AM/Prabhupada 0766 - "ሽሪማድ ብሀገቨታም" ተብሎ የሚታወቀውን ቅዱስ መጽሀፍ በማንበብ ብቻ ፍጹም ደስተኛ ለመሆን ትችላላችሁ፡፡ ሰለዚህ ይህንን ስርዓት ተከተሉ፡፡

Revision as of 13:09, 8 June 2018 by Vanibot (talk | contribs) (Vanibot #0019: LinkReviser - Revised links and redirected them to the de facto address when redirect exists)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Lecture on SB 1.13.12 -- Geneva, June 3, 1974

ፕራብሁፓድ፡ “የመሀራጅ ዩዲስቲር ለአጎቱ ድህትራስትራ አክብሮት እጅ መንሳቱ በፍላጎቱ የተደረገ እና የተጠበቀም ነበር፡፡” ነገር ግን ይህንን የመሰለ አቀባበል ከንጉስ ድህትራስትራ የሚያስመኝ አልነበረም፡፡ ይህንንም አቀባበል የተቀበለው ሌላ ምርጫ ስላልነበረው ነው፡፡ ቪዱራም የመጣው ንጉስ ድህትራስትራን በመንፈሳዊ እውቀት ለማስተማር እና ካለበት ደረጃ ከፍ ሊያደርገው ስለፈለገ ነው፡፡ አንዱ በመንፈሳዊ ሕይወት የበለፀጉት ሰዎች ሀላፊነት የወደቁትን ነፍሳት ካሉበት ደረጃ ከፍ ማድረግ ነው፡፡ ቪዱራም የመጣበት ዓላማ ይህ ነበረ፡፡ እነዚህም የመንፈሳዊ ትምህርቶች በጣም የሚያረኩ በመሆናቸው ንጉስ ድህትራስትራን እያስተማረ እያለ ሌሎችም የቤተሰቡ አባሎች ቀርበው ቪዱራን ማዳመጥ ጀመሩ፡፡ እያንዳንዳቸውም በጥሞና ቪዱራን ማዳመጥ ጀመሩ፡፡ የመንፈሳዊ ንቃት መንገድም እንዲህ ነው፡፡ መልእክቱ እውቅና ባለው ሰው ሲነገር በጥሞና መደመጥ አለበት፡፡ ይህም በሰመመን ላይ ባለው ውስን ነፍስ ላይ ለውጥ ያስመጣለታል፡፡ በተከታታይም በማዳማጥ ወደ ትክክለኛው የራስን የማወቅ ደረጃ ላይ ለመድረስ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ሽራቫናም (ማዳመጥ) በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ "ሽራቫናም ኪርታናም ቪሽኑ ስማራናም ፓዳ ሴቫናም“ (ሽብ፡ 7.5.23) በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ይህ ስርዓት መካሄድ ይኖርበታል፡፡ አሁን እኛ ብዙ መጻህፍትን አትመናል፡፡ ይህንንም መጻህፍት ማንበብ ነው ያለብን፡፡ ዮጌሽቫራ ፕራብሁ መጽሀፍቶችን ለማንበብ ሁሌ ዝግጁ ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም ድቮቲ መጽሀፍ ማንበብ እና ሌሎችም ማዳመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ በጣም አስፈላጊ ነው። ”ሽራቫናም” ደጋግማችሁ ባነበባችሁ ቁጥር እድገት ታደርጋላችሁ፡፡ ብዙ መፃህፍቶች አሉን፡፡ የታተሙትን መጻህፍት ሁሉ ማንበብ ትችላላችሁ፡፡ ልክ እኛም በቀን አንድ ጥቅስ እንደምንማረው፡፡ ብዙ ጥቅሶች አሉን፡፡ በነዚህም ጥቅሶች ለ50 ዓመት መወያየት ትችላላችሁ፡፡ እነዚህም መፃህፍቶች ታትመዋል፡፡ መቀጠል ትችላላችሁ፡፡ ምንም አይነት ሌላ ግምጃ ቤት አያስፈልጋችሁም፡፡ ስለዚህ ይህንን ልምምድ ማድረግ አለባችሁ፡፡ ጊዜያችሁንም አታባክኑ፡፡ በተቻላችሁ መጠን ሰለ ብሀገቨታም የመንፈሳዊ መልእክት ለማዳመጥ ሞክሩ፡፡ ”ያድ ቫይሽናቫናም ፕሪያም“ (ሽብ፡ 12.13.18) በዚህም እንዲህ ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ ”የሽሪማድ ብሀገቨታም በቫይሽናቫዎች ወይም በድቮቲዎች በጣም የተወደደ ቅዱስ መጽሀፍ ነው፡፡“ በቭርንዳቫን ከተማ ውስጥ ድቮቲዎች ሁሌ ሽሪማድ ብሀገቨታምን ሲያነቡ ይገኛሉ፡፡ ይህም ሕይወት እና ነፍሳቸው ነው፡፡ አሁን እኛም 6 ቮልዩም አትመናል፡፡ ሌሎችም በመታተም ላይ ናቸው፡፡ ምን ያህል? 8 ቮልዩም በመታተም ላይ ናቸው፡፡ ሰለዚህ በቂ የሆኑ መፃህፍቶች አሏችሁ፡፡ ሰለዚህ ማንበብ አለባችሁ፡፡ ”ሽራቫናም ኪርታናም ቪሽኑ“ (ሽብ፡ 7.5.23) ዋነኛው ስራችን ይኅው ነው፡፡ ይህም ንፁህ የትሁት አገልግሎት ነው፡፡ ለ24 ሰዓትም ለማዳመጥ እና ለመዘመር ግዜያችንንም ሁሉ ለመሰዋት ስለማንችል የተለያዩ ፕሮግራሞችን አዘጋጅተናል፡፡ አለበለዛ ግን ሽሪማድ ብሀገቨታም በጣም ደስ የሚያሰኝ በመሆኑ ምንም ነገር እንኳን እያደረጋችሁም ቢሆንም ማዳመጥ ትችላላችሁ፡፡ ወይንም በማናቸውም ቦታ ሽሪማድ ብሀገቨታምን በማዳመጥ ደስተኛ ለመሆን ትችላላችሁ፡፡ ስለዚህ ይህንን ልምድ አድርጉ፡፡ መንፈሳዊ ሕይወታችሁንም የተሳካ አድርጉ፡፡ እናመሰግናለን፡፡ ድቮቲስ፡ ጃያ ፕራብሁፓድ