AM/Prabhupada 1071 - ወደ ዓብዩ ጌታ የምንቀርብ እና የምንተባበር ከሆነ ሁሌ ደስተኞች እንሆናለን፡፡

Revision as of 13:11, 8 June 2018 by Vanibot (talk | contribs) (Vanibot #0019: LinkReviser - Revised links and redirected them to the de facto address when redirect exists)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

ማስታዋስ የሚገባንም ነገር ቢኖር የክርሽናን ቅዱስ ስም ስንጠራ ይህ ቅዱስ ስም አንድ ሌላ የሀይማኖት ወገኖች የጌታ ስም ብቻ እንዳልሆነ መረዳት ይገባናል፡፡ “ክርሽና" ማለት የላቀውን ደስታ የሚጥት ማለት ነው፡፡ በቬዳ ስነጽሁፎችም እንደተገለፀው ዓብዩ ጌታ ደስታዎች ሁሉ የተከማቹበት ኩሬ ነው፡፡ እያንዳንዳችን ደስታ በመፈለግ ላይ እንገኛለን፡፡ ”አናንዳማዮ ብህያሳት“ (ቬዳንታ ሱትራ 1 1 12) ነፍሳትም ሁሉ እና ዓብዩ ጌታም ጭምር ሙሉ ንቃት ያለን በመሆናችን ይህ ንቃታችን ደስታን እንድንፈልግ ይገፋፋናል፡፡ ደስታ ዓብዩ ጌታ ለዘለዓለም ደስተኛ ነው፡፡ ስለዚህ ወደ ዓብዩ ጌታ ሁሌ የምንቀርብ እና የምንተባበረው ከሆነ በእርሱም ማህበር የምንገኝ ከሆነ ሁሌ ደስተኛ እንሆናለን፡፡ ዓብዩ ጌታ ቅዱስ ታሪኩን ሊያሳየን ወደ እዚህ ቁሳዊ ዓለም በቭርንዳቫን ውስጥ መጥቶ ደስተኝነቱን ያሳየናል፡፡ ዓብዩ ጌታ ክርሽና በቭርንዳቫን ውስጥ በነበረም ግዜ ከእረኛ ጓደኞቹ የነበረው እንቅስቃሴ ከልጃገረድ ጓደኞቹ እና ከመላ ጓደኞቹ ጋር እንዲሁም ከቭርንዳቫን ነዋሪዎቹ የነበረው እንቅስቃሴ እና በልጅነቱ የነበረው የእረኝነት እንቅስቃሴ እነዚህ የጌታ ክርሽና እንቅስቃሴዎች ሁሉ ሙሉ ደስታን የሚሰጡት ነበሩ፡፡ መለ የቭርንዳቫን ወይንም የቭርንዳቫን ነዋሪዎች በሙሉ በፍቅር የሚቀርቡት ነበሩ፡፡ ከክርሽና በቀር የሚያውቁት ነገር አልነበረም፡፡ ዓብዩ ክርሽና አባቱንም እንኳን ቢሆን አንዳንድ ነገሮችን እንዳያደርግ የሚከለክለው ግዜ ነበረ፡፡ ይህም አባቱ ናንዳ ማሀራጅ ኢንድራ የተባለውን መልዓክ እንዳያመልክ ነበረ፡፡ ይህም ነዋሪዎቹ ከዓብዩ የመላእክት ጌታ በስተቀር ሌላ ማንንም መላእክት እንዳያመልኩ ለማስተማር ነበረ፡፡ ምክንያቱም የሕይወታችን ዓላማ በመጨረሻው ወደ ዓብዩ ጌታ ለመመለስ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ ይህም የዓብዩ ጌታ መንፈሳዊ መኖርያ በብሀገቨድ ጊታ በ 15ኛው ምዕራፍ ውስጥ ተጠቅሷል፡፡ “ና ታድብሀሳያቴ ሱርዮ ና ሻሻንኮ ና ፓቫካሀ” “ያድ ጋትቫ ና ኒቫርታንቴ ታድ ድሀማ ፓራማም ማማ” (ብጊ 15.6)

የዚህም የመንፈሳዊ እና ዘለዓለማዊ ሰማይ ገለፃ ሰማይ ብለን ስንጠቅስ እንደ ቁሳዊው ዓለም ዓይነት ሰማይ ሊመስለን ይችላል፡፡ ስለዚህ ሰማይ ሲባል ፀሀይ፣ ጨረቃ፣ ኮከብ፣ እያልን እናስብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ዓብዩ ጌታ እንደሚገልፀው በመንፈሳዊው ሰማይ ውስጥ ለብርሀን ፀሀይ አያስፈልግም፡፡ “ና ታድ ብሀሳያቴ ሱርዮ ና ሻሻንኮ ና ፓቫካሀ” (ብጊ 15.6) ወይንም ደግሞ በዚሁ ዘለዓለማዊ ሰማይ ውስጥ ጨረቃ እንዲኖር አያስፈልግም፡፡ “ና ፓቫካሀ” ማለት ምንም ዓይነት የኤሌክትሪክ መብራት፣ እሳት ወይንም የሚያበራ ነገር አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም የመንፈሳዊው ሰማይ በብራህማ ጆይቲ ብርሀን ለዘለዓለም የበራ ነው፡፡ “ብራህማጆይቲ ያስያ ፕራብሀ” (ብጊ 5 40) ይህም ከዓብዩ ጌታ ገላ የሚመነጭ ብርሀን ማለት ነው፡፡ ሰዎች ወደ ሌላ ፕላኔቶች ለመሄድ በሚጥሩበት በአሁኑ ግዜ የዓብዩ ጌታን የመንፈሳዊ መኖርያ ለመረዳት አዳጋች አይደለም፡፡ ይህ የዓብዩ ጌታ መኖርያ የሚገኘው በመንፈሳዊው ሰማይ ውስጥ ሲሆን “ጐሎካ” ተብሎም ይታወቃል፡፡ ይህም በብራህማ ሰሚታ ቅዱስ መፅሀፍ ውስጥ ደስ በሚል ሁኔታ ተዘርዝሮ ተፅፏል፡፡ “ጐሎካ ኤቫ ኒቫሳቲ አክሂላትማ ብሁታህ” (ብሰ 5 37) ምንም እንኳን ዓብዩ ጌታ ለዘለዓለም በመንፈሳዊው ዓለም በጐሎካ የሚኖር ቢሆንም በቸርነቱ በዚህም በቁሳዊው ዓለም ውስጥ ሊደረስበት በመቻሉ “አክሂላአትማ ብሁታሀ” ተብሎ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ዓብዩ ጌታ ወደ እዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ በመምጣት ዋና መንፈሳዊ ፎርሙን በመግለጽ ያሳየናል፡፡ “ሳት ቺት አናንዳ ቪግራሀ” (ብሰ 5 1) ይህም እኛ ምን ሊመስል እንደሚችል እንዳንገምት ነው፡፡ እራሱ በምድር ላይ ስለሚወርድ ምንም ዓይነት ግምት ማድረግ አያስፈልገንም፡፡