AM/Prabhupada 1061 - የብሀገቨድ ጊታ ዋና ዋና የትምህርት ርዕሶች በአምስት ፍፁም እውነታዎች የተመረኮዙ ናቸው፡፡



660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

የብሀገቨድ ጊታ ዋና ዋና የትምህርት ርዕሶች በአምስት ፍፁም እውነታዎች የተመረኮዙ ናቸው፡፡ ጌታ ክርሽና ወደእዚህ ዓለም ላይ የወረደው "ያዳ ያዳሂ ድሀርማስያ ግላኒር ብሀቨቲ" (ብጊ፡ 4 7) የሰው ልጅ የዘነጋውን የሕይወት ዓላማ እንደገና ለማስታወስ እና ለማቋቋም ነው፡፡ አንድ ሰው የሕይወትን ዋና ዓላማውን ወይንም መሰረታዊ ተልእኮ ሲዘነጋ ይህ “ድሀርማ ግላኒህ” ወይንም የሰው ልጅ የሕይወቱ ዓላማ መረበሽ ይባላል፡፡ በዚህም ሁኔታ ላይ ከብዙ ሰዎች መሀከል መንፈሳዊ ንቃት ያደረባቸው ወይንም ከብዙ ሰዎች መሀከል ትክክለኛውን የሕይወታችንን ዓላማ መንፈስ የተረዱ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ይህም ብሀገቨድ ጊታ የተገለፀው ለእነዚህ ዓይነት ሰዎች ነው፡፡ ሁላችንም በድንቁርና ነብር እየተሳደድን በመዋጥ ላይ እንገኛለን፡፡ ቢሆንም ግን ጌታ ፈጣሪ ለሁሉም ነፍሳት በተለይም ለሰው ፍጡር በጣም ሩህሩህ ነው፡፡ በተለይ ለሰው ልጅ ይህንን ብሀገቨድ ጊታን አስተማረ፡፡ ይህም አርጁናን እንደጓደኛው አድርጎ በመምረጥ ነው፡፡ አርጁናም የጌታ ክርሽና ጓደኛ በመሆኑ ከድንቁርና የፀዳ ሰው ነበረ፡፡ ነገር ግን ለወደፊቱ ትውልድ ጥቅም እና አርአያነት አርጁና በኩሩክሼትራ የጦርነት ሜዳ ላይ ድንቁርና እንደተሞላበት ሰው ሆኖ ቀረበ፡፡ አርጁናም ለጌታ ክርሽና ስለ ህይወት ችግሮች ሁሉ ጥያቄውን አቀረበ፡፡ ይህም እድል ጌታ ክርሽና የህይወታችን እና የኑሮአችን ተልእኮው ምን መሆን እንዳለበት ለወደፊቱ ትውልድ ለማስተማር እንዲችል አበቃው፡፡ በዚህ መንገድ የሰው ልጅ እንዴት እየኖረ የህይወቱን የውጤት ተልእኮ ማሳካት እንደሚችል ትንተናውን አቀረበ፡፡ ይህም የሰው ልጅ ሕይወት እና ተልእኮው የተሳካ እንዲሆን ለማድረግ ነው፡፡ የብሀገቨድ ጊታ ትምህርት በአምስት የተጠቃለሉ መሰረታዊ እውነቶችን እንድንረዳ ይጠይቃል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የፍጥረት ሁሉ ጌታ የማንነት ሳይንሳዊ እውነታ ተተንትኗል፡፡ ይህም ቀዳማዊ የሆነው የአብዩ ጌታ ጥናት ነው፡፡ ይህም የአብዩ ጌታ የሳይንሳዊ እውነታ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተተንትኗል፡፡ ከዚያም የጂቫዎች ወይንም የነፍሳት ሁሉ መሰረታዊ ደረጃቸው ምን እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ኢሽቫራ እና ጂቫ፡፡ አብዩ ጌታ ኢሽቫራ ወይንም ዋናው ተቆጣጣሪ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ኢሽቫራ ማለት በቁጥጥር ስር የሚያውለን ጌታ ማለት ሲሆን ጂቫ ወይንም ነፍሳት ማለት ደግሞ በቁጥጥር ስር የሆኑ ማለት ነው፡፡ ጂቫ ወይንም ነፍሳት ማለት ደግሞ ኢሽቫራ ወይንም ተቆጣጣሪ ናቸው ማለት ሳይሆን በቁጥጥር ስር የሆኑ ማለት ነው፡፡ በአርቲፊሻል መንገድ “እኔ ነፃ ነኝ ወንም የሚቆጣጠረኝ የለም” ብለን ብናስብ ይህ አስተሳሰብ የአዋቂ አስተሳሰብ ሊሆን አይችልም፡፡ ማናቸውም ነፍሳት በሁሉም ደረጃ ላይ በቁጥጥር ስር የሚገኙ ናቸው፡፡ ቢይንስ ቢያንስ በዚህ በውስን የቁሳዊ ዓለም ሕይወታችን ላይ በቁጥጥር ስር ውለን እንገኛለን፡፡ በዚህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ የኢሽቫራ ወይንም የአብዩ ጌታ ዋና ተቆጣጣሪነት ተተንትኖ ተገልጿል፡፡ ይህም ስለ አብዩ ጌታ ዋና ተቆጣጣሪነት እና ስለ ነፍሳት በቁጥጥር ስር ስለሚገኙት ተገልጿል፡፡ እንዲሁም ስለ “ፕራክርቲ” ወይንም ስለ ቁሳዊው ዓለም ተፈጥሮ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም ስለ ግዜ ወይንም ስለ መላው ትእይንተ ዓለም የመኖርያ ግዜ ተገልጿል። ይህም በውናችን ስለሚታየው የትእይንተ ዓለም ነው፡፡ የሚቆይበት ግዜ እና ስለ ዘለዓለማዊው ግዜም ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም ስለ “ካርማ” ወይንም እንቅስቃሴ እና ውጤቱ ምን እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የትእይንተ ዓለም ፍጥረታት ሁሉ ብዙ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች የተሞላባቸው ሆነው ይገኛሉ፡፡ በተለይ የትእይንተ ዓለም ፍጥረታት ሁሉ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ከብሀገቨድ ጊታ ኢሽቫራ ወይንም አብዩ ጌታ ማን እንደሆነ እንማራለን፡፡ ጂቫዎች ወይንም ነፍሳቶች ማን እንደሆኑ እና ፕራክርቲ ወይንም የትእይንተ ዓለም ምን እንደሆነ እንረዳለን፡፡ እንዴትስ በግዜ ቁጥጥር ስር እንደሚውል እና እንቅስቃሴዎቹ እና ውጤቶቹ ምን እንደሆኑ ተገልጿል፡፡ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ እነዚህ ከአምሰቱ ርእሰ ትምህርቶች ተገልፀዋል፡፡ ታላቁ የጌታ አካል ወይንም ብራህማን ዋናው ተቆጣጣሪ ወይንም ፓራም አትማ ከሁሉም በላይ ወይንም አብይ ደረጃ ላይ ያለ መሆኑን ይገልፃል፡፡ አንድ ሰው በፈቀደው ስም ዓብይ ጌታን ሊጠራው ይችላል፡፡ መገንዘብ የሚገባን ግን አብይ ተቆጣጣሪ እንዳለ ነው፡፡ ይህም አብይ ተቆጣጣሪ ከሁሉም በላይ ነው፡፡ ነፍሳትም በዓይነታቸው ልክ እንደ አብዩ ጌታ ይመሰላሉ፡፡ ይህም ማለት ልክ እንደ አብዩ ጌታ በዓይነት የተመሰሉ ናቸው ማለት ነው፡፡ አብዩ ጌታ የመላ ትእይንተ ዓለምን ወይንም የቁሳዊ ዓለማትን ሁሉ በቁጥጥር ስር የሚያውል ነው፡፡ ወደፊት በሚገኙትም የብሀገቨድ ጊታ ምዕራፎች ውስጥ የቁሳዊው ዓለም እንዴት ከዓብዩ ጌታ ቁጥጥር ውጪ ሊኖር እንደማይችል ተገልጿል፡፡ መላው የትእይንተ ዓለም በአብዩ ጌታ መመርያ ስር እንደምትንቀሳቀስ ተገልጿል፡፡ “ማያ ድህያቅሼና ፕራክርቲ ሱያቴ ሳ ቸራቸራም” (ብጊ፡9 10) አብዩ ጌታ እንዲህ ብሏል፡፡ ”መላው የቁሳዊው ዓላማት ሁሉ የሚንቀሳቀሱት በእኔ መመርያ ስር ነው፡፡” ማያድህያቅሼና “በእኔ አስተዳዳሪነት”