AM/Prabhupada 1074 - በዚህ ዓለም የሚደርስብን መከራ ሁሉ ከቁሳዊው ገላችን ጋራ የተያያዘ ነው፡፡



660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ እንዲህ ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ ”አቭያክቶ ክሳራ ኢቲ ኡክታስ ታም አሁህ ፓራማም ጋቲም“ ”ያም ፕራፕያ ና ኒቫርታንቴ ታድ ድሀማ ፓራማም ማማ“ (ብጊ፡ 8.21) ”አቭያክታ“ ማለት ያልተገለፀ ማለት ነው፡፡ በአንድ ወገን ያለው የቁሳዊው ዓለም እንኳን አልተገለፀልንም፡፡ ያሉን ስሜቶቻችን ፍፁም ብቁ ስላልሆኑ ምን ያህል ኰኰበች እንኳን እንዳሉ ልንረዳ አንችልም፡፡ ወይንም ምን ያህል ፕላኔቶች እንዳሉ ልንረዳ አንችልም፡፡ በእርግጥ የቬዲክ ስነፅሁፎችን በማንበብ ስለ እነዚህ ፕላኔቶች መረዳት እንችላለን፡፡ ልናምነው ወይንም ላናምነው እንችላለን ቢሆንም ግን ለማወቅ የሚያስፈልጉን ፕላኔቶች በሙሉ በቬዲክ ስነፅሁፍ ውስጥ በተለይ በሽሪማድ ብሀገቨታም ውስጥ በዝርዝር ተገልፀዋል፡፡ ከዚህም ከቁሳዊው ትእይንተ ዓለም ባሻገር የመንፈሳዊው ዓለም እንዲህ ተብሎ ተገልጿል፡፡ ”ፓራስ ታስማት ቱ ብሀቮ ንዮ“ (ብጊ፡ 8.20) ይህም ”አቭያክታ“ ወይንም ያልተገለፀልን መንፈሳዊ ዓለም ታላቁ መድረሻችን ነው፡፡ ወደ እዚህም ወደ ታላቁ መድረሻችን ወይንም ቤተመንግስት ለመድረስ አንድ ሰው መጓጓት እና መመኘት አለበት፡፡ ወደ እዚህም ታላቅ ቤተመንግስት አንድ ሰው ከደረሰ በኋላ ”ያም ፕራፕያ“ ወደ እዚህ ታላቅ ቤተ መንግስት ለመድረስ ከቻለ ”ና ኒቫርታንቴ“ ይህ ሰው ወደ እዚህ መከራ ወደ ተሞላበት ቁሳዊ ዓለም ተመልሶ አይመጣም፡፡ የዘለዓለማዊው የዓብዩ ጌታ መኖርያ የሆነው ዓለም ወይንም አንዴ ተሂዶ ወደ እዚህ ዓለም የማንመለስበት ቦታ የእኛ የዘለዓለማዊ መኖርያችን ነው፡፡ ጥያቄዎችም ሊነሱ ይችላሉ፡፡ ወደእዚህ ታላቁ የዓብዩ ጌታ መኖርያ ለመሄድ የሚቻለው በምን ዓይነት መንገድ ነው? ይህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተገልጾልናል፡፡ ይህም በ8ኛው ምእራፍ በጥቅሶች 5, 6, 7, 8 ተዘርዝሯል፡፡ ይህም እንዴት ወደ ዓብዩ ጌታ ወይንም ወደ ዓብዩ ጌታ መኖርያ ለመመለስ እንደምንችል ነው፡፡ የተገለፀውም እንዲህ ተብሎ ነው፡፡ “አንታ ካሌ ቻ ማም ኤቫ ስማራን ሙክትቫ ካሌቫራም” “ያህ ፕራያቲ ሳ ማድ ብሀቫን ያቲ ናስቲ አትራ ሳምሻያህ” (ብጊ፡ 8.5)

“አንታ ካሌ” በሕይወታችን መጨረሻ ላይ ወይንም በሞት ግዜ፡፡ “አንታ ካሌ ቻ ማም ኤቫ” አንድ ሰው በሞት አፋፍ ላይ እያለ ክርሽናን የሚያስታውስ ከሆነ “ስማራን” ክርሽናን ካስታወሰ ይህም በሞት አፋፍ ላይ እያለ እና መሞቻው ሲደርስ የክርሽናን ፎርም የሚያስታውስ ከሆነ ይህንንም የክርሽናን ፎርም እያስታወሰ ይህንን ቁሳዊ ገላ በሞት የሚለቅ ከሆነ በእርግጥ የመንፈሳዊውውን ዓለም ሊደርስበት ይችላል፡፡ “ማድ ብሀቫም” “ብሀቫም” ማለት መንፈሳዊ ዓለም ማለት ነው፡፡ “ያህ ፕራያቲ ሳ ማድ ብሀቫም ያቲ” “ማድ ብሀቫም” ማለት የዓብዩ ጌታ መንፈሳዊ ባህርይ ማለት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም እንደገለፅነው ዓብዩ የመላእክት ጌታ “ሳት ቺድ አናንዳ ቪግራሀ” ነው፡፡ (ብሰ፡5 1) ዓብዩ ጌታ ፎርም አለው፡፡ ይህም ፎርም ዘለዓለማዊ ነው፡፡ “ሳት” እንዲሁም ይህ ፎርም ሙሉ እውቀት የሞላበት ነው፡፡ “ቺት” እንዲሁም ሙሉ ደስታ የሞላበት ነው፡፡ “አናንዳ” አሁን ይህንን ገላችንን ከዚህ ጋር ማመሳከር እንችላለን፡፡ ይህ ገላ “ሳት ቺት አናንዳ ቪግራሀ” ነወይ? አይደለም፡፡ ይህ ገላችን “አሳት” ዘለዓለማዊ ያልሆነ ነው ማለት ነው፡፡ ዘለዓለማዊ መሆን ሲገባው በሞት የተጠመደ ጊዜያዊ ገላ ነው፡፡ “አንታቫንታ ኢሜ ዴሀ” (ብጊ፡ 2.18) ብሀገቨድ ጊታ እንደሚያስተምረን ይህ ገላ “አንታቫንታ” ወይንም ወዳቂ እና ጠፊ ነው፡፡ “ሳት ቺት አናንዳ” ሳት ወይንም ዘለዓለማዊ ከመሆን ፋንታ “አሳት” ወይንም የተቃራኒ ነው፡፡ ቺት ከመሆንም ፋንታ ወይንም እውቀት የሞላበት ከመሆን ድንቁርና የሞላበት ሆኖ ይገኛል፡፡ ስለ መንፈሳዊው ዓለም እንኳን ምንም ዓይነት እውቀቱ የለንም፡፡ በዚህ በምንኖርበት ቁሳዊ ዓለም እንኳን እያለን ሙሉ እውቀት ስለ እዚህ ዓለም የለንም፡፡ ስለ ብዙ ነገሮች በዚህ ምድር ላይ የማናውቀው አለ፡፡ ስለዚህ ይህ ገላ ድንቁርና የተሞላበት ነው፡፡ ሙሉ እውቀት የሞላበት ገላ ከመሆን ይልቅ ድንቁርና የሞላበት ሆኖ ይገኛል፡፡ ይህ ቁሳዊ ገላ የሚደመሰስ እና የሚጠፋ ነው፡፡ ድንቁርናም የተሞላበት ነው፡፡ ደስታም የሌለው ነው፡፡ “ኒር አናንዳ” ደስታ የተሞላበት ከመሆን ይልቅ ድንቁርና የሞላበት ሆኖ ይገኛል፡፡ በዚህ ዓለም ውስጥ የሚፈራረቁብን መከራዎች ሁሉ የሚመነጩት ከዚሁ ከቁሳዊው ዓለም ገላችን ነው፡፡