AM/Prabhupada 0205 - እነዚህ ሰዎች ይህንን ያህል የክርሽና ንቃትን ይቀበሉታል ብዬ አልገመትኩም ነበረ፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

I Never Expected that "These people will Accept" - Prabhupāda 0205


Morning Walk -- May 20, 1975, Melbourne

ፕራብሁፓድ:ስትሰብኩ:የግድ የክርሽና ንቃት መውሰዱን ማየት የለባችሁም:ክርሽና ንቃትን ማዳበር ቀላል ነገር አይደለም: ቀላል አይደለም:ብዙ ትውልድም ሊጠይቅ ይችላል:“ባሁናም ጃንማናም አንቴ” (ብጊ 7 19) ነገር ግን ሃላፊነታችሁን መወጣት አለባችሁ:“ያሬ ዴክሃ ታሬ ካሃ ክርሽና ኡፓዴሽ” (ቼቻ ማድህያ 7 128) ስትሰብኩ ሃላፊነታችሁን ተወጣችሁ ማለት ነው: በእርግጥ እንዲቀበሏችሁ ለማድረግ ጥረት ያስፈልጋል: ሊቀበሏችሁ ካልቻሉ ግን:ያ የእናንተ የስራ መዘናጋት እና መሳሳት አይደለም: ሃላፊነታችሁ ሂዶ መስበክ ብቻ ነው: ልክ እኔ ወደ አገራችሁ ስመጣ:ምንም ነገር ይሳካል ብዬ አልጠበቅሁም ነበር: ምክንያቱም:ልክ እንደዚህ ስል:”ማመንዘር:ስጋ መብላት:አይፈቀድም“ ስል ትተውኝ ይሄዳሉ ብዬ ነበር:(ሳቅ) ስለዚህ ተስፋም አልነበረኝም: ድቮቲ 1:እነዚህን በጣም ይወዳሉ:

ፕራብሁፓድ:አዎን:ነገር ግን በእናንተ ሩሁርሁነት ተቀብላችሁኛል:ነገር ግን የጠበቁት ነገር አልነበረም: እነዚህ ሰዎች ይቀበሉኛል ብዬ በፍጹም አልጠበኩትም: ሀሪ ሶሪ:በክርሽና መተማመን አለብን:

ፕራብሁፓድ:አዎን:ያ ነው የእኛ ሃላፊነት: ሀሪ ሶሪ:ውጤቱን ከጠበቅን:

ፕራብሁፓድ:የመንፈሳዊ አባታችንን እንደ አዘዘን: ሃላፊነታችንን መወጣት አለብን: ”ጉሩ ክርሽና ክርፓያ“ (ቼቻ ማድህያ 19 151) እንደዚሁም ሁሉ ከሁለቱም ወገን ትካሳላችሁ:ከመንፈሳዊ አባት እና ከክርሽና: ይህም የህይወታችሁ መሳካት ነው: