AM/Prabhupada 0666 - ፀሀይ ክፍላችሁ ድረስ ገብታ የምታንፀባርቅ ከሆነ ክርሽና ላባችሁ ውስጥ መግባት ያዳግተዋልን: Difference between revisions

(Created page with "<!-- BEGIN CATEGORY LIST --> Category:1080 Amharic Pages with Videos Category:Prabhupada 0666 - in all Languages Category:AM-Quotes - 1969 Category:AM-Quotes - L...")
 
m (Text replacement - "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->" to "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->")
 
Line 8: Line 8:
[[Category:Amharic Pages - Yoga System]]
[[Category:Amharic Pages - Yoga System]]
<!-- END CATEGORY LIST -->
<!-- END CATEGORY LIST -->
<!-- BEGIN NAVIGATION BAR -- DO NOT EDIT OR REMOVE -->
{{1080 videos navigation - All Languages|Amharic|AM/Prabhupada 0664 - ባዶ የሆነ ፍልስፍና ሌላ ምትሀት ነው፡፡ ባዶ የሆነ የገር ሊኖር አይችልም፡፡|0664|AM/Prabhupada 0674 - ምን ያህል መብላት እንደሚያስፈልጋችሁ አዋቂ ሁኑ፡፡ ይህም በጤንነት ብቁ ለመሆን የሚያስፈልጋችሁን ያህል ብቻ ነው፡፡|0674}}
<!-- END NAVIGATION BAR -->
<!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->
<!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->
<div class="center">
<div class="center">
Line 20: Line 23:


<!-- BEGIN AUDIO LINK -->
<!-- BEGIN AUDIO LINK -->
<mp3player>http://vaniquotes.org/w/images/690216BG-LA_Clip9.MP3</mp3player>
<mp3player>https://s3.amazonaws.com/vanipedia/clip/690216BG-LA_Clip9.mp3</mp3player>
<!-- END AUDIO LINK -->
<!-- END AUDIO LINK -->



Latest revision as of 06:07, 29 November 2017



Lecture on BG 6.13-15 -- Los Angeles, February 16, 1969

ታማላ ክርሽና፡ “የአብዩ ጌታ ግዛት በሁሉም ቦታ የሚገኙትን ሁሉ ይጨምራል፡፡ ቢሆንም ግን በመንፈሳዊው ዓለም የሚገኙት ፕላኔቶች ሁሉ ”ፓራም ድሀማ ” ወይንም ከፍተኛ መኖሪያዎች ተብለው ይታወቃሉ፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ይህም የቁሳዊ ትእይንተ ዓለምም የአብዩ ጌታ ፍጥረት ነው፡፡

ይህም እራሱ የአብዩ ጌታ መንግስት ነው፡፡ ነገር ግን አብዩ ጌታን ሰለረሳነው ይህንን በትክክል አንረዳም፡፡

“አብዩ ጌታ ሞቷል” የሚልም ስሜት አለን፡፡ ስለዚህም ሁሉም ነገር ልክ እንደ ሲኦል ሆኖ ይገኛል፡፡

ነገርግን አብዩ ጌታን የምንቀበል ከሆነ ይህም ዓለም እራሱ የመንፈሳዊ ዓለም ይሆናል፡፡ ይህም አውቶማቲካሊ ነው፡፡

ስለዚህ ይህ ቤተ መቅደስ የመንፈሳዊ አለም እንጂ የቁሳዊ ዓለም አይደለም፡፡

ይህም ከቁሳዊ ዓለም በላይ ሆኖ ይገኛል፡፡ ቀጥል፡፡

“አንድ የበለፀገ ዮጊ ክርሽናንም በትክክል የሚረዳ ዮጊ"

"ልክ ጌታ ክርሽና በዚህ ጥቅስ ውስጥ እንደገለፀው”

“ይኅው ዮጊ ዘላቂ ሰላም ሊያገኝ እና በመጨረሻም ወደ ታላቁ መንፈሳዊ ዓለም ወደ ”ጎሎካ ቭርንዳቫን“ ተብሎ ወደሚታወቀው የክርሽና ሎካ ወይንም ፕላኔት ለመሄድ ይችላል፡፡

”በብራህማ ሰሚትሀ እንዲህ ብሎም ተጠቅሷል፡፡ ምንም እንኳን አብዩ ጌታ ጎሎካ ቭርንዳቫን ተብሎ የሚታወቀው መኖርያው ውስጥ የሚኖር ቢሆንም

በሁሉም ቦታ እንደ ብራብማን የሚገኝ እና በእያንዳንዱም የፍጥረታት ልብ ውስጥ እንደ ፓራማትማ ቁጭ ብሎ የሚገኝ ነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አዎን፡፡ ክርሽና በጎሎካ ቭርንዳቫና መኖሪያው ብቻ ነው የሚገኘው የምትሉ ከሆነ ታድያ እንዴት አድርጎስ በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ ክርሽና ሆኖ ለመኖር ይችላል? በብራህማ ሰሚትሀ ግን እንዲህ ብሎ ተጠቅሷል፡፡ ስለዚህም ስልጣን ካላት እናታችን መስማት ይኖርብናል፡፡ ብራህማ ሰሚታም እንደሚገልጽልን “ጎሎካ ኤቫ ኒቫሳቲ አክሂላትማ ብሁታሀ (ብሰ፡5 37) ምንም እንኳን በጎሎካ ቭርንዳቫን ውስጥ የሚኖር ቢሆንም ክርሽና በሁሉም ቦታ የሚገኝ ነው፡፡ ክርሽና በሁሉም ቦታ ያለ ነው፡፡ የተለያዩ ምሳሌዎችም ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ፀሀይ ለምሳሌ ከ90,000,000 ሚልዮን ማይልስ በላይ ሆና እና ከእኛ ርቃ ትገኛለች፡፡ ነገር ግን በክፍላችንም ውስጥ ትገኛለች፡፡ አለበለዛ እንዴት ፀሀይ መጣች ለማለት እንችላለን፡፡ “ኦ ፀሀይ እዚህ መጥታለች” እንደዚሁም ሁሉ ፀሀይ ክፍላችሁን ጥሳ ገብታ የምትገኝ ከሆነ ለክርሽና በልባችሁ ጥሶ መግባት እና በየክፍሉ እና በየኮርነሩ ለመገኘት ምን ያዳግተዋል? ምንም ጥቅም የለሽ ነውን? እርሱ በሁሉም ቦታ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ይህንን ልንረዳው ይገባናል፡፡ እንዴት በሁሉም ቦታ ተሰራጭቶ እንደሚገኝ መገንዘብ ይገባናል፡፡ ቀጥል፡፡

ታማላ ክርሽና፡ “ማንም ሰው ወደ መንፈሳዊው ዓለም ለመሄድ ወይንም ወደ አብዩ ጌታ መኖርያ በራሱ ጥረት ለመሄድ አይችልም” “ያለ አብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና ትክክለኛ የመረዳት አቅም እንዲሁም እንደ ቪሽኑ ያሉትን የክርሽና አካላት በትክክል ሳንረዳ ወደ መንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ለመግባት አይቻልም፡፡” “ስለዚህም አንድ ሰው በክርሽና ንቃት ላይ በትክክል የተሰማራ ከሆነ እንደ ትክክለኛ ዮጊ ይቆጠራል፡፡” ምክንያቱም ሀሳቡ ሁሉ በክርሽና እንቅስቃሴዎች ሁልግዜ የተመሰጠ ሰለሆነ ነው፡፡ በቬዳ ስነጽሁፎችም ይህንን እንማራለን፡፡“ ”የአብዩን የመላእክት ሁሉ ጌታን በመረዳት ብቻ አንድ ሰው ከዚህ ከተደጋጋሚ ትውልድ እና ሞት ሊያርግ ይችላል፡፡“ በሌላም አነጋገር የዚህ የዮጋ ስርዓት ብቁነት የሚታወቀው አንድ ሰው ከቁሳዊው ዓለም ኑሮ የተላቀቀ ሆኖ ሲታይ ነው፡፡ ይህም ብቁነት በማጂካዊ ንግግሮች ወይንም በጂምናስቲክ ትሁት የሆኑ ሰዎችን እያታለሉ መኖር አይደለም፡፡ እናመሰግናለን፡፡ ይኅው ነው፡፡