናም ፓዳ ሴቫናም አርቻናም ቫንዳናም ዳሽያም ዘጠኝ ዓይነትም የተለያዩ ስርዓቶች ይገኛሉ፡፡ ሰለዚህ ቫንዳናም ፀሎት ማድረግም ከብሀክቲ ስርዓቶች አንዱ ነው፡፡ ሽራቫናም ማለት ስለ ክርሽና መስማት ማለት ነው፡፡ አሁን ለምላሌ ስለ ክርሽና ከዚሁ ከብሀገቨድ ጊታ እያዳመጥን እንገኛለን፡፡ ከዚያም ስለ እርሱ ዝና እና ቅዱስ ስም መዘመር ማለት ነው፡፡ ሀሬ ክርሽና ይህም የመጀመሪያው ነው፡፡ ሽራቫናም ኪርታናም ቪሽኑ ሽብ፡7 5 23) ቪሽኑ ማለትም ይህ ነው፡፡ ሁሉም ነገር ለቪሽኑ ነው፡፡ ሜዲቴሽኑም ለቪሽኑ ነው፡፡ ብሀክቲ ወይንም የፍቅር አገልግሎቱም ለቪሽኑ ነው፡፡ አሁን ያለ ቪሽኑ ወይንም ያለ ክርሽና የቪሽኑ ዋነኛው ፎርም በቀር ሌላ ሜዲቴሽን አያስፈልግም፡፡ ”ክርሽና ቱ ብሀገቨን ስቫያም (ሽብ፡ 1.3.28) ይህም ማለት የአብዩ የመላእክት ሁሉ ጌታ ዋነኛው ፎርም ማለት ነው፡፡ ይህንንም ስርዓት የምንከተለው ከሆነ ክርሽናን በትክክሉ እንደምንረዳው ምንም ጥርጥር የለውም፡፡