AM/Prabhupada 1077 - ዓብዩ ጌታ ፍፁም እንደመሆኑ በእራሱ እና በቅዱስ ስሙ መሀከል ምንም ዓይነት ልዩነት አይገኝም፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


660219-20 - Lecture BG Introduction - New York

ሽሪማድ ብሀገቨታም “ብሀስዮ ያም ብራህማ ሱትራናም” ተብሎ ይታወቃል፡፡ የቬዳንታ ሱትራም የተብራራ ገለፃ እንደሆነም ይታወቃል፡፡ ወደ እነዚህም የቬዲክ ስነፅሁፎች ህሊናችንን ብናተኩር ”ታድ ብሀቫ ብሀቪታሀ ሳዳ“ ”ሳዳ ታድ ብሀቫ ብሀቪታ“ (ብጊ፡ 8.6) አንድ ሰው እነዚህን መፃህፍቶች በማንበብ ሲሰማራ ልክ ዓለማዊው ሰው በዓለም የሚገኙትን መፃህፍቶች ሁሌ እንደሚያነብ ለምሳሌ እንደ ጋዜጣ መፅሄቶች ልብ ወለድ እና ታሪኮች ወዘተ ወይንም ሌላ የሳይንስ ወይንም የፍልስፍና መፅሀፍቶች እነዚህ ሁሉ የተለያዩ አስተሳሰቦችን የሚያፈልቁ ናቸው፡፡ ስለዚህም ይህንን የማንበብ አቅማችንን ወደ ቬዲክ መፃህፍቶች ላይ ብናተኩር ይህም ቭያሳዴቭ በትህትናው ወደ አቀረበልን መፃህፍት ትኩረት ብናደርግ የሞት አፋፍ በደረስን ወቅት ላይ ዓብዩ ጌታን ለማስታወስ ምንም ሊያዳግተን አይችልም፡፡ በዓብዩ ጌታም የተገለፀልን መንገድ ይኅው ብቻ ነው፡፡ ይህም መገለፅ ብቻ ሳይሆን እውነትን የተመረኮዘ ነው፡፡ “ናስትዪ አትራ ሳምሻያ ህ: (ብጊ፡ 8.5) ያለ ምንም ጥርጥር ማለት ነው፡፡ ”ታስማት“ አብዩ ጌታ እንደገለፀውም ”ታስማት ሳርቫሹ ካሌሹ ማም አኑስማራ ዩድህያ“ (ብጊ 8.7) አርጁናንም እንዲህ ብሎ መክሮታል ”ማም አኑስማራ ዩድህያ ቻ“ እንዲህም ብሎ አልመከረውም ”እኔን ብቻ አስታውስ እንጂ አሁን ያለብህን ሀላፊነት መወጣት የለብህም“ ብሎ አልነገረውም፡፡ ይህ አልነበረም የተነገረው፡፡ ዓብዩ ጌታ ተግባራዊ ያልሆነ ነገር አይመክርም፡፡ በዚህ ቁሳዊ ዓለምም ውስጥ ገላችንን ለመንከባከብ እንኳን ስራ መስራት ይገባናል፡፡ ይህም ስራ በአራት ዓይነት የሕብረተሰብ ክፍሎች የተመደበ ነው፡፡ እነዚህም ብራህማና፣ ክሻትርያ፣ ቫይሻ እና ሱድራ ተብለው ይታወቃሉ፡፡ በአእምሮዋቸው የላቁ ሰዎች ስራቸው ከሌላው የተለየ ነው፡፡ አስተዳደር ውስጥ ያሉ የሕብረተሰቡ ክፍሎችም ስራቸው ለየት ሆኖ የሚገኝ ነው፡፡ ነጋዴዎች እና አርሶ አደሮችም ስራቸው ከሌላው ሕብረተሰብ ለየት ብሎ ይገኛል፡፡ እንዲሁም የቀን ሰራተኞችም ስራቸው ከሌላው ሕብረተሰብ ለየት ብሎ ይገኛል፡፡ በሰው ልጅ ሕብረተሰብ ውስጥ የተለያዩ የቀን ሰራተኞች፣ ነጋዴዎች፣ ፖለቲከኞች እና አስተዳዳሪዎች ይገኛሉ፡፡ ወይንም ደግሞ አእምሮዋቸው ከፍ ብሎ የሚገኝ በስነፅሁፍ እና በሳይንሳዊ ምርምር ዘርፍ የተሰማሩ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ እያንዳንዱ ሰው የተወሰነ ስራውን ሲሰራ ይገኛል፡፡ ለመኖርም ሲባል እያንዳንዱ ሰው ለመስራት ሲገደድ ይታያል፡፡ ስለዚህ ዓብዩ ጌታ እንደጠቀሰው “የምትሰራውን ስራ እና ሙያ መተው አያስፈልግህም” ነገር ግን በስራህ ላይ የዓብዩ ጌታን መንፈስ እንድታስታውስ ያስፈልግሀል፡፡ “ማም አኑስማራ” (ብጊ 8.7) ይህም በሞት አፋፍ ላይ እያለህ እኔን እንድታስታውሰኝ ይረዳሀል፡፡ እኔንም ለማስታውስ ልምምድ የማታደርግ ከሆነ ከዚህ ትግል ከተሞላበት የዓለማዊው ኑሮ ጋር እኔን ለማስታወስ አስቸጋሪ ይሆንብሀል፡፡ ይህም ምክር እንደገና በጌታ ቼታንያ ተገልጾልናል፡፡ “ኪርታንያህ ሳዳ ሃሪህ” (ቼቻ፡ አዲ 17.31) “ኪርታንያ ሳዳ” አንድ ሰው የዓብዩ ጌታን ቅዱስ ስም ለመዘመር ሁልግዜ ጥረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ የዓብዩ ጌታ ቅዱስ ስም እና ዓብዩ ጌታ ምንም ልዩነት የላቸውም፡፡ ስለዚህም ዓብዩ ሽሪ ክርሽና ለአርጁና እንዲህ ብሎ ገልጾለታል፡፡ “ማም አኑስማራ” (ብጊ 8.7) “እኔን ሁልግዜ አስታውሰኝ፡፡” የጌታ ቼታንያ ትእዛዝም እንዲሁ ነው “የሽሪ ክርሽናን ቅዱስ ስም ሁልግዜ ዘምር፡፡” እዚህም ክርሽና እንዲህ ብሏል “እኔን ሁልግዜ አስታውስ፡፡” ወይም ክርሽናን ሁልግዜ አስታውስ፡፡ ጌታ ቼታንያ ደግሞ “የክርሽናን ቅዱስ ስም ሁልግዜ ዘምር፡፡” ስለዚህ በክርሽና መሀከል እና በሽሪ ክርሽና ቅዱስ ስም መሀከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለም፡፡ ፍፁም በሆነው የመንፈሳዊው ዓለም አንዱ ከሌላው ምንም ዓይነት ልዩነት የለውም፡፡ የፍፁምነት ደረጃ ማለት ይህ ነው፡፡ እንደዚህም ሁሉ ዓብዩ ጌታ ፍፁም እንደመሆኑ ሁሉ በእርሱ እና በቅዱስ ስሙ መሀከል ምንም ዓይነት ልዩነት የለም፡፡ ስለዚህ ይህንን በመረዳት ልምምዳችንን መቀጠል ይገባናል፡፡ “ታስማት ሳርቬሹ ካሌሹ” (ብጊ 8.7) 24 ሰዓት ሙሉ በሕይወታችን የምናደርገውን እንቅስቃሴ ሁሉ በማስተካከል ለ24 ሰዓት ዓብዩ ጌታን የምናስታውስበትን መንገድ መፍጠር አለብን፡፡ ይህስ እንዴት ይቻላል? አዎን ይህ የሚቻል ነገር ነው፡፡ ይህም በአቻርያዎች ወይንም መንፈሳዊ መምህራን በምሳሌ በደንብ ተገልጾልን ይገኛል፡፡ ይህስ ምሳሌ ምንድን ነው? ይህም አንድ ከሌላ ሰው ጋር ፍቅር የያዛት ሴት ምንም እንኳን ባል ቢኖራትም ከሌላ ሰው ጋር ፍቅር ይዟት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ዓይነቱ ፍቅር ሀይል ያለው ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም “ፓራኪያ ራስ” ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህም በሴት ወይንም በወንድ በኩል ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ ሰውም እንዲሁ ከባለቤቱ በተጨማሪ ከሌላ ሴት ጋር ፍቅር ይዞት ከሆነ ወይንም ደግሞ አንድ ሴት ከባለቤትዋ በተጨማሪ ከሌላ ወንድ ጋር ፍቅር ይዟት ከሆነ ይህ ዓይነቱ ፍቅር በጣም ሀይል ያለው እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ አቻርያዎችም ይህን ምሳሌ ሲሰጡ የሴትየዋ ባህርይ አግባብ የሌለው እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡ ይህም ከባልዋ በተጨማሪ ከሌላ ሰው ጋር ፍቅር የያዛት በመሆኑ ነው፡፡ ይህንንም ፍቅረኛዋን ሁልግዜ ታስበዋለች፡፡ በባሏም ደግሞ በቤቷ ውስጥ እንዴት ብዙ ስራ እንደምትሰራ ታሳየዋለች፡፡ ይህም ባልዋ በምንም ነገር እንዲጠረጥራት ስለማትፈልግ ነው፡፡ ከፍቅረኛዋም ጋር እንዴት ምሽቶቹን ታሳልፍ እንደነበረ ሁልግዜ ታስታውሳለች፡፡ የቤት ስራዋንም ሁሉ በደንብ ከመስራት ይልቅ እንደዚህም ሁሉ ዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽናን ሁል ግዜ ማስታወስ ይገባናል፡፡ ምንም እንኳን በቁሳዊ ዓለም ውስጥ ያለውን ሀላፊነታችንን በደንብ ባንወጣም፡፡ ይህም የሚቻል ነገር ነው፡፡ ይህም ጠንካራ የሆነ የዓብዩ ጌታ ፍቅር እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡