AM/Prabhupada 0485 - ሽሪ ክርሽና በምድር ላይ የፈፀመው ታሪክ ሁሉ በአገልጋዮቹ እንደሴረሞኒ ሆኖ ሲታዋስ ይገኛል፡፡



Lecture -- Seattle, October 18, 1968

እንግዳ፡ ሰለ ጃጋናት የሰረገላ በዓል መነሻ እና ለምንስ እንደሚከበር ብትገልጽልን በጣም ደስ ይለናል፡፡ ለምንስ የጃጋናት በዓል እንደተባለ ብትገልጽልን

ፕራብሁፓድ፡ የጃገናት በዓል ቁም ነገራዊ ታሪክ እንዲህ ነው፡፡ ክርሽና ቭርንዳቫናን ሲለቅ ክርሽና ያደገው በአሳዳጊ አባቱ ናንዳ መሀራጅ ነበረ፡፡ ነገር ግን ከአደገ በኋላ እና 16 ዓመት ሲሞላው በወላጅ አባቱ በቫሱዴቭ ተወስዶ ነበረ፡፡ ወንድማማቾቹም ክርሽና እና ባላራምም ቭርንዳቨናን ለቀው ሂደው ነበረ፡፡ ነዋሪዎችም ነበሩ፡፡ ቤተ መንግስታቸውም በድዋርካ ውስጥ ነበረ፡፡ በኩሩክሼትራ ውስጥም ....ኩሩክሼትራ ሁልግዜ የሀይማኖት ስርዓት የሚካሄድበት ነበረ "ድሃርማ ክሼትራ" ቅዱስ ቦታ ነበር። በዚያን ግዜ የጨረቃ ኤክሊፕስ ነበረ፡፡ ብዙ ሰዎችም ከተለያየ ክፍለ ሀገር ወደ እዚሁ ቅዱስ ቦታ መጥተው ነበረ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ክርሽና እና ባላራማ ከእህታቸው ከሱባድራ ጋር መጥተው ነበረ፡፡ የመጡትም እንደ ነገስታት አሸብረቀው ነበረ፡፡ በብዙ ወታደሮች ተከበው እንደ ንጉስ ሆነው ነበረ የመጡት፡፡ እነዚህም የቭርንዳቫን ነዋሪዎች ክርሽናን አግኝተውት ነበረ፡፡ በተለይ ጐፒዎቹ ሁሉ ክርሽናን ዓይተውት ነበረ፡፡ እንዲህ በማለትም እያዘኑ ተናገሩ፡፡ "ክርሽና አንተ እዚህ ነህ፡፡ እኛም እዚህ ነን፡፡" "ነገር ግን ቦታው በጣም የተለየ ነው፡፡ እኛም በቭርንዳቫን ውስጥ አይደለንም፡፡" ሰለዚህም በጣም ትልቅ የሆነ ታሪክ አለ፡፡ ይህም የሚያስረዳው እንዴት እነርሱ እንዳዘኑ እና እንዴት ክርሽናም ሊያፅናናቸው እንደሞከረ ነው፡፡ ይህም በዓል የሚያስታውሰው በሁለቱ መሀከል ያለውን መለያየት እና እንዴት የቭርንዳቫን ነዋሪዎች በክርሽና መለየት እንዴት ቅሬታ እንደተሰማቸው ነው። ሰለዚህም ክርሽና በሰረገላው ላይ ወጥቶ ሲሄድ ይህ ራትሀ ያትራ ይባላል፡፡ የራትሀ ያትራ ታሪክም ይኅው ነው፡፡ ሰለዚህም ማናቸውም በክርሽና የተፈፀመ ታሪክ በአገልጋዮቹ እንደ ሴረሞኒ እየተደረገ ይታሰባል፡፡ ይህ ነው ራትሀ ያትራ ተብሎ የሚታወቀው በዓል፡፡