AM/Prabhupada 1075 - በሕይወታችን ውስጥ በምናደርገው ስራ የሚቀጥለው ሕይወታችን ምን ለመሆን እንደሚችል እየወሰንን እና እያዘጋጀን እንገኛለን፡፡

Revision as of 13:12, 8 June 2018 by Vanibot (talk | contribs) (Vanibot #0019: LinkReviser - Revised links and redirected them to the de facto address when redirect exists)
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

ዓብዩ ጌታ እንዲህ ብሏል “አንታ ካሌ ቻ ማም ኤቫ ስማራን ሙክትቫ ካሌቫራም” (ብጊ 8.5) አንድ ሰው በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ዓብዩ የመላእክት ጌታን የሚያስታውስ ከሆነ ልክ ሕይወቱ እንዳለፈች “ሳት ቺት አናንዳ” ፎርም የያዘ መንፈሳዊ ገላውን ያገኛል፡፡ (ብሰ፡ 5 1) ይህንንም ቁሳዊ ገላችንን በሞት ተለይተን እንዴት ሌላ አዲስ ቁሳዊ ገላ በዚህ ምድር ውስጥ እንደምናገኝም የተደነገገ ስርዓት አለ፡፡ አንድ ሰው ሊሞት የሚችለው በሚቀጥለው ሕይወቱ ምን ዓይነት ገላ መረከብ እንዳለበት ከተወሰነ በኋላ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የሚወሰነው በዓብዩ ጌታ ባላስልጣኖች ነው፡፡ ለምሳሌ ልክ በሰራነው ስራ አኳያ ወይ ወደ ከፍ ያለ ስልጣን እንሸጋገራለን ወይንም ደግሞ ወደ ዝቅ ያለ ደረጃ እንወርዳለን፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እንደየስራችን የወደፊት ሕይወታችን ይወሰናል፡፡ በዚህ ሕይወታችን የምናደረገው ወይም የምንሰራው ስራ ሁሉ የሚቀጥለው ሕይወታችን ምን እንደሚሆን ይወስናል፡፡ የሚቀጥለው ሕይወታችን ምን መሆን እንደሚችል የሚወስነው በዚህ ሕይወታችን ውስጥ በምንሰራው ስራ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ሕይወታችን ወደ አብዩ የመላእክት ጌታ ቤተ መንግስት ለመሄድ የምንዘጋጅ ከሆነ ልክ ይህንን ቁሳዊ ገላችንን በሞት እንደተለየነው ወደ መንፈሳዊ ዓለም እናመራለን፡፡ ዓብዩ ጌታ እንዲህ ብሏል “ያህ ፕራያቲ” አንድ ወደ መንፈሳዊ ዓለም የሚመለስ ሰው “ሳ ማድ ብሀቫም ያቲ” (ብጊ 8.5) ማድ ብሀቫም ይህ የፀደቀ ሰው ልክ የዓብዩ ጌታን የመሰለ ገላ ይኖረዋል፡፡ ወይንም ልክ እንደ ዓብዩ ጌታ ዓይነት መንፈስ ይኖረዋል፡፡ ከዚህ ቀደም እንደጠቀስነው የተለያዩ መንፈሳውያን አሉ፡፡ “ብራህማቫዲ፣ ፓራማትማቫዲ እና ድቮቲ ወይንም አገልጋዮች” በመንፈሳዊው ዓለም ወይንም በብራህማ ጆይቲ ውስጥ የተለያዩ መንፈሳዊ ፕላኔቶች አሉ፡፡ እነዚህም በቁጥር ሊገመቱ የማይችሉ ፕላኔቶች ናቸው፡፡ ይህም ቀደም ብሎ ተገልጾልናል፡፡ የእነዚህም የመንፈሳዊ ፕላኔቶች ቁጥር በዚህ ቁሳዊ ትእይንተ ዓለም ውስጥ ከሚገኙት ህዋዎች ቁጥራቸው በጣም ከፍ ያለ ነው፡፡ ይህ ቁሳዊ ዓለም “ኤካምሼና ስትሂቶ ጃጋት” (ብጊ 10.42) ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህ ቁሳዊ ዓለም የመላ መንፈሳዊ ዓለም አንድ አራተኛ ብቻ ነው፡፡ ሶስት አራተኛው የመንፈሳዊው ዓለም ነው፡፡ በዚህም በአንድ አራተኛው ትእይንተ ዓለም ውስጥ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ትእይንተ ዓለሞች ይገኛሉ፡፡ ይህንንም በአሁኑ ግዜ በተግባር እያየን እየሰማነው ነው፡፡ በአንድ ህዋ ውስጥ በብዙ ሚሊዮን እና ቢሊዮን የሚቆጠሩ ፕላኔቶች ይገኛሉ፡፡ እንደዚህም ሁሉ በመላው የቁሳዊው ዓለም ትእይንተ ዓለም ውስጥ በብዙ ሚሊዮን እና ቢሊዮን የሚቆጠሩ ፀሀዮች ኮከቦች እና ጨረቃዎች ይገኛሉ፡፡ ይህም ሆኖ ይህ ጠቅላላው የቁሳዊው ትእይንተ ዓለም የመንፈሳዊው ዓለም አንድ አራተኛ ብቻ ሆኖ ይገኛል፡፡ ሶስት አራተኛው ትእይንተ ዓለም ግን የሚገኘው በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ ነው፡፡ ይህ “ማድ ብሀቫም” ታላቁ “ብራህማን” ተብሎ የሚታወቀው የዓብዩ ጌታ ጮራ ውስጥ ለመደባለቅ የሚፈልገው በዚህ በብራህማ ጆይቲ ጮራ ውስጥ ተደባልቆ ይቀራል፡፡ ማድ ብሀቫም ማለት ብራህማ ጆይቲ የሚባለው የዓብዩ ጌታ መንፈሳዊው የብረሀን ጮራ እና በጮራው ውስጥ የሚገኙ መንፈሳዊ ፕላኔቶችም ናቸው፡፡ ቢሆንም ግን ከዓብዩ ጌታ ጋር በአንድነት ለመሆን የሚፈልጉት ትሁት የጌታ አገልጋዮች ወደ ዓብዩ ጌታ ያለበት የመንፈሳዊ ቫይኩንታ ፕላኔቶች ውስጥ ይገባሉ፡፡ በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ በቁጥር ሊተመኑ የማይችሉ ቫይኩንትሀ ፕላኔቶች አሉ፡፡ በእነዚህም ፕላኔቶች ውስጥ ዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና ይገኝባቸዋል፡፡ እዚህም “ናራያና” ተብሎ የሚታወቀውን እና አራት እጆች ያሉትን ፎርም ይዞ በተለያየ ስም እየተጠራ ይኖራል፡፡ እነዚህም ስሞች “አኒሩድሀ፣ ማድሀቫ፣ ጐቪንዳ” የመሳሰሉት ናቸው፡፡ አራት እጆች ያሉት "ናራያና" ተብሎ የሚታወቀው የዓብዩ ጌታ ፎርም በቁጥር የማይተመን ስሞች አሉት፡፡ አንዱ “ማድ ብሀቫም” ተብሎ የሚታወቀው የመንፈሳዊ ፕላኔትም እዚሁ መንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ማናቸውም መንፈሳውያን በሞት አፋፍ ላይ እያሉ ይህን የብራህማ ጆይቲ የዓብዩ ጌታን ፎርም የሚያስታውሱ ወይንም “ፓራማትማ” ተብሎ የሚታወቀውን በልባችን የሚገኝ ጌታ የሚያስተውል ወይንም ዓብዩ የመላእክት ጌታ ሽሪ ክርሽናን የሚያስታውስ ወደ መንፈሳዊው ዓለም ለመጓዝ ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን ዓብዩ ጌታን በቀጥታ ያገለግሉ የነበሩ ትሁት አገልጋዮች ብቻ ወደ ቫይኩንትሀ ፕላኔቶች ወይንም ወደ ዓብዩ ጌታ የላቀው መኖርያ ወደ ጐሎካ ቭርንዳቫን ለመሄድ ይችላሉ፡፡ ዓብዩ ጌታም እንዲህ ብሏል “ሃህ ፕራያቲ ሳ ማድ ብሀቫም ያቲ ናስቲ አትራ ሳምሻያህ” (ብጊ 8.5) ይህንንም ማንም ሰው መጠራጠር አይገባውም፡፡ እምነት እንዲጐልበትም አያስፈልግም፡፡ ይህ ነው ጥያቄው፡፡ ብሀገቨድ ጊታን እድሜ ልካችንን በማንበብ ላይ እንገኛለን፡፡ ቢሆንም ግን ሽሪ ክርሽና አንድ እኛ በሀሳባችን ያልተቀበለነውን ነገር ሲናገር ወድያው ውድቅ እናደርገዋለን፡፡ ብሀገቨድ ጊታን የማንበብ ስርዓቱ ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ ልክ አርጁና እንዳለው መሆን አለበት፡፡ “ሳርቫም ኤታም ርታም ማንዬ” “አንተ የተናገርከውን ነገር በሙሉ እቀበለዋለሁ፡፡” እንደዚህም ሁሉ እኛም ማዳመጥ ይገባናል፡፡ ዓብዩ ጌታም እንዲህ ብሎናል፡፡ በሞት አፋፍ ላይ እያለን ማናቸውም የሚያስታውሰኝ ሰው ምንም እንኳን እንደ ብራህማን፣ ፓራማትማ ወይንም እንደ ዓብዩ ጌታ ቢሆንም ወደ መንፈሳው ዓለም መግባቱ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ይህ ምንም ጥርጥር የሚያስፈልገው አይደለም፡፡ በዚህም ምንም ዓይነት እምነት እንዲጐለን አያስፈልግም፡፡ የዚህም ስርዓቱ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ቀርቦልናል፡፡ አጠቃላይ ህግጋቱ ሁሉ ተጠቅሶልናል፡፡ ይህም እንዴት አንድ ሰው ወደ መንፈሳዊው ዓለም ለመግባት እንደሚችል ነው፡፡ ይህም ዓብዩ የመላእክት ጌታን በሞት አፋፍ ላይ እያለን በማስታወስ ብቻ ነው፡፡ ይህም የአጠቃላዩ ስርዓት ተገልጾልናል፡፡ “ያም ያም ቫፒ ስማራን ብሀቫም ትያጅአቲ አንቴ ካሌቫራም” “ታም ታም ኤቫይቲ ኮንቴያ ሳዳ ታድ ብሀቫ ብሀቪታሀ” (ብጊ 8.6)