AM/Prabhupada 0423 - እኔ ለእናንተ ስል በጣም ስደክም እገኛለሁ እናንተ ግን ይህንን እድል ስትጠቀሙበት አትታዩም፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

እኔ ለእናንተ ስል በጣም ስደክም እገኛለሁ እናንተ ግን ይህንን እድል ስትጠቀሙበት አትታዩም፡፡
- Prabhupāda 0423


Lecture on SB 2.9.14 -- Melbourne, April 13, 1972

ይህም በጣም ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው፡፡ እድሉም እዚህ አለ፡፡ በላክሽሚ እድሉ ተሰጥቶናል፡፡ ክርሽናን እንዴት ማገልገል እንደምንችል፡፡ “ላክሽሚ ሳሀስራ ሻታ ሳምብህራማ ሴቭያማናም” (ብሰ፡5 29) በአንድ ሕይወት በመሞከር ብቻ ወደ ክርሽና ቤተ መንግስት ለመግባት ብቁ ለመሆን የምችል ከሆነ ገብቼም ዘለዓለማዊ ኑሮ ደስታ የተሞላበት ከሆነ እና ይህንንም እድል እርግፍ አድርጌ የምተው ከሆነ ምን ያህል ዕድለ ቢስ ነኝ? አገልግላችሁ ከሞት በኋላ ብትወድቁ እንኳን እንደገና የመዘወወሩ ዕድል ይኖራችኋል፡፡ ምንም እንኳን እድል ባይኖረን ምንም እንኳን ሙሉ አገልግሎት ባንሰጥ ምንም እንኳን ብንወድቅ የሰጠነው ትንሽም አገልግሎት እንኳን ወዳቂ አይደለም፡፡ “በረከት ያለው ነው” ምክንያቱም ለሚቀጥለው ትውልዳችን ቢያንስ ቢያንስ የሰው ትውልድ እድል እንደምናገኝ የተረጋገጠ ነው፡፡ ነገር ግን ለካርሚዎች የሚቀጥለው ትውልዱ ምን ዓይነት እንደሆነ ሊታወቅ አይችልም፡፡ የተሰጠም መረጃ የለም፡፡ ያም ያም ቫፒ ስማራን ሎኬ ትያጃትዪ አንቴ ካሌቫራም (ብጊ፡ 8 6) ዛፍ ለመሆን ይችላል፡፡ ድመት ሊሆን ይችላል፡፡ ደሚጎድ ሊሆንም ይችላል፡፡ ከመላእክት በላይ ግን ሊሆን አይችልም፡፡ ይኅው ነው፡፡ መላእክት ማለትስ ምንድን ነው? እነርሱም በከፍተኛዎቹ የገነት ፕላኔቶች ውስጥ የመኖር እድል አላቸው ከዚያም ወደ ዝቅተኛው ዓለማት ሊወድቁ ይችላሉ፡፡ ክሽኔ ፑንዬ ፕናር ማርትያ ሎካም ቪሻንቲ የመንፈሳዊ ባንክ ገቢያቸው ሲያልቅ ፑንያ ወይንም ጥሩ ለሰሩበት ደስታውን ካገኙ በኋላ እና ስጦታቸው ሲያልቅ እንደገና ወደ ታችኛዎች ፕላኔቶች መምጣታቸው የማይቀር ነው፡፡ ”አብራህማ ብሁቫና ሎካን ፑናር አቫርቲኖ ርጁና“ ምንም እንኳን ወደ ከፍተኛው የትእይንተ ዓለም ፕላኔት ወደ “ብራህማ ሎካ” ጌታ ብራህማ ወደሚኖርበት ፕላኔት ብንሄድ እንኳን ወደ ዝቅተኞቹ ፕላኔቶች መውደቃችን አይቀርም፡፡ በዚህም ብራህማ ሎካ የአንድ ቀኑን ርዝመት በእኛ ቀናቶች እንኳን ለመቁጠር የማይቻል ነው፡፡ ማድ ድሀማ ጋትቫ ፑናር ጃንማ ና ቪድያቴ “ነገር ግን ወደ እኔ የምትመጡ ከሆነ ወደ እነዚህ ዝቅተኛ ፕላኔቶች እንደገና ተመልሳችሁ አትመጡም፡፡ የክርሽና ንቃት የሚሰጠው ዕድልም ይህንን ነው፡፡ ትያክትቫ ስቫ ድሀርማም ቻራናምቡጃም ሀሬር ብሀጃን አፓክቮ ትሀ ፓቴት ታቶ ያዲ ያትራ ክቫ ቫብሀድራም አብሁድ አሙሳ ኪም ኮ ቫርትሀ አፕቶ ብሀጃታም ስቫ ድሀርማታሀ (ሽብ፡ 1.5.17) ታስያይቫ ሄቶህ ፕራያቴታ ኮቪዶ ና ላብህያቴ ያድ ብህራማታም ኡፓርይ አድሀሀ ታል ላብህያቴ ድሁክሀቫድ አንያታሀ ሱክሃም ካሌና ሳርቫትራ ጋብሂራ ራምሀሳ (ሽብ፡ 1.5.18) ይህንን ሁሉ ማንበብ አለባችሁ፡፡ አታነቡ ይሆናል፡፡ በብሀገቨታ የመጀመሪያው ቮልዩም ይህ ሁሉ ተጠቅሷል፡፡ ነገር ግን ይህንን ሁሉ የምታነቡ አይመስለኝም፡፡ ታነባላችሁን? የማታነቡም ከሆነ ረጋ ያለ መንፈስም አይኖራችሁም፡፡ ”ኦ ከጃፓን ወደ ህንድ ልሂድ ከህንድም ወደ ጃፓን ልሂድ“ ይህም ረጋ ያላለ መንፈስ የሚመጣው ስለማታነቡ ነው፡፡ እኔ ለእናንተ በጣም እየታገልኩ እገኛለሁ፡፡ እናንተ ግን እራሳችሁን ተጠቃሚ እያደረጋችሁ አትገኙም፡፡ የመብላት እና የመተኛትን ጥቅም ብቻ አትውሰዱ፡፡ እነዚህንም መፃህፍቶችንም ተጠቀሙባቸው፡፡ ከዚያም ሕይወታችሁ የተሳካ ይሆናል፡፡ የእኔ ሀላፊነት ከፍተኛ ዋጋ ያለቸውን ነገሮች መስጠት ነው፡፡ ከዚያም ተርፎ ሌት ተቀን እናንተን ቃል በቃል ለማሳመን ጥረት እያደረግሁ ነው፡፡ ይህንን ግን እናንተ የማትጠቀሙበት ከሆነ እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ?