AM/Prabhupada 1065 - በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ገላችን እኛ (ነፍሳችን) እንዳልሆንን መረዳት ይገባናል፡፡



660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ገላችን እኛ (ነፍሳችን) እንዳልሆንን መረዳት ይገባናል፡፡ በዓለማዊ አንደበት ተበክለን በምንገኝበት ግዜ ሕይወታችን ውስን ሆኖ ይገኛል፡፡ ይህ ውስን የሆነ ደረጃ ይባላል፡፡ በዚህም ግዜ ሀሰተኛ አንደበት ይዘን እንገኛለን፡፡ ንቃቱ በስህተት የተመሰረተ ሰው ነፍስ ወይንም ሕይወት ከቁሳዊ ዓለም ንጥረ ነገሮች የተፈጠረች ናት ብሎ ያስባል፡፡ ይህም በስህተት የተመሰረተ አንደበት ወይንም ህልውና ይባላል፡፡ "ያስያትማ ቡድሂ ኩናፔ ትሪ ድሆቱኬ" አንደ ሰው አስተሳሰቡ ሁሉ ከዚህ ዓለማዊ ገላ አንፃር ብቻ የተመሰረተ ከሆነ የራሱን መንፈሳዊ ማንነት በግልጽ ሊረዳው አይችልም፡፡ ብሀገቨድ ጊታም የሚያስተምረው ከዓለማዊ እና ከገላ አንፃር የተመሰረተውን የአርጁናን ስህተተኛ አስተሳሰብ ወደ ትክክለኛ መንገድ ለመምራት ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም ሰው ከዚህ ከተሳሳተ "የቁሳዊው ገላ እኔ ነኝ" ብሎ ከሚያስብ ስህተተኛ አስተሳሰብ ነፃ መውጣት አለበት፡፡ በመንፈሳዊ መንገድ ንቃቱን አዳብሮ ከዚህ ቁሳዊ ዓለም ነፃ ለመውጣት የሚፈልግ ሁሉ ይህ ዋናው ስራው መሆን ይኖርበታል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ይህ የምናየው ቁሳዊው ገላችን ክዳናችን እንጂ እኛ እንዳልሆንን መረዳት ይገባናል፡፡ ሙክቲ ወይንም ነፃነት ማለት ከዓለማዊ ባህርይ ነፃ መሆን ማለት ነው፡፡ ሙክቲ ማለት ከዚህ ከቁሳዊ ዓለም እና ከተበከለው ዓለማዊው ኑሮ ነፃነት አግኝቶ ወደ ንጹህ መንፈሳዊ ንቃት ያለው ዓለም መሸጋገር ማለት ነው፡፡ በሽሪማድ ብሀገቨታም ቅዱስ መፅሀፍም ውስጥ የነፃነት ትርጉሙ በግልፅ ተጠቅሷል፡፡ ሙክቲር ሂትቫንያትሀ ሩፓም ስቫሩፔና ቭያቫስትሂቲህ (ሽብ 2 10 6) ስቫሩፔና ቭያቫስትሂቲህ ሙክቲ ማለት ከዚህ ከተበከለ ከቁሳዊው ዓለም ንቃት ነፃ መሆን ማለት ነው፡፡ ከዚያም አልፎ በንፁህ መንፈሳዊ ንቃት ውስጥ መሰመጥ ማለት ነው፡፡ የብሀገቨድ ጊታም መልእክት ሁሉ የሚያስተምረን ይህንኑ ንፁህ የሆነ ንቃታችንን እንዴት ለማነቃቃት እንደምንችል ነው፡፡ ይህም በብሀገቨድ ጊታ በመጨረሻው ምዕራፍ ውስጥ ተጠቅሶ ይገኛል። በዚህም ምዕራፍ ውስጥ ክርሽና ለአርጁና ይህንን ንፁህ የሆነውን አንደበት አግኝቶ እንደሆነ ሲጠይቀው ይገኛል፡፡ መንፈሱ ያልተረበሸ እና ንፁህ ደረጃ ላይ መሆኑን ጠይቆት ነበረ፡፡ ይህም ንፁህ መንፈስ ማለት አብዩ ጌታ የሚፈልገውን ተከትሎ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይህም ንፁህ መንፈስ ይባላል፡፡ የንፁህ ሰው መንፈስ ገለፃውም ሆነ ድምደማው ይኅው ነው፡፡ ይህም ንፁህ መንፈስ በውስጣችን ያለ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን የጌታ ቁራሽ አካል እንደመሆናችን በዚህ ቁሳዊ ዓለም ላይ መንፈሳችን ተበርዞ ይገኛል። በቁሳዊው ዓለም መንፈስ እና ባህርዮች ስንጠቃ እንገኛለን፡፡ ቢሆንም ግን አብዩ የመላእክት ጌታ ታላቅ እንደመሆኑ በእነዚህ ዓለማዊ ባህርዮች ሊጠቃ አይችልም፡፡ ይህ ነው በዓብዩ ጌታ እና በእኛ መሀከል ያለው ልዩነት፡፡ ይህ ንቃትስ ምንድነው? ይህም ንቃት “እኔ” የሚል ነው፡፡ “እኔ” የምንለውስ ማንን ነው? በዓለማዊ መንፈስ ተጠቅተን እያለን “እኔ” ማለት ለማደርገው ነገር ሁሉ እኔ ጌታ ነኝ ማለት ነው፡፡ ይህም ንፁህ ያልሆነ ዓለማዊ መንፈስ ነው፡፡ ይህም ”በዚህ ዓለም የድካሜ ሁሉ ተደሳች እኔ ነኝ“ ብሎ የሚያስብ ነው፡፡ የዚህም መላ የቁሳዊው ዓለም ነፍሳት ሁሉ በዚህ በተሳሳተ መንፈስ ሲንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ ይህም ”እኔ የዚህ ዓለም ጌታ እና ፈጣሪ ነኝ ብሎ በማሰብ ነው፡፡“ ይህም ዓለማዊ መንፈስ ሁለት ዓይነት መንፈስ ወይንም አስተሳሰብ ይዞ ይገኛል፡፡ አንደኛው ”እኔ በዚህ ዓለም ውስጥ ፈጣሪ ነኝ፡፡“ ብሎ የሚያስብ ሲሆን ሌላው ደግሞ ”እኔ የልፋቴ ሁሉ ተደሳች ነኝ፡፡“ ብሎ የሚያስብ አንደበት ነው፡፡ ቢሆንም ግን ፈጣሪ እና የጥረታችን ሁሉ ተደሳች መሆን የሚገባው አብዩ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ነፍስ ደግሞ የዓብዩ አምላክ ቁራሽ አካል እንደመሆኗ ፈጣሪ ወይንም የድካሙ ተደሳች ልትሆን አትችልም፡፡ ነገር ግን አገልጋይ ናት፡፡ ልክ በማሽን እንደምናየው እያንዳንዱ የማሽኑ ወገን ለማሽኑ አገልጋይ ነው፡፡ ወይንም የገላችንን አፈጣጠር ላይ በማተኮር ይህንን ለመረዳት እንችላለን፡፡ በገላችንም ላይ እጆችን እግሮችን እና ዓይኖችን እናገኛለን፡፡ እነዚህም ሁሉ የገላ ወገኖች ተባብረው ሲሰሩ እናያቸዋለን፡፡ ነገር ግን እነዚህ የገላ ወገኖች ሁሉ የልፋታቸው ዋነኛ ተደሳቾች አይደሉም፡፡ ተደሳቹም ሆድ ነው፡፡ እግር ከአንድ ወገን ወደ ሌላ ወገን ሲዘዋወር ይታያል፡፡ እጆችም ሲለቅሙ እና ምግብንም ሲያዘጋጁ እናያቸዋለን፡፡ ጥርሶችም ሲፈጩ እንዲሁም ሌሎችም ሁሉ እንዲሁ ሲያገለግሉ ይታያሉ፡፡ ሆድንም ለማስደሰት በስራ ተሰማርተው ይታያሉ፡፡ ምክንያቱም ሆድ መላ ገላን ለማጠንከር ዋነኛው አካል ነው፡፡ ሁሉም ነገር ተሰርቶ ለሆድ መሰጠት አለበት፡፡ ፕራኖፓሀራክ ቻ ያትሄንድሪያናም (ሽብ 4 31 14) ለምሳሌ የዛፍን ስር ወሀ በማጠጣት መላ ዛፉን አረንጓዴ ለማድረግ ይቻላል፡፡ ወይንም ሆድን በማስደሰት ጤነኛ ለመሆን እንችላለን፡፡ የገላ ክፍሎች ማለትም እጆች እግሮች ዓይኖች ጆሮዎች ጣቶች ሁሉም የገላችን አካላት የሆድን ፍላጎት እስከአሟላን ድረስ ጤነኛ ልናደርጋቸው እንችላለን፡፡ እንደዚህም ሁሉ አብዩ የመላእክት ጌታ የስራችን ሁሉ ተደሳች መሆን ይገባዋል፡፡ እኛ ደግሞ ታዛዥ ነፍሳት መሆን እንደሚገባንም ሁሉ እና የዓብዩ ፈጣሪ አምላክ ፍጥረታት እንደመሆችንም ሁሉ እርሱን ማገልገል ይገባናል፡፡ ይህም አገልግሎታችንም እራሳችንን ይረዳናል ያስደስተናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ጥሩ ምግብ ከጣቶቻችን ተይዞ ይሆናል፡፡ ጣቶችም እንዲህ በማለት ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ ”ለምን ይህንን የመሰለ ምግብ ለሆድ እንሰጣለን?" "እራሳችን ይህንን ምግብ እንደሰትበት“ ብለው ቢያስቡ ይህም ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም ጣቶች በዚህ ሊደሰቱ አይችሉም፡፡ የምግቡንም ውጤት ጣቶቻችን ሊደሰቱበት ከፈለጉ ይህንን ምግብ ጣቶች ለሆድ ማበርከት አለባቸው፡፡