AM/Prabhupada 0026 - በመጀመሪያ ደረጃ ክርሽና ወዳለበት ትእይንተ ዓለም ውስጥ ከሞት በኋላ ትተላለፋላችሁ፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

You Are First of all Transferred to the Universe
Where Kṛṣṇa is - Prabhupāda 0026


Morning Walk -- October 5, 1975, Mauritius

አንድ ህንዳዊ እንዲህ ጠየቀ: "ስዋሚጂ: በቬዲክ ትምህርት: በዚህ ኑሮ የምንሰራው ስራ ሁሉ: የወደፊት የትውልድ አይነታችንን ይወስናል: ተብሏል:" “እና ለምንሰራው ስራ ሁሉ:በአማላክ ህግ መሰረት:የትውልድ አይነት ይኖረናል:” ፕራብሁፓዳ እንዲህ አለ:“አዎን በእርግጥ:ትወለዳለህ:ይህንን መራቅ አትችልም:” “ግን ትውልድህ እንደ ካርማህ (ስራህ)ነው: ህንዳዊው ሰው:”እና በዚህ ኑሮ የፃፍነውን ነው የምንረከበው?“ ፕራብሁፓዳ:”ለምሳሌ ይህ ሸሚዝ ሲቀደድብህ ሌላ አዲስ ሸሚዝ ትገዛለህ“ ”ታድያ አዲስ ሸሚዝ ግን የምትገዛው:አቅምህ በፈቀደው ገንዘብ ነው:“ ”ጥሩ ሃብት ካለህ:ጥሩ ሸሚዝ ትገዛለህ:ደህና ገንዘብ ከሌለህ ግን:ርካሽ ሸሚዝ ትገዛህ“ ህንዳዊው ሰው:”ስዋሚጂ ሲኦልም በዚህ ምድር አለ: ለማለት እፈልጋለሁ“ ”ምክንያቱም እንዴት አድርገን ነው እዳችንን በዚህ አለም ላይ ለመክፈል የምንችለው?“ ”ኃጥያታችንን:የኃጥያታችንን እዳ:የት ነው ለመክፈል የምንችለው?“ ”በዚህ ሲኦል ውስጥ?“ ፕራብሁፓዳ: ”ሲኦል ቅጣት የሚከናወንበት ቦታ ነው“ ህንዳዊው ሰው:”እርሱም እዚሁ መሬት ላይ ነው“ ፕራብሁፓዳ:"ለምን እዚህ መሬት ላይ?“ ህንዳዊው ሰው:”የመሬታችን ፕላኔት ላይ:አይደለምን?“ ፕራብሁፓዳ:”አይደለም:ሊሆን የሚችለው“ ህንዳዊው ሰው:”በማንኛቸውም ፕላኔት?“ ፕራብሁፓዳ:”ከዚህ ብዙ ሚልዮን ማይልስ ርቆ ነው የሚገኘው“ ህንዳዊው ሰው:”ሲኦል በአንድ ቦታ ብቻ ነው ያለው ወይንስ በተለያየ ቦታ ነው?“ ”እንዲህ ይመስልሃል ስዋሚጂ?“ ፕራብሁፓዳ:”አዎን የተለያዩ ፕላኔቶች አሉ“ ህንዳዊው ሰው:”በዚህ አለም ላይ ብዙ የሚሰቃዩ ሰዎች አሉ“ ፕራብሁፓዳ:”በመጀመሪያ ደረጃ ሃጥያተኞች ስቃይ ምን እንደሆነ በሲኦል ውስጥ ለምደው ወደ እዚህ አለም እንደገና ለመሰቃየት ይወለዳሉ“ ህንዳዊው ሰው:”ነፍሳችን ከገላችን ስትወጣ ወደ ሲኦል ትሄዳለችን?“ ፕራብሁፓዳ: ”የሲኦል ፕላኔት“ ህንዳዊው ሰው:”በኦል ይወለዳሉ ወይንስ እዚሁ ምድር ላይ ወዲያውኑ ይወለዳሉ?“ ፕራብሁፓዳ:”አዎ:ኃጥያተኞች ወዲያውኑ እዚህ ምድር ላይ አይወለዱም“ በመጀመሪያ በሲኦል ላይ ስቃይ ምን እንደሆነ ይለምዳሉ: ይህንን ስቃይ ምን እንደሆነ ከለመዱ በኋላ ደግሞ:እዚህ አለም ላይ እንደገና ተወልደው ይሰቃያሉ: ልክ የ ”አይ ኤ ኤስ“ ፈተና እንደምታልፈው ሁሉ: ከዚያም የማጂስትሬቱ (ዳኛ)ምክትል ሁነህ ትማራለህ: ከዚያም ወደ ማጂስትሬቱ ደረጃ ትሾማለህ: እንደዚህም ሁሉ ወደ አምላክ ለመመለስ ንጽህና ቢኖርህም እንኳን:በመጀመሪያ ወደ ተላላፊ ፕላኔት ትጓዛለህ: ይህም አሁን ክርሽና በሚገኝበት አለማዊ ዩኒቨርስ ውስጥ:እዚያም ሁነህ የማገልገልን ልምምድ ታደርጋለህ: ከዚያም ወደ እውነተኛው ቭርንዳቫና (መንፈሳዊው አለም)ትጓዛለህ: ህንዳዊው ሰው:”ስለዚህ ሞታችን" ፕራብሁፓዳ:”አማላክ የሚሰራው ስራ ሁሉ እንከን የለውም“ ”ፑርናም ፑርናም አዳሃ ፑርናም ኢዳም ፑርናት ፑርናም“ ኢሾፓኒሻድ ጥቅስ በአማላክ የተፈጠረው ነገር ሁሉ:ፍጹም ነው: