AM/Prabhupada 0198 - መጥፎ ሀጥያታዊ ባህርያችሁን አስወግዳችሁ በእነዚህ መቁጠሪያዎች ላይ ዘምሩ፡፡ ይህም የሀሬ ክርሽናን ማህሌትን ነው፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

Give up these Bad Habits and Chant these Beads, Hare Kṛṣṇa Mantra - Prabhupāda 0198


Temple Press Conference -- August 5, 1971, London

ሴት ጋዜጠኛ፡ በዓለም ላይ ምን ያህል ተከታዮች በአሁን ግዜ አላችሁ ወይንስ መቁጠር ያዳግታል?

ፕራብሁፓድ፡ በእርግጥ እውነተኛ ለሆነ ነገር ተከታዮች ትንሽ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ቆሻሻ ለሆነ ነገር ግን ተከታዮቹ ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሴት ጋዘጠኛ፡ ምን ያህል? ማለቴም ድቁና የወሰዱት ምን ያህል ናቸው?

ፕራብሁፓድ፡ ወደ ሶስት ሺህ ይሆናሉ፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ ታድያ ይህን እያደገ ይገኛልን?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን ቀስ በቀስ እያደገ ይገኛል፡፡ ይህም እኛ ብዙ ነገር ሰለምንከለክል ነው፡፡ ሰዎች ሲከለክሏቸው አይወዱም፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ አዎን በየትኛው አገር ነው ብዙ ተከታዮች ያሏችሁ? በአሜሪካ ውስጥ ነው?

ፕራብሁፓድ፡ በአሜሪካ በአውሮፓ በካናዳ በጃፓን በአውስትራልያ በሕንድ ደግሞ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሉ፡፡ ይህንን የመሰሉ በሚልዮን የሚቆጠሩ እንቅስቃሴዎች አሉ፡፡ ከሕንድ ውጪ በሌላ አገሮች ውስጥ ብዛታቸው ትንሽ ነው፡፡ በሕንድ አገር ግን በሚዮን የሚቆጠሩ ይገኛሉ፡፡ ወንድ ጋዜጠኛ፡ ፈጣሪ አምላክን ለማወቅ የሚቻለው በዚህ ድርጅት ብቻ ነው ብለህ ታምናለህ?

ፕራብሁፓድ፡ ምን አልክ? ድቮቲ፡ ፈጣሪ አምላክን ለማወቅ የሚቻለው በዚህ ድርጅት ብቻ ነው ብለህ ታምናለህ ወይ?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን፡፡ ወንድ ጋዜጠኛ፡ እንዴት ይህንን ለማረጋገጥ በቃህ?

ፕራብሁፓድ፡ ከባለሰልጣኖች ከዓብዩ አምላክ ከክርሽና ክርሽና እንዲህ ብሏል “ሳርቫ ድሀርማን ፓሪትያጃ ማም ኤካም ሸራናም ቭራጃ” (ብጊ፡ 18 66) ወንድ ጋዜጠኛ፡ ታድያ ሌላ ሰው ፈጣሪ አምላክ እንዲህ ብሎኛል ቢልህ ታምነዋለህ? ሽያማሱንደር፡ ይህ ማለት ሌሎች የሀይማኖት ስርዓቶችን አንቀበልም ማለት አይደለም፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አይደለም፡፡ ሌሎች ስርዓቶችን እናምንባቸዋለን፡፡ ለምሳሌ ደረጃዎች አሉ፡፡ ወደ ከፍተኛው ወለል ለመሄድ ከፈለግህ ደረጃዎችን መጠቀም ትችላለህ፡፡ እንደዚህም ሁሉ አንዳንድ ስርዓቶች ሀምሳ ደረጃዎች ሊኖራቸው ይችላል፡፡ አንዳንዶችም ደግሞ አንድ መቶ ደረጃዎች ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ለመጨረስ አንድ ሺህ ደረጃዎች ያሰፈልጉ ይሆናል፡፡ ወንድ ጋዜጠኛ፡ እናንተ አንድ ሺህ ደረጃዎች ሂደናል ነው የምትሉት? ፕራብሁፓዳ፡ አዎን ሴት ጋዜጠኛ፡ እዚህ ከአለነው መካከል ውስጥ አንዳችን ተከታዮች ለመሆነ ከፈለግን ምን መስጠት ወይንም ምን መተው ነው ያለብን፡፡

ፕራብሁፓድ፡ በመጀመሪያ አግባብ የሌለው የወሲብ ግኑኝነት ማቆም ያሰፈልጋል፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ ይህስ ማለት ማናቸውንም አይነት የወሲብ ግኑኝነት ማለት ነውን? ኢሊሲት ማለት ምንድነው?

ፕራብሁፓድ፡ ኢሊሲት የወሲብ ግኑኝነት ማለት በትዳር ያልተደገፈ የወሲብ ግኑኝነት ማለት ነው፡፡ ያለ ትድዳር የወሲብ ግኑኝነት ማለት ኢሊሲት የሆነ ወሲብ ማለት ነው፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ ሰለዚህ ወሲብ በትዳር ይፈቀደል ከትዳር ውጪ ግን አይፈቀድም፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ከትዳር ውጪ ወሲብ የእንስሳ ኑሮ ማለት ነው፡፡ ልክ እንደ እንስሶች ምንም የትዳር ግኑኝነት የላቸውም የወሲብም ግኑኝነት ከማንም ጋር አላቸው፡፡ ነገር ግን በሰው ልጅ ሕብረተሰብ ውስጥ ቁጥጥር አለ፡፡ በእያንዳኑዱ አገር እና በእያንዳንዱ ሀይማኖት የትዳር ስርዓት አለ፡፡ ሰለዚህ ያለ ትዳር የወሲብ ግኑኝነት አግባብ የሌለው የወሲብ ግኑኝነት ነው፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ ነገር ግን ወሲብ በትዳር ላይ የተፈቀደ ነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አዎን፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ ሌላስ ነገር ምንድነው መተው የሚገባን?

ፕራብሁፓድ፡ ሱሰኛ የሚያደርጉ እና የሚያሰክሩ ነገሮች ሁሉ መተው አለባቸው፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ እንደ ሀሺሽ እና እነደ አልኮል ማለት ነው?

ፕራብሁፓድ፡ ማንም አይነት የሚያሰክር ነገር ሁሉ መቆም አለበት፡፡ ሽያማሱንዳር፡ ይህ ሻይንም ይጨምላል፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ይህ ሻሂን ሲጋራን ሁሉ ይጨምራል ምክንያቱም ሱስ ስለሚያስይዙ ነው፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ እነዚህ አልክሆል ማሪዋና ሻሂን ይጨምራሉ፡፡ ሌላስ ነገር ምን አለ?

ፕራብሁፓድ፡ የእንስሳ ምግብም መቆም አለበት፡፡ ማናቸውም ዓይነት የእንስሳ ምግብ የተከለከለ ነው፡፡ ስጋ እንቁላል አሳን የመሳሰሉትን ነው፡፡ በተጨማሪም ቁማርንም መተው ያሰፈልጋል፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ አንድ ሰው ቤተሰቡንስ ትቶ መሄድ ያሰፈልገዋልን? እንደምናየው ሁሉም በቤተ መቅደስ ውስጥ ነው የሚኖረው፡፡ አይደለም?

ፕራብሁፓድ፡ አዎን፡፡ አንድ ሰው እነዚህን ሁሉ ሀጥያታዊ ነገሮች ሁሉ ካልተወ በመንፈሳዊው ድቁና ስርዓት ውስጥ ሊሰማራ አይችልም፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ ሰለዚህ አንድ ሰው ቤተሰቡንም ትቶ መሄድ ያሰፈልገዋልን?

ፕራብሁፓድ፡ ቤተሰብ? ሴት ጋዜጠኛ፡ አዎን

ፕራብሁፓድ፡ ቤተሰብ? እኛ ትኩረት ያለን ሰለ ግለሰቡ ነው እንጂ ሰለቤተሰቡ አይደለም፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው በክርሽና ንቃታችን ድቁና ስርዓት ለመሰማራት ከፈለገ ሁሉንም ዓይነት የሀጥያት ስራዎችን ማቆም ይገባዋል፡፡ ሴት ጋዜጠኛ: ሰለዚህ ቤተሰብንም መተው ያሰፈልጋል ማለት ነውን? ታድያ .... ሽያማሱንዳር፡ አይደለም ቤተሰብ መተው አያሰፈልግም፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ እኔ የምለው ለምሳሌ የድቁና ስርዓት ለመቀበል ከፈለግሁኝ ቤተሰብ ትቼ መጥቼ እዚህ መኖር አለብኝ ወይ? ሽያማሱንዳር፡ አይደለም

ፕራብሁፓድ፡ ያ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ አሀ ቤት መቀመጥ እችላለሁ ማለት ነው? ፕራብሁፓድ: አዎን ሴት ጋዜጠኛ፡ የስራስ ጉዳይ እንዴት ነው? ስራ መተው ያሰፈልጋልን?

ፕራብሁፓድ፡ መተው የሚያስፈልገው መጥፎ ባህርዮችን ብቻ እና በየግዜው የሀሬ ክርሽናን ቅዱስ ስም መዘመር ብቻ ነው፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ የገንዘብ እርዳታ ማድረግ ይገባኛል?

ፕራብሁፓድ፡ አያስፈልግም ይህ የአንቺ ፈቃደኝነት ብቻ ነው፡፡ እርዳታ ብታደርጊ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን ግዴታ የለውም፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ ይቅርታ አልገባኝም

ፕራብሁፓድ፡ በማንም ሰው የገንዘብ እርዳታ አንተማመንም፡፡ የምንተማመነው በፈጣሪ አምላክ በክርሽና ነው፡፡ ሴት ጋዜጠኛ፡ ሰለዚህ ምንም ዓይነት ገንዘብ መስጠት አይጠበቅብኝም ማለት ነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አይጠበቅም ሴት ጋዜጠኛ፡ አንድ እውነተኛን ጉሩ (መንፈሳዊ መምህር) ከሌሎች አታላዮች ለይቶ የሚያሳይ አንዱ መንገድ ይህ ነውን?

ፕራብሁፓድ፡ እውነተኛ ጉሩ በንግድ የተሰማራ አይደለም፡፡