AM/Prabhupada 0405 - የሰይጣን አንደበት ያላቸው አብዩ ጌታ አብይ ሰው እንደመሆኑ ለመረዳት ያዳግታቸዋል፡፡ ይህም የከሀዲያን አስተሳሰብ ነው፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

የሰይጣን አንደበት ያላቸው አብዩ ጌታ አብይ ሰው እንደመሆኑ ለመረዳት ያዳግታቸዋል፡፡ ይህም የከሀዲያን አስተሳሰብ ነው፡፡
- Prabhupāda 0405


Lecture on SB 7.7.30-31 -- Mombassa, September 12, 1971

ሰይጣናዊ አንደበት ያላቸው አምላክ ሰው መሆኑን አይረዱም:ይህም ሰይጣናዊ ነው: ሊረዱት አይችልም:ይህም ከእራሳቸው ጋር አምላክን ሊያወዳድሩ ስለሚፈልጉ ነው: ዶክተር እንቁራሪት:እንደዚህ ነው ታሪኩ አትላንቲክ ውቅያኖስን ለመረዳት ፈለገ ይህንንም ያመዛዝን የነበረው 3 ፊት ከምትሆነው ኩሬው ነው: ስለ አይቶት የማያውቀውን አትላንቲክም ሲያጫውቱት:እርሱም ከራሱ ትንች ኩሬ ጋር ማወዳደር ጀመረ: 4 ወይንም 5 ፊት ሊሆን ይችላል:ወይንም 10 ፊት ብሎ ያሰባል:ይህም ከራሱ 3 ፊት ጋር ስለሚያወዳድረው ነው: ይህም ጓደኛው ትልቅ ውቅያኖስ አይቼ መጣሁ ስለአለው ነው: ይህንንም ግዙፍነት ባለው ልምድ ለማመሳከር ፈለገ: የኔ ይህን ያህል ነው እያለም ማሰላሰል ቀጠለ:3 ፊት 4 ፊት 5 ፊት ነገር ግን በሚሊዮን ፊትም ማሰላሰል ቢሞክር ትልቅነቱን ሊረዳ አይችልም: እንደዚህም እነዚህ ከሃዲያን እና ሰይጣናውያን:አምላክን እንደራሳቸው እየቆጠሩ ማወዳደር ይፈልጋሉ: ክርሽና እንዲህ ሊሆን ይችላል:ክርሽና እንዲህ ሊሆን ይችላል: በጠቅላላው አነጋገር እነርሱ እና ክርሽና አንድ እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ:እንዴትስ ይህ ሊሆን ይችላል? ክርሽና አብይ እንደሆነ አያምኑም: አምላክ እንደ እኔ ነው ብለው ያስባሉ:እኔም አምላክ ነኝ:ይህ ሰይጣናዊ አስተሳሰብ ነው: