AM/Prabhupada 0661 - ከእነዚህ ልጆች በላይ የሚሆን ለክርሽና ትኩረት ያለው የለም፡፡ ምክንያቱም ሁሌ ክርሽናን በማስታወው የተሰማሩ ናቸው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on BG 6.13-15 -- Los Angeles, February 16, 1969

አንድ ሰው ትኩረቱን ወደ እኔ በማድረግ ጥልቅ ሀሳብ ውስጥ መግባት አለበት፡፡ ከሁሉም በላይ ይህ ጥልቅ ሀሳብ ባዶ ትኩረት ላይ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህም ትኩረት በቪሽኑ ላይ መሆን አለበት፡፡ ወደ ቪሽኑ ፎርም፡፡ ይህም ”ሳንክህያ ዮጋ“ ይባላል፡፡ ይህም ሳንክህያ ዮጋ በመጀመሪያ ልምምድ የተደረገበት በጌታ ካፒላዴቭ ነበረ፡፡ እርሱም የአብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና ወርዶ የመጣው አካል ነበረ፡፡ የዮጋ ሚስጢር ማለት ይህ ነው፡፡ ይህም ስርዓት ማለት የዮጋ የመቀመጥ ስርዓት የአፍንጫችንን መጨረሻ ላይ ማተኮር ቀጥ ብሎም መቀመጥን የመሳሰሉትን ስርዓት ነው፡፡ እነዚህም ስርዓቶች ሁሉ ሀሳብ እና አእምሮዋችሁን ሁሉ ወደ ቪሽኑ ፎርም ወይንም ክርሽና ላይ እንድታተኩሩ የሚረዳችሁ ነው፡፡ ”ሀሳባችሁን ወደ እኔ አድርጋችሁ አተኩሩ“ ይህም ማተኮር ማለት ወደ ክርሽና ማተኮር ማለት ነው፡፡ በዚህም በእኛ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ በጥልቅ የምናተኩረው ወደ ክርሽና ነው፡፡ ወደ ሌላ ነገር አይሆነም፡፡ ስለዚህ ከእነዚህ ልጆች በላይ የሆነ ዮጊ ሊገኝ አይችልም፡፡ ምክንያቱም እነርሱ የሚያደርጉት ስራ ሁሉ በጥልቅ ሀሳብ ወደ ክርሽና ሰለሚያተኩሩ ነው፡፡ ጠቅላላ ስራቸው ሁሉ በክርሽና አገልግሎት የተመሰረተ ነው፡፡ በአትክልት ቦታ ገብተው መሬት ሲቆፍሩ ይታያሉ፡፡ ”እዚህም ቆንጆ ፅጌረዳ ይታያል፡፡ ይህንንም ለክርሽና እናቅርብለት፡፡“ ይህም ሜዲቴሽን ተግባራዊ የሆነ ሜዲቴሽን ወይንም የጥልቅ ሀሳብ ትኩረት ነው፡፡ ”ጽጌረዳ አበቅልና ለክርሽና አቀርብለታለሁ፡፡“ በቁፋሮ ላይ እንኳን እያሉ ጥልቅ ሀሳባቸው በክርሽና ላይ የተመሰረተ ያደርጉታል፡፡ ቆንጆ ቆንጆ ምግብም እያዘጋጁ ይገኛሉ፡፡ ”ይህም ቆንጆ ምግብ ለክርሽና ይቀርብለታል፡፡“ ስለዚህ ምግብ በማዘጋቸት እንኳን ሜዲቴሽን አለ፡፡ አያችሁ? መዘመር እና ለክርሽና መደነስ ይቅርና፡፡ እነዚህም አገልጋዮች 24 ሰዓት በክርሽና ሜዲቴሽን ላይ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህም ትክክለኛ እና እውነተኛ ዮጊዎች ይባላሉ፡፡ ማንም ሰው መጥቶ እኛን መቀናቀን ይችላል፡፡ እነዚህ ልጆች ትክክለኛ ዮጊዎች ናቸው፡፡ ይህንንም ትክክለኛ የዮጋ ስርዓት እያስተማርን እንገኛለን፡፡ ይህም በግምታዊ መንገድ አይደለም፡፡ ይህም የብሀገቨድ ጊታን ስልጣናዊ ትምህርት በመከተል ነው፡፡ እኛ እራሳችን በግምት የፈጠርነው ነገር የለም፡፡ ይህም ቃል በቅዱስ መጽሀፉ ውስጥ የተጠቀሰ ነው፡፡ ይህም ሀሳባችንን እና ትኩረታችንን ሁሉ ወደ ክርሽና ወይንም ቪሽኑ ማድረግ ነው፡፡ የእነዚህም አገልጋዮች ስራ ሁሉ ወደ እዚሁ ትኩረት እንዲሄድ የተስተካከለ ነው፡፡ ይህም ከክርሽና በስተቀር ሌላ ነገር ላይ ትኩረት እንዳያደርጉ ነው፡፡ ክርሽና ክርሽና ክርሽና ሰለዚህ እነዚህ አገልጋዮች በከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሜዲቴተርስ ናቸው፡፡ ”በልብህ ውስጥ እኔን አድረገህ የሕይወትህ ሁሉ የመጨረሻው ግብህ እንሆን ልታደርገኝ ያስፈልጋል፡፡“ ስለዚህ ክርሽና የሕይወታችን እንቅስቃሴ ሁሉ ዓላማ ነው፡፡ እነዚህም አገልጋዮች እራሳቸውን ወደ ክርሽና ሎካ ፕላኔት ለማዘዋወር በመዘጋጀት ላይ ናቸው፡፡ ትክክለኛው የዮጋ ስርዓት ማለት ይህ ነው፡፡ የሚለማመዱትም ነገር ሁሉ ትክክለኛ የዮጋ ስርዓትን የተከተለ ነው፡፡ ሰለዚህም ቀጥሉበት፡፡